Equipment and Accessories

የደሴ ዙሪያ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለደሴ ዙሪያ ወረዳ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል ኤሌክትሮኒክስ፣ የቋሚ ዕቃ፣ ሞተር ሳይክል፣ የህክምና መሳሪያ፣ የመኪና ጎማ፣ የእንስሳት መድሃኒት እና የህክምና መሳሪያዎች መግዛት ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የደሴ ዙሪያ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለደሴ ዙሪያ ወረዳ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል

  • ሎት 1 የኤሌክትሮኒክስ
  • ሎት 2. የቋሚ ዕቃ
  • ሎት 3. ሞተር ሳይክል
  • ሎት 4. የህክምና መሳሪያ
  • ሎት 5 የመኪና ጎማ
  • ሎት 6 የእንስሳት መድሃኒት እና የህክምና መሳሪያዎች

ከተራ ቁጥር 1-6 የተዘረዘሩትን በአድስ ዘመን ጋዜጣ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በዚህ መሠረት፡-

  1. በዘርፉ ህጋዊ ፈቃድ ማቅረብ የሚችል
  2. በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ቲን ነበር ያላቸው
  4. የግዥ መጠኑ 500,000.00 /አምስት መቶ ሺህ ብር/ እና ከዚያ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
  5. የተጨማሪ እሴት ታክስ ወይም ቫት ከፋይ መሆን አለባቸው።
  6. የዘመኑን ግብር የከፈሉመሆን አለባቸው።
  7. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከተራቁጥር 1 እስከ 6 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከጨረታው ሰነድ ጋር አይይዘው ማቅረብ አለባቸው።
  8. የጨረታው ሰነድ ከደሴ ዙ/ወ/ገንዘብ ጽ/ቤት በመገኛት የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) ለእያንዳንዱ ሰነድ በመክፈል መግዛት ይኖርባቸዋል።
  9. ጨረታው ከ24/1/2019 ዓ.ም እስከ 03/2/2019 ዓ.ም በአየር ላይ ይውላል።
  10. ጨረታው በ04/2/2019 ዓ.ም 3፡30 ታሽጎ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል።
  11. ተጫራቾች ኦርጅናል እቃ መሙላትና ያሸነፉበትን እቃ በባለሙያ ማስፈተሸ አለባቸው።
  12. የሚገዙ እቃዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፍኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል።
  13. ማንኛውም ተጫራች በሰነዱ ላይ ሲሞሉ በሎት ስለሆነ ሙሉ በሙሉ መሙላትና ለእያንዳንዱ የእቃ ዋጋ ላይ ቫትን ጨምሮ መሙላት አለባቸው።
  14. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚያቀርቡት ዕቃ ዋጋ 2% በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው።
  15. አሸናፊው ተጫራች የሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ የሚያሲዝ ይሆናል።
  16. አሸናፊ ተጫራች ያሸነፉባቸውን ዕቃዎች በራሱ ወጪ በየሴክተሩ ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት።
  17. ተጫራቾች የተሰጣቸውን የጨረታ ሰነድ በአግባቡ መሙላት አለባቸው።
  18. የተጫራቾች መመሪያ በተመለከተ መመሪያው ብዙ ስለሆነ በሶፍት ኮፒ ከደ/ዙ/ወ/ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥ ቢሮ መውሰድ አለባችሁ
  19. በጨረታው ላይ የሚሳተፉ ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋና ቅጅ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በማሸግ እስከ 04/2/2019 ዓ.ም ደሴ/ዙ/ወ/ግዥ ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ 3፡30 ሰዓት ድረስ  እንድያስገቡ እየገለፅን ጨረታው የሚከፈተው በዚሁ እለት ከቀኑ 4፡00 ሰዓት መሆኑን እናሳውቃለን።
  20. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ደሴ/ዙ/ወ/ግዥ ቢሮ ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 033-111-7763 ወይም 033 312 1787 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
  21. መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ስልክ ቁጥር 033 111 7763 / 033 312 1787 ይደውሉ።
የደሴ ዙሪያ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

 


Tender details

  • Deadline: 2026-10-14
  • Bid closing time: 09:30
  • Bid opening: 2026-10-14 10:00
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: Dessie Locality Woreda Finance and Economic Development Bureau
  • Bid bond: 2%
  • Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Oct 05, 2026)
  • Posted at: 2026-10-06T08:03:34.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders