Stationery
በቤንች ሸኮ ዞን የሰ/ቤ/ወ/ፋ/ጽ/ቤት በ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት በወረዳው ውስጥ ለሚገኙ የመንግስት ሴ/ር/መ/ቤቶች ለተለያዩ ስራ አገ/ት የሚውሉ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
- ሎት 1 የጽህፈት መሣሪያ
- ሎት 2 የመኪና መለዋወጫ
- ሎት 3 የመኪና ጥገና የእጅ ዋጋ
- ሎት 4 የሞተር ሳይክል ተሽከርካሪ
- ሎት 5 የቆዳ ውጤቶች
በቤንች ሸኮ ዞን የሰ/ቤ/ወ/ፋ/ጽ/ቤት በ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት በወረዳው ውስጥ ለሚገኙ የመንግስት ሴ/ር/መ/ቤቶች ለተለያዩ ስራ አገ/ት የሚውሉ ከዚህ በላይ በሎት የተዘረዘሩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል። ስለዚህ ማንኛውም ህጋዊ ተጫራች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን የጨረታ መስፈርቶችን የሚያሟሉ መወዳደር እንዲችሉ ይጋብዛል።
1. ተጫራቾች ለማቅረብ የሚያስችል በዘርፉ የታደሰ የ2019 ዓ.ም የንግድ ፍቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉበት ማስረጃ ማቅረብ የሚችልና የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ያለው መሆን አለበት።
2. ተጫራቾች ተጨማሪ እሴት ታክስ ቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ቲን ነምበር ያለው መሆን አለበት።
3. ተጫራቾች የምዝገባ ሰርተፊኬት ፎቶ ኮፒና የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለበት።
4. ተጫራቾች ሎት ለጽ/መሣሪያ፤ ሎት 2 የመኪና መለዋወጫ፣ ሎት 3 የመኪና ጥገና የእጅ ዋጋ እና ሎት 4 የሞተር ሳይክል ተሸከርካሪ የጨረታ ዓይነት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ CPO ብር 10,000 (አስር ሺህ ብር) ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
5. ለቆዳ ውጤቶች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ CPO ብር 5000 (አምስት ሺህ ብር) ለየብቻው በፖስታ በማሸግ ከጀርባው ለየትኛው የጨረታ ዓይነት እንደተወዳደሩ በመጥቀስ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ወይም ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማቅረብ አለበት።
6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ /1/ ዋና ኦርጅናል እና ሁለት ኮፒ/2/ በተለያዩ (3) ፖስታዎች በማሸግ ከጀርባው ዋናውንና ኮፒውን የሚገልጽ ጽሁፍ በመፃፍ ድርጅቱ ባለበት አድራሻ ህጋዊ ማህተም በማሳረፍና የስልክ ቁጥራቸውን በመፃፍ ለዚህ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
7. በሰ/ቤ/ወ/ገቢዎች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የጨረታ ሰነድ ክፍያውን የማይመለስ 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ህጋዊ ደረሰኝ በመያዝ የጨረታ ሰነዱን ከሰ/ቤ/ወ/ፋ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 4 በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።
8. ጨረታው በማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለ15 የመንግስት የስራ ቀናት በአየር ላይ ውሎ በ15ኛው ቀን ልክ 11፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በ16ኛው ቀን ልክ 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ዕለቱ በዓል ከሆነ ወይም የመንግስት ስራ ቀን ካልሆነ በቀጣይ የስራ ቀን ይከፈታል።
9. ተጫራቾች ማህበራት ከሆኑ የተደራጁበትን ህጋዊ ሰውነት የሚገልፅ መረጃ የሚያቀርቡ ይበረታታሉ።
10. ማንኛውም ተጫራች ያሸነፈበት የዕቃ ዓይነት በደብዳቤ ከተገለፀበት በ7 ቀናት ውስጥ ጥራቱን የጠበቀ ዕቃ በጨረታ ሰነድ መሰረት ብቻ ለማቅረብ ሙሉ ፍቃደኛ ሆኖ ውል የሚገባ መሆን አለበት እንዲሁም ለቅድመ ክፊያ 30% ዋስትና ለማስያዝ ፍቃደኛ መሆን አለባቸው።
11. አሸናፊ ድርጅት ውል በገባበት በ7 ቀናት ልዩነት ውስጥ ብቻ ያሸነፈባቸው የዕቃ ዓይነት ሙሉ በሙሉ ለማቅረብ ፍቃደኛ መሆን አለባቸው። ለዚህ አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈበት ከጠቅላላ ዋጋ የውል ማስከበሪያ ሰነድ 10% በማስያዝ በአሸነፈበት በ15 ቀን ውል ባይገባ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ብር ለመንግስት ውርስ ሆኖ በገዛ ፍቃዱ እንደተወው ይቆጠራል።
12. ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያ በሚታይ ፅሁፍ ማቅረብ አለባቸው። እንዲሁም ሌሎች ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ማቅረብ የተከለከለ ሲሆን በዋጋ ማቅረቢያ ላይ ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም።
13. በጨረታ መክፈቻ ዕለት ተወዳደሪዎች ወይም ተጫራቾች ያለመገኘት የጨረታ አከፋፈትን ሊያስተጓጉል አይችልም።
14. አሸናፊ ድርጅት የመጓጓዣ ወጪ ወይም የመኪና ትራንስፓርት ሙሉ በሙሉ በመሸፈን እስከ ሰ/ቤ/ወ/ፋ/ኢ/ቤት ድረስ አጓጉዞ ለማቅረብ፤ ለማስረከብ ፍቃደኛ መሆን አለባቸው።
15. ማሳሰቢያ፡- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ይሁን ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 09 46 52 19 85/ 09 35 17 08 95 ይደውሉ።
የደ/ም/ኢት/ህ/ክ መንግስት በቤንች ሽኮ ዞን የሰ/ቤ/ወ/ፋ/ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-10-19
- Bid closing time: 17:00
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን ልክ 11፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-10-20 10:30
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ልክ 4፡30 ሰዓት
- Region: South West Ethiopia Region
- Publishing entity: North Bench Woreda Finance and Economic Development Bureau
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Oct 05, 2026)
- Posted at: 2026-10-06T09:31:52.000Z
- Source: Qelal Tenders