Cleaning and Janitorial Equipment and Service

የአማራ ፓይፕ ፋብሪካ ኃላ/የተ/የግል ኩባንያ ባህር ዳር ከተማ የሚገኝ የአማራ ክልል የመንግስት ልማት ድርጅት ሲሆን ፋብሪካው የተለያዩ የፅህፈት መሳሪዎችን እና የተለያዩ የፅዳት ዕቃዎች ግዥ በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር APF/03/2019/Local

የአማራ ፓይፕ ፋብሪካ ኃላ/የተ/የግል ኩባንያ ባህር ዳር ከተማ የሚገኝ የአማራ ክልል የመንግስት ልማት ድርጅት ሲሆን ፋብሪካው ከዚህ በታች በሎት የተገለጹትን፡-

  • ሎት 1- የተለያዩ የፅህፈት መሳሪዎችን እና
  • ሎት 2- የተለያዩ የፅዳት ዕቃዎች ግዥ በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች፡-

1. ለ2018 በጀት ዓመት የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይነት ምዝገባ ሰርቲፊኬት እና የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።

2. ተጫራቾች ከላይ በተ.ቁ 1 ላይ የተገለጸውን ለ2018 በጀት ዓመት የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ ማቅረብ የማይችሉ ከሆኑ ከሚመለከተው ግብር ሰብሳቢ መንግስታዊ ተቋም የ2018 በጀት ዓመት ግብር ያልከፈለበትን ምክንያት ገልፆ እና በዚህ ጨረታ እንዲሳተፍ የሚፈቅድ ደብዳቤ ለፋብሪካው በመጻፍ ደብዳቤውን ከመጫረቻ ሠነዶቻቸው ጋር የማቅረብ ግዴታ አለባቸው።

3. ዝርዝር የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ በፋብሪካው የፋይናንስ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 105 በመቅረብ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል ማግኘት ይችላሉ።

4. ተወዳዳሪ ድርጅቶች ለተወዳደሩበት ሎት/ ዕቃዎች ያቀረቡትን ጠቅላላ ዋጋ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ጨምሮ 2% የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (CPO) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማቅረብ አለባቸው።

5. ተጫራቾች በጨረታው የጊዜ ገደብ ውስጥ የመጫረቻ ሠነዶቻቸውን በፋብሪካው ቢሮ ቁጥር 206 ለዚህ ጉዳይ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።

6. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር በ15ኛው ቀን ቢሮ ቁጥር 206 ከቀኑ 8፡00 ተዘግቶ በዚሁ ዕለት 8፡30 ይከፈታል።

7. 15ኛው ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም የሕዝብ በዓል ቀን ከሆነ የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ቦታ እና ሰዓት ይሆናል።

8. ፋብሪካው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ አማራ ፓይፕ ፋብሪካ ኃላ/የተ/የግል ኩባንያ ቢሮ ቁጥር 206 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 09-35-98-37-29/ 09-18-70-18-26/ 09-11-95-96-04 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።

የአማራ ፓይፕ ፋብሪካ ኃላ/የተ/የግል ኩባንያ

ባህር ዳር


Tender details

  • Deadline: 2026-10-19
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid closing (note): የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር በ15ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00
  • Bid opening: 2026-10-19 14:30
  • Bid opening (note): የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር በ15ኛው ቀን ከቀኑ 8፡30
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: Amhara Pipe Factory PLC
  • Buyer TIN: 0006196550
  • Bid bond: 2%
  • Bid document price: 500.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Oct 04, 2026)
  • Posted at: 2026-10-05T11:44:19.000Z
  • Buyer website: https://amharapipe.et/
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders