Stationery

በአብክመ ሰሜን ሽዋ ዞን የአጣዬ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በስሩ ላሉ ሴክተር ጽ/ቤቶች የጽህፈት መሳሪያዎች፣ አላቂ የቢሮ ዕቃዎች፣ የጽዳት እቃ እና ደንብ ልብስ ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 01/2019

በአብክመ ሰሜን ሽዋ ዞን የአጣዬ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በስሩ ላሉ ሴክተር ጽ/ቤቶች

  • የጽህፈት መሳሪያዎች፣
  • አላቂ የቢሮ ዕቃዎች፣
  • የጽዳት እቃ እና
  • ደንብ ልብስ ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም

  1. በዘርፉ የወጣ ንግድ ፈቃድና በዘመኑ የታደሰ ፎቶ ኮፒ ማቅረብ የምትችሉ
  2. መለያ ቁጥር /ቲን/ ፣ ግዥው ከ500000/አምስት መቶ ሺህ /ብር በላይ መሆኑ ሲታመን ተጫራቹ የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን ማስረጃ ፎቶ ኮፒ በማድረግ ማቅረብ የምትችሉ
  3. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-2 የተዘረዘሩትን ማስረጃዎችን በግልጽ የሚታይ ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸዉ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው
  4. የሚገዙ ዕቃዎች አይነትና ዝርዝር መግለጫ/ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ።
  5. ተጫራቾች በቀረበው ዝርዝር መስረት ለሚጫረቱበት ጠቅላላ ዋጋ 25000 /ሃያ አምስት ሺህ ብር ብቻ/ የጨረታ ማስከበሪያ የግዥ መመሪያው በሚፈቅደው ማሲያዣ መሰረት በCPO ወይም በጥሬ ገንዘብ በአጣ/ከ/አስ/ገንዘብ ጽ/ቤት ገቢ በማድረግ / ደረሰኙን ማቅረብ ይኖርባችኋል።
  6. የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 400/አራት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል ከአጣ/ከ/አስ/ ገንዘብ ጽ/ቤት መግዛት ትችላላችሁ።
  7. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በታሸገ ፖስታ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ለ10 ተከታታይ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡30 ሰዓት ከአጣ/ከ/አስ/ ገንዘብ ጽ/ቤት ዘወትር በስራ ሰዓት በመቅረብ መግዛትና ለዚሁ በተዘጋጀው በጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ትችላላችሁ።
  8. ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ በዚሁ ዕለት በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታው ይከፈታል።
  9. ጨረታው በ11ኛው ቀን የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
  10. ተጫራቾች በራሳቸው የዋጋ ማቅረቢያ ሞልተው ማቅረብ አይችሉም።
  11. ተጫራቾች የጨረታውን ዋጋ ሲሞሉ ስርዝ ድልዝ መሆን የለበትም፤ ከሆነ ከውድድር ውጭ ይሆናል።
  12. መ/ቤቱ ግዥውን ውል ከመፈረሙ በፊት የቀረበውን ዋጋ ሳይቀይር እስከ በ20% ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል።
  13. በጨረታ አሸናፊው ተጫራች ለጽ/ቤቱ ባቀረበው የዋጋ ዝርዝር ከጠቅላላ ዋጋ ከነቫቱ 10% የውል ማስከበሪያ በCPO ወይም በጥሬ ገንዘብ በማስያዝ ውል የመፈረም ግዴታ ያለበት መሆኑን ማወቅ አለበት።
  14. በጨረታ አሸናፊው ተጫራች ያሸነፈበትን እቃ ሙሉ በሙሉ በጽ/ቤቱ ንብረት ክፍል ባለበት ቦታ ማስረከብ እንዳለበት ማወቅ ይኖርበታል።
  15. ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  16. ተጫራቾች የተናጠል ዋጋ ሲሞሉ ወደ ጎን ድምር በመደመር መላታቸሁን መዘንጋት የለባችሁም።
  17. ጨረታው በአብክመ የመንግስት ግዥ አፈጻጸም መመሪያ ቁጥር 144/2018 መሰረት ተፈፃሚ ይሆናል።

ማሳሰቢያ ፡-

  • መረጃ መጠየቅ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 033 661 0688 ወይም 09 10 66 34 22 ላይ በመደወል መጠየቅ ይቻላል።
  • ጨረታውን የምናወዳድረው በሎት ስለሆነ በሎቱ ውስጥ ላሉ ዕቃዎች በሙሉ ዋጋ መሞላት አለበት፤ ተጫራቹ ካልሞላ ከውድድር ውጭ ይሆናል።
  • የገዙትን የጨረታ ሰነድ ምንም ሳያስቀሩ የድርጅቱን ማህተም በማድረግ ሳይቀናነስ መመለስ ይኖርባችኋል።
  • በዚሁ ጽ/ቤት ቀደም ሲል ለውድድር ተጋብዘው አሸናፊ ሆነው ለማቅረብ ፈቃደኛ ያልሆኑ ነጋዴዎችን በሙሉ የማናሳትፍ መሆኑን ማወቅ ይኖርባችኋል።

የሰሜን ሸዋ ዞን የአጣዬ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት

አጣዬ


Tender details

  • Deadline: 2026-10-17
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-10-17 10:30
  • Bid opening (note): ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: North Shewa Zone Ataye City Administration Finance and Economic Development Bureau
  • Bid bond: 25,000.00 ብር
  • Bid document price: 400.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Oct 07, 2026)
  • Posted at: 2026-10-08T09:20:40.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders