Cleaning and Janitorial Equipment and Service

በልደታ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት ስር የሚገኘው የእናት ኢትዮጵያ የመጀ/ደ/ት/ቤት እና ካራማራ ቅድመ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ለ2019 ዓ/ም የተለያዩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ ግዥዎችን መፈጸም ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በልደታ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት ስር የሚገኘው የእናት ኢትዮጵያ የመጀ/ደ/ት/ቤት እና ካራማራ ቅድመ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ለ2019 ዓ/ም በግልጽ ጨረታ ግዥዎችን መፈጸም ይፈልጋል።

  • ሎት 1- የደንብ ልብሶች የጨረታ ማስከበርያ በብር መጠን-------------2,000
  • ሎት 2- አላቂ የቢሮ እቃዎች የጨረታ ማስከበርያ በብር መጠን--------2,000
  • ሎት 3 ህትመት የጨረታ ማስከበርያ በብር መጠን ---------------------1,000
  • ሎት 4 አላቂ የትምህርት እቃዎች የጨረታ ማስከበርያ በብር መጠን ------1,000
  • ሎት 5 ሌሎች አላቂ የፅዳት እቃዎች የጨረታ ማስከበርያ በብር መጠን------1,000
  • ሎት 6 ልዩ ልዩ መሳርያዎች የጨረታ ማስከበርያ በብር መጠን--------------2,000
  • ሎት 7-ፕላንትና ማሽነሪ መግዣየጨረታ ማስከበርያ በብር መጠን---------3,500
  • ሎት 8 ለህንፃና ቁሳቁስ መግዣ ጨረታ ማስከበርያ በብር መጠን-------------1,500
  • ሎት 9 የሰራተኛ የደንብ ልብስ ስፌት እቃዎች -መገዣበብር------------------1,500
  • ሎት 10 አላቂ የህክምና እቃ መገዣ የጨረታ ማስከበርያ በብር መጠን ---------1,000
  • ሎት 11-ህንፃና ቁሳቁስ እድሳትና ጥገና የጨረታ ማስከበሪያ በብር መጠን-------3,500

ለጨረታው የሚያስፈልጉ መስፈርቶች

1. የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያለው የዘመኑን ግብር የከፈለ እና የዕቃ አቅራቢዎች የምዝገባ የምስክር ወረቀትያለው እና የቫት ተመዝጋቢ የሆነ።

2. ተጫራቾች በባንክ የተረጋገጠ (CPO) ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።

3. ተጫራቾች ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት እለት አንስቶ በተከታታይ 10 የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ በእናት ኢትዮጵያ የመጀ/ደ/ት/ቤት ፋይናንስ ግዥና ን/አስ/ደጋፊ የስራ ሂደት በግንባር በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።

4. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስታወቂያው ከወጣበት እለት ጀምሮ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት በት/ቤቱ ግዥ ክፍል ቢሮ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።

5. ጨረታው በ10ኛው ቀን በ11፡30 ሰዓት ታሽጎ በማግስቱ 4፡30 በት/ቤቱ ቤተ መፅሀፍት ይከፈታል። የመክፈቻ ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓትና ቦታ ይከፈታል።

6. ተጫራቾች የጨረታ ሳጥን ከመከፈቱ በፊት ለተወዳደሩባቸው እቃዎች ናሙና (sample) ማቅረብ የሚኖርባቸው ሲሆን የተሟላ ፍላጎት መግለጫ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

7. ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸው እቃዎች ለእያንዳንዱ የሚያቀርቡት ዋጋ ከነቫቱ መሆን አለበት።

8. የዘገየ ጨረታና ስርዝ ድልዝ ያለበት ሰነድ ተቀባይነት የለውም።

9. አማራጭ ጨረታ ተቀባይነት የለውም።

10. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ግዥ ፈፃሚው መስሪያ ቤት ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

11. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

12. ናሙና ማቅረብ የማይቻልባቸው ትልልቅ እቃዎች ፍላጎት መግለጫ (specification) ተያይዞ መቅረብ ይኖርበታል።

13. ናሙናዎች በሙሉ መቅረብ የሚችሉት ለግዢ ክፍል ብቻ በመረካከቢያ ቅፅ ላይ ተሞልቶ መሆን አለበት።

አድራሻችን፤- አብነት በሞላ ማሩ ወደ ጌጃ ቃለ ህይወት በሚወስደው መንገድ ገባ ብለው ያገኙናል።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0112 300 115--------0111 230 120

በልደታ ክ/ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት የእናት ኢትዮጵያ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤትና ካራማራ ቅድመ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-10-15
  • Bid closing time: 17:30
  • Bid closing (note): ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ቆይቶ በ10ኛው ቀን በ11፡30 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-10-16 10:30
  • Bid opening (note): ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ቆይቶ በማግስቱ 4፡30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Enat Ethiopia Kindergarten & Elementary School
  • Buyer address: አብነት ከሞላ ማሩ 50 ሜትር ገባ ብሎ
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Oct 04, 2026)
  • Posted at: 2026-10-05T11:49:48.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders