House and Building Sale
ብርሃን ባንክ አ.ማ. መኖሪያ ቤት ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
More tags
Description
የሐራጅ ማስታወቂያ
ብርሃን ባንክ አ.ማ ከባለእዳዎቹ ላይ ለሚፈልገው ገንዘብ በዋስትና የያዛቸውን እና ከዚህ በታች የተመለከቱትን ንብረትቶች በአዋጅ ቁጥር 97/1990 እና በተሻሻለው አዋጅ ቁጥር 216/92 ለባንኮች በተሰጠው ስልጣን መሠረት ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
- ተጫራቾች ለጨረታ ከመቅረባቸው በፊት የሚከተሉትን ደንቦች በመገንዘብ ማክበር ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታ መነሻ ዋጋውን የ1/4 (አንድ አራተኛ) (ሲፒኦ) በብርሃን ባንክ ኢማ ስም ለጨረታ ማስከበሪያ በማስያዝ በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።
- የጨረታው አሸናፊ ጨረታውን እንዳሸነፈ ከተገለፀለት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ15 (አስራ አምስት) ቀናት ውስጥ አጠቃሎ ከፍሎ ንብረቱን መረከብ አለበት:: በእነዚህ ቀናት ውስጥ አጠቃሎ ካልከፈለ ጨረታው ተሰርዞ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል:: በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ሲፒኦ ይመለስላቸዋል።
- የመኖሪያ፣ ንግድ እና መጋዘን ቤቶቹ ጨረታ ንብረቱ በሚገኝበት ቦታ ይከናወናል።
- የጨረታ አሸናፊው በሚገዛው ንብረት ላይ የሚፈለግ ማናቸውም ለመንግስት የሚከፈሉ ግብር፣ ተጨማሪ እሴት ታክስ፣ የስም ማዛወሪያ ክፍያዎች እና የሊዝ ክፍያዎች ይመለከተዋል።
- መያዣ ሰጪዎች ሐራጁ በሚከናወንበት ቦታ ቀንና ሰዓት መገኘት ይችላሉ:: ባይገኙ ግን ሐራጁ በሌሉበት ይካሄዳል።
- በባንኩ ብድር መምሪያ መስፈርት መሰረት እና በተሰጠው ጊዜ ውስጥ የሚፈለግበትን ለሚያሟላ ተጫራች ባንኩ በከፊል ብድር ሊያመቻች ይችላል።
- ለጨረታ የቀረቡትን ንብረቶች በስራ ሰዓት ኘሮግራም አስይዞ ለመጐብኘት ይቻላል።
- ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብት አለው።
1. የመኖሪያ ቤት
|
ተቁ |
የተበዳሪዉ ስም |
የመያዣ ሰጭዉ ስም |
መኖሪያ/ የንግድ ቤት የሚገኝበት አድራሻ |
የቦታው ስፋት በካሬ ሜትር |
የንብረቱ አገልግሎት
|
የባለቤትነት ማረጋገጫ ካርታ ቁጥር |
የጨረታ መነሻ ዋጋ
|
ጨረታዉ የሚካሄድበት ቀን እና ሰዓት፤ |
|
1 |
ጀነራል ፓወር ኃ/ የተ/የግ/ማህበር |
መውደድ ፀጋዬ
|
አአ ከተማ ን/ስ/ላፍቶ ክ/ከተማ ወረዳ 08 |
347 ካሜ
|
መኖሪያ ቤት
|
37724/21915/01
|
21,000,000.00
|
ጥቅምት 23 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00-5፡30 |
|
2 |
አስቻለው የኔጌት |
ቦጋለች የኔሰው |
እንጅባራ ከተማ 02 ቀበሌ |
200 ካ.ሜ
|
መኖሪያ ቤት
|
1574/09
|
2,500,000.00
|
ጥቅምት 24 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00-5፡30 |
|
3 |
ህሩይ አምደወርቅ |
ሙሉጎጃም አይነታው |
እንጅባራ ከተማ 05 ቀበሌ |
200 ካ.ሜ
|
መኖሪያ ቤት
|
082/2014
|
2,000,000.00
|
ጥቅምት 24 ቀን 2019 ዓም ከቀኑ 8፡00-9፡30 |
ተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥሮች 011-6506900 እና 011-6506276 በመደወል መጠየቅ ይቻላል።
Tender details
- Deadline: 2026-11-03
- Bid closing time: 15:30
- Bid closing (note): የሐራጁ መዝጊያ ቀንና ሰዓት የተለያየ ነው
- Bid opening: 2026-11-03 15:30
- Bid opening (note): የሐራጁ መክፈቻ ቀንና ሰዓት የተለያየ ነው
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Berhan Bank S.C.
- Bid bond: 25%
- Published on: Reporter (Oct 04, 2026)
- Posted at: 2026-10-05T12:59:14.000Z
- Source: Qelal Tenders