Machinery and Equipment
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ወላይታ ሶዶ ዲስትሪክት የእርሻ ትራክተርና ማረሻ ባሉበት ሁኔታ በድርድር ጨረታ አወዳድሮ ለመሽጥ/ለማከራየት ይፈልጋል
Description
የድርድር ጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ወላይታ ሶዶ ዲስትሪክት በሊዝ ፋይናንሲንግ ሞዳሊቲ የአቶ አበበ ሃዋዱ የእርሻ መካናይዜሽን አገልግሎት መስጫ የእርሻ ትራክተር እና የእርሻ ማረሻ በዱቤ ግዥና ኪራይ ያስተላለፈ ቢሆንም ደንበኛው በውሉ መሰረት የኪራይ ክፍያ ግዲታቸውን ባለመወጣታቸው ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የእርሻ ትራክተርና ማረሻ ባሉበት ሁኔታ በድርድር ጨረታ አወዳድሮ ለመሽጥ/ለማከራየት ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ |
የተከራዩ ስም |
የሚሸጠው ንብረት አይነት እና ዝርዝር መረጃ |
ንብረቱ የሚገኝበት አድራሻ |
የድርደር ጨረታ መነሻ ዋጋ (ብር) |
የድርድር ጨረታ የሚካሄድበት ቦታ |
የድርድር ጨረታ የሚካሄድበት ቀንና ሰዓት |
የጨረታ ሁኔታ |
|
1 |
አቶ አበበ ሃዋዴ የእርሻ መካናዜሽን አገልግሎት መስጫ |
1 የእርሻ ትራክተር (በቁጥር 01 ) ብራንድ Massey Ferguson የስሪት ዘመን 2021 አቅም 112HP እና ሞዴል MF6711 2.የእርሻ ማረሻ (በቁጥር 01) ብራንድ (OTMA የስሪት ዘመን 2019 ሞዴል O/QD70/E፤ |
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ሐዋሳ ዲስትሪክት ጽ/ቤት ቅጥር ጊቢ ውስጥ ነው።
|
5,923,887.97
|
በኢትዮጵያ ልማት ባንክ ወላይታ ሶዶ ዲስትሪክት ጽ/ቤት ውስጥ ነው።
|
ጥቅምት 12 ቀን 2019 ዓ.ም 4፡00 እስከ 6፡00 |
የድርድር ጨረታ |
የድርድር ጨረታው መመሪያ
1. በድርድር ጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ ተደራዳሪ የታደሰ መታወቂያ ኮፒና የሚገዛበትን ዋጋ የሚገልጽ ማመልከቻ፤ የድርድር መነሻ ዋጋ 1/5ኛ በኢትዮጵያ ልማት ባንክ ወላይታ ሶዶ ዲስትሪክት ስም የተዘጋጀ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) በማስያዝ እስከ ጥቅምት 11 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ እስከ 10፡00 ድረስ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ወላይታ ሶዶ ዲስትሪክት ጽ ቤት ወርክ አውት ዲቪዢን ማመልከቻ ይዞ መቅረብ ይቻላል።
2. ንብረቱ የሚገኘው በሀዋሳ ከተማ፤ ሐይቅ ዳር ክ/ከተማ፤ በኢትዮጵያ ልማት ባንክ በሐዋሳ ዲስትሪክት ቅጥር ግቢ ውስጥ ነው።
3. ንብረቱን ሙሉ በሙሉ በካሸ በጥሬ ገንዘብ ለመግዛት ተወዳድሮ ያሸነፈ ተደራዳሪ፡-
- የንብረቱ የሽያጭ ዋጋ ላይ 15% ተጨማሪ እሴት ታክስን (VAT) እና ሌሎች ገዥ እንዲከፍላቸው በሕግ የተወሰነ የታክስ ክፍያን ጨምሮ ይከፍላል።
- ንብረቱን ከመረከቡ በፊት በዘርፉ ከቀረጥ ነጻ የመጠቀም መብት ማቅረብ ያስፈልጋል ወይም መንግሥት ከንብረቶቹ የሚፈልገውን የጉምሩክ ቀረጥና ታክስ መከፈል ግዴታ አለበት።
