Textile, Garment and Leather
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የሚሊኒየም አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ለ2019 ዓ.ም ለመሥሪያ ቤቱ ሥራ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ዕቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
More tags
Description
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 01/2019
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የሚሊኒየም አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ለ2019 ዓ.ም ለመሥሪያ ቤቱ ሥራ አገልግሎት የሚውሉ፡- ሎት1. የደንብ ልብስ ፤ ሎት2. የትምህርት አላቂ ዕቃዎች ፤ ሎት 3. የፅዳት ዕቃዎች፤ ሎት4 ቋሚ ዕቃ ፣ ሎት5. የስፖርት ዕቃዎች ፣ ሎት6. ልዩ ልዩ ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በመሆኑም በዚህ መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩት መስፈርቶች የምታሟሉ በዘርፉ የተሰማራችሁ ሕጋዊ ነጋዴዎችን በጨረታ አወዳድረን በጥራት እና በዋጋ በማወዳደር አሸናፊ ከሆኑት ድርጅቶች ለመግዛት የምንፈልግ መሆኑን እያሳወቅን።
- ተጫራቾች የ2019 ዓ.ም የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው።
- የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) የተሰጠው።
- ወቅታዊ የ2018 ዓ.ም የግብር ግዴታቸውን የተወጡና በጨረታው መሣተፍ የሚችሉ መሆኑን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- በኢፌዴሪ የመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ በአቅራቢነት ሊስት (Supplier List) ውስጥ የተመዘገቡ።
- በጨረታ መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን የሚገልጽ የጨረታ ተሳትፎ ከገቢዎችና ጉምሩክ ጽ/ቤት ቀኑ ያላለፈበት ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
1. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 /አስር/ ተከታታይ የሥራ ቀናት የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል የሚሊኒየም አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ፋይናንስ ክፍል ከጠዋቱ 2:30-11:30 ሰዓት ድረስ መግዛት የሚችሉ መሆኑን እየገለጽን ተጫራቾች በገዙት የጨረታ ሰነድ በእያንዳንዱ ገጽ ላይ ሕጋዊ የድርጅት ማህተምና ፊርማ ማደረግ ይኖርባቸዋል።
2. ተጫራቾች የተጠቀሱትን ዕቃዎች በሙሉ ወይም በከፊል መጫረት ይችላሉ።
3. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በጨረታ ሰነድ ውስጥ በሚገኘው የዕቃዎች ዝርዝር ላይ የእያንዳንዱን ዋጋ በመሙላት በ2 በታሸገ ኤንቨሎፕ ሰነዱን አሽገው ዋናውን እና ኮፒውን ለያይተው ጨረታው እስከሚያበቃበት 10ኛው ቀን እስከ 11፡30 ሰዓት ድረስ ብቻ ማስገባት ይችላሉ። ጨረታው በ11ኛው የሥራ ቀን ከዋለ ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ 3:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። (ተጫራቾች ባይገኙም ጨረታውን ከመከፈት አያስተጓጉለውም)።
4. ተጫራቾች በሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሰነድ ላይ የሚያቀርቡት የዕቃ አይነት ዋጋ ስርዝ ድልዝ የሌለበት ሥልጣን ባለው አካል የተፈረመባቸው የተሟላ አድራሻቸውን የሚገልጽና ሕጋዊ ማህተም ያረፈበት ሊሆን ይገባል።
5. ተጫራቾች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ባቀረቡት ዋጋ ላይ የዋጋ ለውጥም ሆነ ማሻሻያ ማድረግ አይቻልም።
6. አሸናፊ ተጫራች አሸናፊነቱ ከተገለጸለት 7 ተከታታይ የሥራ ቀናት ቅሬታ ተጠብቆ ከ8-15 ቀን ውስጥ በተወዳደሩበት ዋጋ እና በቴክኒክ አሸናፊነታቸው ከተገለጸላቸው በኋላ ቀርቦ የውል ማስከበርያ 10% /አስር ፐርሰንት CPO/ ለግዢ ፈጻሚ አካል ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
7. በጨረታው ያሸነፈ ተጫራች ለአሸነፋቸው ዕቃዎች ውል ከተዋዋሉበት ቀን ጀምሮ በአስር የሥራ ቀናት ውስጥ በራሳቸው ትራንስፖርት የማስጫኛና ማውረጃ ወጪ በመክፈል በሚሊኒየም አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ንብረት ክፍል ገቢ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።
8. አንድ ተጫራች ሌላው በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም፡፡ ት/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
9. ተጫራቾች በጨረታ ለቀረቡት ዕቃዎች ሳምፕል ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
10. ከጥቃቅንና አነስተኛ ተደራጅታችሁ የዋስትና ደብዳቤ ለምታመጡ ድርጅቶች በምትወዳደሩበት ዘርፍ የራሳችሁ ምርት (አምራች) መሆናችሁን የሚገልፅ መረጃ በማቅረብ በአመረታችሁት ዕቃ ላይ ብቻ የምትወዳደሩ መሆኑን እናሳውቃለን።
11. ት/ቤቱ አሸናፊ ተጫራች ከመረጠ በኋላ በሚገዙት ዕቃዎች ብዛት እና መጠን ላይ እንደ አስፈላጊነቱ እስከ 20% /ሃያ ፕርሰንት/ የመጨመር ወይም የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው።
12. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ሎት የተጠቀሰውን ብር በመመሪያው መሰረት ከታወቀ ባንክ የጨረታ ማስከበሪያ በCPO በት/ቤቱ ስም በማሠራት ከጨረታው መክፈቻ ቀን እና ሰዓት በፊት በቅድሚያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
|
ተ.ቁ |
የግዥ አይነት |
ሎት |
የጨረታ ማስከበሪያ |
0.5-2% |
|
1 |
የደንብ ልብስ |
1 |
22,000 |
1% |
|
2 |
የትምህርትና የቢሮ አላቂ ዕቃዎች |
2 |
20,000 |
1% |
|
3 |
የፅዳት ዕቃዎች |
3 |
15,000 |
2% |
|
4 |
ቋሚ ዕቃ |
4 |
22,000 |
1.7% |
|
5 |
የስፖርት ዕቃዎች |
5 |
7,000 |
1.5% |
|
6 |
ልዩ ልዩ ዕቃዎች |
6 |
8,000 |
1% |
አድራሻ፦
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የሚሊኒየም አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት
አጠና ተራ ድልድይ ስር ወደ ፍሊጶስ በሚወስደው መንገድ 20 ሜትር ገባ ብሎ
ስልክ፡- 011-280-42-34/35
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የሚሊኒየም አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-10-16
- Bid closing time: 09:00
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው የሥራ ቀን ከዋለ ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-10-16 09:30
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው የሥራ ቀን ከዋለ ከጠዋቱ 3:30 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Millennium Secondary School
- Buyer address: የካ ክ/ከተማ ወደ ኮተቤ በሚወስደው መንገድ በተለምዶ 02 ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ወደ ህዝብ ደህንነት በሚያወጣው አስፓልት ከፍ ብሎ ወረዳ 10 አጠገብ ሚሊንየም አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት፡፡
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 300.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Oct 06, 2026)
- Posted at: 2026-10-06T10:37:07.000Z
- Source: Qelal Tenders