Stationery
የመከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን የጽሕፈት መሣሪያ፣ የጽዳት እቃዎች፣ የሠራተኛ ደንብ ልብስ እና የተሽከርካሪ ጎማና ባትሪ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር መ.ሠ.ፋ/ብ.ግ.ጨ-002/2019
የመከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን በስሩ ለሚገኙት ክፍሎች ከዚህ በታች በሎት የተገለፁትን ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
- Lote 1 የጽሕፈት መሣሪያ
- Lote 2 የጽዳት እቃዎች
- Lote 3 የሠራተኛ ደንብ ልብስ
- Lote 4 የተሽከርካሪ ጎማና ባትሪ
በዚህም መሠረት ተጫራቾች ከዚህ በታች የተገለፁትን መስፈርቶች በማሟላት በጨረታው የምትሳተፉ መሆኑን እንገልፃለን።
1. ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ/ VAT Registration Certificate/፤ በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የተመዘገቡ እና የቲን ሰርተፊኬት፣ የብቃት ሰርተፊኬት፣ tax clearance certificate፣ የመንግስት የግዥ እና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ሰርተፊኬት ማቅረብ አለባቸው።
2 ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር በየሎቱ 500/ አምስት መቶ/ ብር በመክፈል መሠ.ፋ ግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 015 ድረስ በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ።
3. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ማለትም
- ሎት 1 ብር 50,000 /ሃምሳ ሺህ ብር/
- ሎት2 ብር 50,000 /ሃምሳ ሺህ ብር/
- ሎት3 ብር 50,000 / ሃምሳ ሺህ ብር/
- ሎት4 ብር 50,000 / ሃምሳ ሺህ ብር/
በባንክ በተመሰከረለት /ሲ.ፒ.ኦ/ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረት ባንክ ጋራንቲ ብቻ በመከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን ስም ከጨረታው ኦርጅናል ቴክኒካል ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
4. ተጫራቾች ለሚጫረቱባቸው ፋይናንሺያል እና ቴክኒካል ሰነዶቻቸውን ኦሪጂናል እና አንድ አንድ ኮፒ ለየብቻ ለይቶ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ቢሮ ቁጥር 015 በመምጣት መሥሪያ ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ እንዲሁም ተያያዥ ዶክመንቶች ማቅረብ አለባቸው።
5. ይህ ጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ውሎ በ16ኛው ቀን ልክ 8፡00 ሰዓት ላይ የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከቀኑ 8፡30 መ.ሠ.ፋ ግዥ ክፍል ይከፈታል።
6. የጨረታ አሸናፊዎች ማሸነፋቸው በጽሁፍ የሚገለጽላቸው እና የውል ስምምነት የሚፈፅሙ ይሆናል።
7. በጨረታ ያላሸነፉ ድርጅቶች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል።
8. ፋውንዴሽኑ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ፡-
አድራሻ፡- አዲስ አበባ ከሜክሲኮ ወደ ቄራ በሚወስዳው ላንድ ማርክ ሆስፒታል አጠገብ
ስልክ ቁጥር፡-011 557 2752 / 09 10 99 38 14
የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን
Tender details
- Deadline: 2026-10-20
- Bid closing time: 14:00
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ልክ 8፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-10-20 14:30
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ልክ 8፡30 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Defense Forces Foundation
- Buyer address: ከቄራ ወደ ሜክሰኮ በሚወስደው መንገድ ላንድማርክ ሆስፒታል ጎን
- Bid bond: በየሎቱ 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር)
- Bid document price: በየሎቱ 500.00 (አምስት መቶ ብር)
- Published on: Addis Zemen (Oct 05, 2026)
- Posted at: 2026-10-06T07:26:20.000Z
- Source: Qelal Tenders