4. የድርድር ጨረታው አሸናፊ ባንኩ ማሸነፉን በደብዳቤ ከገለጸበት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ በ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ አጠቃሎ መከፈል ይኖርበታል። የድርድር ጨረታው አሸናፊ በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ቀሪ ገንዘብ አጠቃሎ ካልከፈለ ጨረታው ተሰርዞ ያስያዘው ገንዘብ በሙሉ ለባንኩ ገቢ ይደረጋል። ለተሸነፉ የድርድሩ ተጫራቾች ያስያዙት ገንዘብ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል።
5. ንብረቱ በባንኩ ካፒታል ዕቃ ዱቤ ግዥና ኪራይ መስፈርት መሰረት የመከራየት እቅድ ያለው ተደራዳሪ የባንኩን ካፒታል ዕቃ ዱቤ ግዥና ኪራይ መስፈርት ስለማሟላቱ በቅድሚያ እርግጠኛ መሆንና በባንኩ ፖሊሲ እና መመሪያ መሰረት ባንኩ የሚያከናውነው የፕሮጀከት ጥናት ላይ የሚቀመጡ ቅድመ ሁኔታዎችን መስማማት ይጠበቅበታል።
6. የድርድር ጨረታው አሸናፊ፤ አሸናፊ ሆኖ አስፈላጊውን ሂደት ካጠናቀቀበት ቀን ጀምሮ ንብረቱን ለማስተዳደር የሚወጡ ወጪዎችን ማለትም የመጠለያ ኪራይ፤ የጥበቃ ክፍያ አንዲሁም ተያያዥ ወጪዎችን የመሸፈን ግዴታ አለበት።
7. የካፒታል ዕቃው ካለበት መጋዘን ወደ ሚፈልግበት ቦታ ማጓጓዣ ወጪ፤ የጉዞ ኢንሹራንስ፣ መትከያ፤ ሥራ ማስጀመሪያና ተያያዥ ወጪዎችን ገዥው ተከራይ ይሸፍናል።
8. ስለንብረቱ ሁኔታ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ኢትዮጵያ ልማት ባንክ ወላይታ ሶዶ ዲስትሪክት በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር በስልክ ቁጥር 046-180-1528 38 ደውሎ ማነጋገር ይችላል።
9. የድርድር ጨረታ ተጫራቹ ወይም ሕጋዊ ወኪል በተገኘበት ጥቅምት 12 ቀን 209ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት በኢትዮጵያ ልማት ባንክ ወላይታ ሶዶ ዲስትሪክት ሎን ወርከአውት ዲቪዥን ቢሮ ይደረጋል።
10. ንብረቶቹን መጎብኘት የሚፈልግ ተደራዳሪ ተጫራች ከድርድር ጨረታ ቀን በፊት ባሉት ጊዜያት ቀጠሮ በመያዝ ንብረቶቹ በሚገኙበት በሐዋሳ ዲስትሪከት ቅጥር ግቢ ውስጥ በአካል በመቅረብ መጎብኘት ይቻላል።
11. ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ የድርድር ጨረታን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።በተጨማሪም ንብረቱ በገዥው ስም እንዲዞር ባንኩ ለሚመለከተው መንግሥታዊ አካል ደብዳቤ ይጽፋል።
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ወላይታ ሶዶ ዲስትሪክት
Tender details
- Deadline: 2026-10-22
- Bid closing time: 10:00
- Bid opening: 2026-10-22 10:00
- Region: South Ethiopia Regional State
- Publishing entity: Development Bank of Ethiopia
- Buyer address: DBE Head Office, Property and Facility Management Directorate Procurement Team, Tower II,5th floor,
- Bid bond: 1/5ኛ
- Published on: Addis Zemen (Oct 07, 2026)
- Posted at: 2026-10-08T09:09:34.000Z
- Source: Qelal Tenders