Vehicle (garage service)
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ፍትህ ቢሮ የሚገለገልበቸውን መኪናዎች ለአንድ አመት በሚቆይ ኮንትራት ለማስጠገን ይፈልጋል
Description
የተሽከርካሪ ጥገና አገልግሎት ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ፍትህ ቢሮ የሚገለገልበቸውን መኪናዎች ለአንድ አመት በሚቆይ ኮንትራት ለማስጠገን ይፈልጋል።
በዚህም መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ድርጅቶች በጨረታው እንድትሳተፉ ይፈልጋል።
1. በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ለመክፈላቸው መረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
2. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (T NO)ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ፣
3. በትራንስፖርት ሚኒስቴር ወይም በደ/ኢ/ክ/መ/ትራንስፖርት ቢሮ ወይም ደረጃ 3 እና ከዚያ በላይ የብታት ማረጋገጫ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 25,000.00 /ሃያ አምስት ሺህ ብር/ብቻ በባንክ በተረጋገጠ CPO/ሲ.ፒ.ኦ/ ጨረታ ከመከፈቱ በፊት ማስያዝ አለባቸው።
5 .የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከመ/ቤቱ ግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በግንባር ቀርበው ወይም በህጋዊ ወኪሎቻቸው አማካኝነት የማይመለስ 400.00/አራት መቶ ብር/ በመከፈል መግዛት ይችላሉ።
6. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ የጥገና አገልግሎት ዋጋ ላይ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) በማካተት ኦርጅናል እና ኮፒውን የፋይናንሻል እና ቴክኒካል ሰነዶችን በተለያየ ፖስታ /ኢንቨሎፕ በሰም በማሸግ ዘወትር በስራ ሰዓት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ተከታታይ ቀን 4፡00 ሰዓት ድረስ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፍትህ ቢሮ ግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በግንባር በመቅረብ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
7. የጨረታው ሳጥን በ16ተኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡15 ሰዓት ላይ ይታሸግና በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፤16ተኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን ከላይ በተገለጸው ሰዓት ይከፈታል።
8. ተጫራቾች በቂና ምቹ የጥገና መስጫ ቦታ ያላቸው መሆኑን ለጨረታ ኮሚቴዎች ማሳየት ይኖርባቸዋል።
9. መስሪያ ቤቱ የተሸለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ፦ በስልክ ቁጥር 0931561347/0913304979 ደውለው መጠየቅ ይችላል።
በደ/ኢ/ክ/መንግስት ፍትህ ቢሮ ግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፍትህ ቢሮ
ሳውላ
Tender details
- Deadline: 2026-10-19
- Bid closing time: 10:15
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ተኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡15 ሰዓት
- Bid opening: 2026-10-19 10:30
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ተኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
- Region: South Ethiopia Regional State
- Publishing entity: Southern Ethiopia Regional Government Justice Bureau
- Bid bond: 25,000.00 /ሃያ አምስት ሺህ ብር/
- Bid document price: 400.00 /አራት መቶ ብር/
- Published on: Addis Zemen (Oct 04, 2026)
- Posted at: 2026-10-05T09:55:46.000Z
- Source: Qelal Tenders