Textile, Garment and Leather

የዲላ ትምህርት ኮሌጅ የተዘጋጁ የደንብ ልብሶችና ጫማዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 03/2019

የዲላ ትምህርት ኮሌጅ

ሀ/ የተዘጋጁ የደንብ ልብሶችን ማለትም

1. የተዘጋጁ የደንብ ልብሶችና ጫማዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በዚሁ መሰረት ከላይ የተጠቀሱትን የተዘጋጁ የደንብ ልብሶችንና ጫማዎችን ዋጋ ቫትን አካቶ በመሙላት ኮሌጁ ለዚሁ ሥራ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

ለ/ በዚሁ መሰረት

1 በጨረታው የሚሣተፉ ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር አጠናቅቀው የከፈሉ፣ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው መሆን ይኖርባቸዋል።

2/ ተጫራቾች በ(VAT) ከፋይነት መመዝገባቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።

3/ ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሣብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ እንዲሁም ከጨረታው ራሣቸውን ማግለል አይችሉም።

4/ የሀገር ውስጥ ተጫራቾች በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ስለመሆናቸው የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት የሚያቀርቡ መሆን ይኖርባቸዋል።

5/ ተጫራቾች በጨረታው ለሚሣተፋባቸው ዕቃዎች ካቀረቡት ጠቅላላ ዋጋ ከላይ የተገለጸውን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 12000.00 /አስራ ሁለት ሺህ/ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (CPO) ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

6/ ተጫራቾች በጨረታው ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል መሳተፍ ይችላሉ።

7/ ተጫራቾች ናሙና ለሚያስፈልጋቸው ዕቃዎች ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

8/ የተዘጋጀ የደንብ ልብስና ጫማ በሳምፕል መልክ ማቅረብ ይኖርበታል።

9/ የቀረበው የተዘጋጀ የደንብ ልብስና ጫማ ሳምፕል ጨረታው ተከፍቶ ከመታየቱ በፊት ስለትክክለኛነቱ በባለሙያ ታይቶ ትክክለኛ ያልሆነ ሳምፕል ያቀረበ ተጫራች ከጨረታ ውጭ ይደረጋል።

10/ ኮሌጁ በጨረታው አሸናፊ ለሆነው ድርጅት ከፍያ የሚፈጽመው በኢትዮጵያ ብር ብቻ ነው።

11/ ተጫራቾች ለጨረታው የሚያቀርቧቸውን ሠነዶች ዋናውንና ኮፒውን እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናቸውን በሚገባ በታሸገ ኤንቨሎፕ ውስጥ በማሸግ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ አስራ ስድስተኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ የዲላ ትምህርት ኮሌጅ የግልጽ ጨረታ ቁጥር 03/2019 ዓ/ም በማለት ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

12/ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ይቆያል። ጨረታው በ16ኛው የስራ ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከቀኑ በ8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመሥሪያ ቤቱ የማኔጅመንት መሰብሰቢያ አዳራሽ በግልጽ ይከፈታል።

13/ የጨረታው አሸናፊ ድርጅት በጨረታው ያሸነፈባቸውን ዕቃዎች ማንኛውንም ወጪ የጉምሩክ ቀረጥን ጨምሮ በመሸፈን ዕቃዎቹን የሚያስረክበው ዲላ ትም/ ኮሌጅ ነው።

14/ ተጫራቾች ለጨረታ በሠነድ ላይ ያቀረቡት ዋጋ ያሸነፉባቸውን የተዘጋጁ የደንብ ልብሶች እስከሚያስረክቡበት ጊዜ ድረስ ፀንቶ የሚቆይ ይሆናል።

15/ ተጫራቾች የጨረታ አሸናፊ መሆናቸው ከተረጋገጠ በኋላ የመልካም ሥራ አፈፃፀም ዋስትና 10% በማስያዝ ከመሥሪያ ቤቱ ጋር የሽያጭ እና የግዥ ውል ይፈራረማሉ።

16/ የቀረበው የተዘጋጀ የደንብ ልብስና ጫማ ሳምፕል ጨረታው ተከፍቶ ከመታየቱ በፊት ስለትክክለኛነቱ በባለሙያ ታይቶ ትክክለኛ ያልሆነ የተዘጋጀ የደንብ ልብስና ጫማ ያቀረበ ተጫራች ከጨረታ ውጭ ይደረጋል።

17/ ተጫራቾች የሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሀሳብ የዕቃዎቹን አይነት፣ የአምራቹን ስም፣ የተመረተበትን ሀገር፣ የሞዴል ቁጥርና የተመረተበትን ዓመት ጭምር ማካተት ይኖርበታል።

18/ አሸናፊው ድርጅት የተዘጋጀ የደንብ ልብስ የሚያቀርብ ስለሆነ የእያንዳንዱን ሠራተኛ ልብስ ልኬትና የጫማ ቁጥር እንዲሁም የሸሚዝ ቁጥር ቦታው ላይ በመገኘት ለክቶ የሚወስድ ይሆናል።

19/ የደንብ ልብሱ ከለር ለሥራ መደቦቹ ተስማሚ የሆነ ወጥ ከለር መሆን ይኖርበታል።

20/ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት (CPO) ለተሸናፊዎች ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል።

21/ የጨረታ ሰነዱን በዲላ ትምህርት ኮሌጅ አካውንት ቁጥር 1000200244382 ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ሰነዱን ከግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር በግዥ ማግኘት ይችላሉ።

22/ መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ እንዲሁም ብዛት የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ይሆናል።

ለበለጠ መረጃ

የዲላ ትምህርት ኮሌጅ ስ.ቁ 046-331-36-29

የዲላ ት/ኮ/ግ/ፋ/ን አስተዳደር ስ.ቁ 046331-42-51

ፋክስ 046-331-24-92

በደ/ኢት/ክ/መ/ትምህርት ቢሮ የዲላ ትምህርት ኮሌጅ


Tender details

  • Deadline: 2026-10-19
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid closing (note): ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው የስራ ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-10-19 14:30
  • Bid opening (note): ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው የስራ ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት
  • Region: South Ethiopia Regional State
  • Publishing entity: Dilla Education College
  • Bid bond: 12,000.00 ብር
  • Bid document price: 100.00 /አንድ መቶ ብር/
  • Published on: Addis Zemen (Oct 04, 2026)
  • Posted at: 2026-10-05T10:44:11.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders