Business, Industry and Factory Foreclosure

አማራ ባንክ አ.ማ. ድርጅት፣ መኖሪያ ቤት በግልጽ የሐራጅ ጨረታ አወዳድር ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

የሐራጅ ማስታወቂያ

የሐራጅ ቁጥር፦ አማራ ባንከ/51/2019

አማራ ባንክ አ.ማ በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 216/92 በተሰጠው ስልጣን መሠረት ከዚህ ቀጥሱ የቀረበውን ንብረት በግልጽ የሐራጅ ጨረታ አወዳድር ለመሸጥ ይፈልጋል።

ለሶስተኛ ጊዜ የወጣ የሐራጅ ማስታወቂያ

ተ.ቁ

የተበዳሪው ስም

የንብረት አስያዥ ስም

አበዳሪው ቅርንጫፍ

የንብረቱ አድራሻ

የቦታው ስፋት

የባለቤትነት ማረጋገጫ ሰነድ ቁጥር

የንብረቱ ዓይነት የይዞታው አገልግሎት

የጨረታ መነሻ ዋጋ/ብር/

ጨረታው የሚከናወንበት

ክ/ከተማ

ከተማ

ወረዳ

ቀበሌ

ቀን

ሰዓት

ቦታ

1

አንዋር መሀመድ አብዱልቃድር

አንዋር መሀመድ

ሎጊያ

 

ሎጊያ

 

ሎጊያ

 

_

03

1224 ካ.ሜትር

 

ሠ/ሎ/ከ/አ/491/17

ለድርጅት

11,341,159.19

 

ጥቅምት 27 ቀን 2019 ዓ.ም.

ከ4፡00 እስከ 5፡00 ሰዓት

አማራ ባንክ አ.ማ ደሴ ዲስትሪክት ቢሮ

2

አለው ቢተው ትዛዙ

 

ወ/ሮ ጥሩዓለም እጅጉ ዘሪሁን

ፍኖተ ሰላም

_

ፍኖተ ሰላም

04

_

250 ካ.ሜ

5918ለ_2014

ለመኖሪያ

1,307,585.52

ጥቅምት 27 ቀን 2019 ዓ.ም.

ከ3፡00እስከ 4፡00 ሰዓት

አማራ ባንክ አ.ማ ባህር ዳር ዲስትሪክት ቢሮ

3

ፀሀይነሽ ሆኔ ኃይሌ

ፀሀይነሽ ሆኔ ኃይሌ

ደብረታቦር

_

ደብረታቦር

_

01

650 ካሬ ሜትር

8.2/27/898/14

መኖሪያ

14,994,071.19

ጥቅምት 27 ቀን 2019 ዓ.ም.

ከ4፡00 እስከ 5፡00 ሰዓት

አማራ ባንክ አ.ማ ባህር ዳር ዲስትሪክት ቢሮ

ማሳሰቢያ

  1. ተጫራቾች የጨረታ መነሻ ