Wood and Wood Working

ፀደይ ባንክ አ.ማ. የካውንተር ስራ ለአንድ አመት ቋሚ ውል በመያዝ ለማሰራት ግዥ ለመፈፀም ፈቃድ ያላቸውን ተጫራቾች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር ብ/ግ/ጨ/004/2019

ፀደይ ባንክ አ.ማ የካውንተር ስራ ለአንድ አመት ቋሚ ውል በመያዝ ለማሰራት ግዥ ለመፈፀም ፈቃድ ያላቸውን ተጫራቾች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።

ስለሆነም ከዚህ በታች የቀረበውን መስፈርት የሚያሟላ ማንኛውም በዘርፉ የተሰማራ ድርጅት/ነጋዴ/ መወዳደር የሚችል መሆኑን እንገልጻለን።

1. የ2018 ዓ.ም የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምስክር ወረቀት፣ የግብር መክፈያ ሰርቲፊኬት፣ የታክስ ክሊራንስና የብቃት ማረጋገጫ ሊኖራቸዉ ይገባል። ቴክኒካል ዶክሜንትና የሚያቀርቡበትን ዋጋ በጨረታ ዶክሜንቱ መሰረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

2. ለጨረታ ማስከበሪያ የአጠቃላይ ዋጋውን 2% ወይም የአጠቃላይ ዋጋው 2% ከብር 500,000.00 የሚበልጥ ከሆነ ብር 500,000.00 በሲፒኦ /CPO/ ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ የ90 ቀን በፀደይ ባንክ አማ ስም ማሰራት ይኖርባቸዋል። ከየትኛውም የፀደይ ባንክ አማ ቅርንጫፍ የተሰጠ ሲፒኦም ሆነ ባንክ ጋራንቲ ተቀባይነት የለውም።

3. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከመስከረም 25 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት የስራ ቀኖች ማለትም ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2:00 ሰዓት እስከ 6:00 ሰዓት እና ከሰዓት በኋላ ከ7:00 ሰዓት እስከ ምሽቱ 11:00 ሰዓት እንዲሁም ቅዳሜ ከጠዋቱ 2:00 ሰዓት እስከ 6:00 ሰዓት የማይመለስ አምስት መቶ ብር /500.00/ ፀደይ ባንክ ለገሃር ቅርንጫፍ ወይም በማንኛውም የፀደይ ባንክ ቅርንጫፍ በመክፈል ሰንጋተራ አካባቢ በሚገኘው የባንኩ ዋና መ/ቤት 16ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 09 ከግዥ ክፍል ሰነዱን መዉሰድ ይችላሉ።

4. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የጨረታ ሰነድ በሰም በታሸገ ፖስታ እስከ ጥቅምት 10 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ አዲስ አበባ ሰንጋተራ አካባቢ በሚገኘው ፀደይ ባንክ ዋና መ/ቤት 16ተኛ ፎቅ ግዥና ዉል አስተዳደር ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው በዚሁ ዕለት በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመስሪያ ቤቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል።

5. የጨረታዉ መዝጊያ ሰዓት ካለፈ በኋላ የሚመጣ ማንኛዉም የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረዉም።

6. ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ ፡- አዲስ አበባ ሰንጋተራ አካባቢ ጤና ሚኒስቴር ዝቅ ብሎ በሚገኘው የፀደይ ባንክ ዋና መ/ቤት

ስልክ ቁጥር 011 558 1658

ፀደይ ባንክ አ.ማ


Tender details

  • Deadline: 2026-10-20
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-10-20 10:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Tsedey Bank S.C.
  • Buyer address: Legahar Orda Building, 8th Floor room No-804
  • Bid bond: 2% ወይም የአጠቃላይ ዋጋው 2% ከብር 500,000.00 የሚበልጥ ከሆነ ብር 500,000.00
  • Bid document price: 500.00 ብር
  • Published on: Reporter (Oct 04, 2026)
  • Posted at: 2026-10-05T12:57:05.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders