House and Building Sale
አቢሲንያ ባንክ አ.ማ. መኖሪያ ቤት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
House and Building SaleSales, Disposals and ForeclosureHouse and Building Foreclosure
Addis Ababa
More tags
Description
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
አቢሲንያ ባንክ አ.ማ. ለሰጠው ብድር በዋስትና የያዘውንና በሰንጠረዡ የተመለከተውን ንብረት በአዋጅ ቁጥር 97/1990 እንደተሻሻለው ለባንኮች በተሰጠው ስልጣን መሠረት ንበረቱ በሚገኝበት ቦታና ባለበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
ተጫራቾች ለጨረታው ከመቅረባቸው በፊት የሚከተሉትን ደንቦች መገንዘብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታ መነሻ ዋጋውን 1/4(አንድ አራተኛ) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም ሲ.ፒ.ኦ በአቢሲንያ ባንክ አ.ማ. ስም በማሰራት ለጨረታ ማስከበሪያ በማስያዝ በጨረታው ለመሳተፍ ይችላሉ።
- የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ ከባንኩ በደብዳቤ ከተገለፀለት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ15 (አስራ አምስት) ቀናት ውስጥ አጠቃሎ ከፍሎ በጨረታ ያሸነፈበትን ንብረት መረከብ ይኖርበታል። በእነዚህ ቀናት ውስጥ አጠቃሎ ካልከፈለ ጨረታው ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል። በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ቼክ ወይም ሲ.ፒ.ኦ. ይመለስላቸዋል።
- ተበዳሪው/መያዣ ሰጪው በሐራጁ ቀንና ሰዓት ጨረታ በሚካሄድበት ቦታ መገኘት ይችላሉ፡፡ነገር ግን ባይገኙ ሐራጁ በሌሉበት ይካሄዳል።
- የጨረታው አሸናፊ ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ማናቸውም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎችን፣እንዲሁም ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ማናቸውም ወጪዎችን ገዥ ይከፍላል።ውዝፍ የሊዝ ክፍያ ካለ ባንኩ የሚከፍል ሲሆን ቀሪ የሊዝ ክፍያ እዳ ደግሞ ወደ አሸናፊው/ገዥው የሚተላለፍ ይሆናል።
- የጨረታው አሸናፊ ንብረቱ በሚገኝበት የከተማ አስተዳደር ዘንድ ቀርቦ ባሸነፈበት ንብረት ላይ የሚከፈሉ ክፍያዎችን፣ ግብርና ታክስ ይከፍላል።
- የጨረታው አሸናፊ ለመንግስት የሚከፈለውን 15% (አስራ አምስት በመቶ) የተጨማሪ እሴት ታክስ ለመንግስት የሚከፍለው ጉዳዩ የሚመለከተው የመንግስት አካል መከፈል አለበት ካለ ብቻ ነው።
- በባንኩ የብድር ፖሊሲና መመሪያ መሠረት መስፈርቱን ለሚያሟሉ የጨረታው ከፍተኛ ዋጋ አቅራቢዎች ባንኩ ከፊል ብድር ሊሰጥ ይችላል።
- ንብረቱን በሥራ ሰዓት ፕሮግራም አስይዞ ለመጎብኘት ወይም ለማየት የሚቻል ሲሆን፣
- ጨረታው የሚካሄደው ሞጆ ከተማ አቢሲንያ ባንክ ሞጆ ቅርንጫፍ ውስጥ ነው።
- ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥሮች 022-212-1696 እና በ022-212-0730 አዳማ በመደወል መጠየቅ ይቻላል።
|
ተ.ቁ |
የተበዳሪው ስም |
ከተበዳሪው የሚፈለግበት ቀሪ ዕዳ |
የመያዣ ሰጪው ስም |
ንብረቱ የሚገኝበት አድራሻ |
የጨረታ መነሻ ዋጋ ብር |
ጨረታው የሚካሄድበት ቀንና ዓ.ም. |
የምዝገባ ሰዓት |
የጨረታ ሰዓት |
ጨረታው የሚካሄድበት ቦታ |
የንብረቱ አገልግሎት |
የቦታው ስፋት (በካ.ሜ) |
የባለቤትነት ማረጋገጫ ካርታ ቁጥር |
|
1 |
አቶ ተስፋሚካኤል አድነው ገብሬ |
እስከ መስከረም 14 ቀን 2019 ዓ.ም ድረስ ብር 1,339,134.70 |
አቶ ተስፋሚካል አድነው ገብሬ |
ሞጆ ከተማ፣ መልካ ለሚ (02) ቀበሌ |
1,516,910.86 |
ጥቅምት 26 2019 ዓ.ም |
4፡00-4፡30 |
4፡30-5፡30 |
አቢሲንያ ባንክ ሞጆ ቅርንጫፍ ውስጥ |
መኖሪያ ቤት |
201.022 |
OR021024413005 |
ጨረታው ከመካሄዱ በፊትም ሆነ ከተካሄደ በኋላ ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ወይም ብድሩ ከተከፈለ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብት አለው።
Tender details
- Deadline: 2026-11-05
- Bid closing time: 11:30
- Bid opening: 2026-11-05 11:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Bank of Abyssinia S.C.
- Buyer address: Addis Ababa Ethiopia
- Bid bond: 25%
- Published on: Reporter (Oct 04, 2026)
- Posted at: 2026-10-05T11:54:32.000Z
- Source: Qelal Tenders