Raw Materials and Supplies
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት የጌዴኦ ዞን ግብርና መምሪያ በ2019 በጀት ዓመት በዞኑ ውስጥ ለሚገኙት ለቡሌ እና ለራጴ ወረዳ አሲዳማ አፈርን ለማሻሻል አገልግሎት የሚውል የአፈር ኖራ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Raw Materials and SuppliesAgriculture and FarmingProducts and Services
South Ethiopia Regional State
Description
የአፈር የኖራ ግዥ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት የጌዴኦ ዞን ግብርና መምሪያ በ2019 በጀት ዓመት በዞኑ ውስጥ ለሚገኙት ለቡሌ እና ለራጴ ወረዳ አሲዳማ አፈርን ለማሻሻል አገልግሎት የሚውል የአፈር ኖራ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች፣
- በበጀት ዓመት በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችል፣
- የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤
- የአቅራቢነት ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤
- የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያለው፤
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤
- በግብርና ሚንስቴር የጥራት የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤
ከላይ በዝርዝር የተቀመጡ መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 21 ቀናት የጨረታ ሰነዱን ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ 500 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ሰነዱን ከጌዴኦ ዞን ፋይናንስና ፕላን መምሪያ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆን ይኖርበታል፣ ቫትን ያላከተተ ከሆነ ቫትን እንዳካተተ ተደርጎ ይቆጠራል።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 100,000 /አንድ መቶ ሺህ ብር/ በባንከ በተረጋገጠ /CPO/ ሲፒኦ፤ ወይም በባንክ ዋስትና ማቅረብ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የሚሸጡበትን ዋጋ በተዘጋጀው ዝርዝር ሰነድ ላይ ዋጋ ሞልተው አንድ ኦርጅናል ሰነድ እና ሁለት ኮፒ ሰነድ በተለያየ ፖስታ ካሸጉ በኃላ ከሲፒኦ ጋር በአንድ ትልቅ ፖስታ በሰም በማሸግ ማቅረብ ይገባቸዋል።
- ኦርጅናልና ኮፒ ሰነድ ላይ ማንኛውም አይነት ስርዝ ድልዝ /በፍሉድ/ የተስተካከለ በሚታይ መልኩ በድጋሚ ተጽፎ በተጫራች ወይም በህጋዊ ተወካይ መፈረም አለበት፤
- በእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ ላይ ህጋዊ የድርጅት ማህተምና ፊርማ ማረፍ አለበት፤
- ጨረታዉ የሚከፈተው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ወጥቶ በአየር ላይ ከዋለበት በተከታታይ በሚቆጠር 21 ቀናት በኋላ በ22ኛው ቀን ጠዋት የጨረታው ሳጥን በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ስለሆነም ተጫራቾች በዕለቱ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 4፡00 ሠዓት ባለው ጊዜ የመወዳደሪያ ሰነዶቻቸውን በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። 22ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ጨረታዉ የሚከፈት ይሆናል።
- የጨረታው ሳጥን የሚገኘው በጌዴኦ ዞን ፋይናንስና ፕላን መምሪያ ቅጥር ግቢ ግዥና ንብ/አስ/ዋና ሥራ ሂደት ነው።
- ተጫራቾች በጨረታው ተወዳድረው ያሸነፉትን ኖራ ጌዴኦ ዞን ቡሌ ከተማ እና ራጴ ወረዳ ሃሮ ወላቦ ቀበሌ ድረስ የማጓጓዣ፣ የማስጫኛ እና የአውራጅ ወጪ ችለው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ
በስልክ ቁጥር: 046-131-0108 መደወል ይችላሉ።
በጌዴኦ ዞን ፋይናንስና ፕላን መምሪያ የግዥና ንብ/አስ/ዋና ሥራ ሂደት
ዲላ
Tender details
- Deadline: 2026-10-24
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ወጥቶ በአየር ላይ ከዋለበት በተከታታይ በሚቆጠር 21 ቀናት በኋላ በ22ኛው ቀን ጠዋት በ4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-10-24 10:30
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ወጥቶ በአየር ላይ ከዋለበት በተከታታይ በሚቆጠር 21 ቀናት በኋላ በ22ኛው ቀን ጠዋት በ4፡30 ሰዓት
- Region: South Ethiopia Regional State
- Publishing entity: Gedeo Zone Finance and Economic Development Command Bureau
- Bid bond: 100,000.00 ብር
- Bid document price: 500.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Oct 03, 2026)
- Posted at: 2026-10-05T11:15:24.000Z
- Source: Qelal Tenders