Textile, Garments and Uniforms

በምስራቅ ወለጋ ዞን የኤበንቱ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ደንብ ልብስ፣ አላቂ የፅህፈት እና የጽዳት መሳሪያዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ የፈርኒቸር ዕቃዎች፣ የመኪና መለዋወጫ ዕቃዎችና ጎማዎች፣ የመኪና ጥገና፣ የግንባታ መሳሪያዎች፣ የእጽዋት ዘር እና የእንስሳት ሕክምና መሳሪያዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ ግልጽ የጨረታ  ማስታወቂያ

በምስራቅ ወለጋ ዞን የኤበንቱ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት ለወረዳው ባለ በጀት መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውል

  • ደንብ ልብስ፣
  • አላቂ የፅህፈት እና
  • የጽዳት መሳሪያዎች፣
  • የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣
  • የፈርኒቸር ዕቃዎች፣
  • የመኪና መለዋወጫ ዕቃዎችና ጎማዎች፣
  • የመኪና ጥገና፣
  • የግንባታ መሳሪያዎች፣
  • የእጽዋት ዘር እና የእንስሳት ሕክምና መሳሪያዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በዚህ ጨረታ መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው ማስረጃ

  1. በዘርፉ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና ፍቃዱንም በዘመኑ የታደሰ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
  2. በቀረበው ዝርዝር ስፔስፊኬሽን መሰረት ማቅረብ የሚችሉ።
  3. የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ወይም /TOT/ ምዝገባ ሰርተፊኬት እና ግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር /TIN/ ማቅረብ የሚችሉ።
  4. የአቅራቢነት ምዝገባ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
  5. ግብር የከፈሉ መሆናቸውን ከገቢዎች ባለስልጣን ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ።
  6. ያሸነፉበትን ዕቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ኤበንቱ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ንብረት ክፍል አሸናፊነቱ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ10ተከታታይ የስራ ቀናት ወሰጥ ገቢ ማድረግ የሚችሉ።
  7. ጥራታችውን የጠበቁ ዕቃዎችን ማቅረብ የሚችሉና ጥራት የሌላቸውን ዕቃዎችን መቀየር የሚችሉ።
  8. ለጨረታ ማስከበሪያ በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ የተመሰከረለት የክፍያ ትዕዛዝ /CPO/ በአንዱ ዘርፍ 5000.00 /አምስት ሺህ ብር/ ማስያዝ የሚችሉ፣ በጥቃቅንና አነስተኛ እንተርፕራይዝ አዋጅ መሰረት የተደራጁ ከሆነ ደግሞ ካደራጄው አካል የዋስትና ደብዳቤማቅረብ የሚችሉ።
  9. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00/ አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ከኤበንቱ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 6 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
  10. ማንኛውም ተጫራች ከመ/ቤቱ የገዛውን የጨረታ ሰነድ ላይ የእያንዳንዱን ዕቃ ዋጋ ላይ የተጨማሪ እሴት ታክስ(VAT) ወይም ቲኦቲ(TOT) ጨምሮ በመሙላት ዶክሜንቱን ፈርሞና ማህተም አድርጎ ምንም ሳያጓድል ዋናውን እና ኮፒውን በተለያዩ ፖስታ በማሸግበመጨረሻም ሁለቱን ፖስታ በአንድ ትልቅ ፖስታ በማሸግ በተዘጋጀለት የጨረታ ሰነድ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለበት።
  11. የጨረታው ሰነድ በ15ኛው ቀን በ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 1 በግልጽ ይከፈታል። የተጫራቾች አለመገኘት የጨረታውን መከፈት አያግደውም (በሌሉበት ይከፈታል)።
  12. ክፍያ የሚፈጸመው የታዘዘውን ዕቃ በሙሉ ገቢ ሲያደርግ ነው።
  13. መስሪያ ቤቱ ዕቃዎችን 20% ይጨምራል ወይም ይቀንሳል።
  14. መ/ቤቱ ከነቀምቴ ከተማ 138 ኪ.ሜ ከአዲስ አበባ 466ኪ.ሜ ርቀት ላይ ይገኛል
  15. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው

ለበለጠ ማብራሪያ ኤበንቱ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር  09 10 82 56 36/ 09 17 24 44 48 ደውሎ ማነጋገር ይቻላል

በምስራቅ ወለጋ ዞን የኤበንቱ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-10-19
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን በ 8፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-10-19 14:30
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን በ 8፡30 ሰዓት
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: ኤበንቱ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
  • Bid bond: 5000.00 ብር
  • Bid document price: 500.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Oct 05, 2026)
  • Posted at: 2026-10-06T10:39:41.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders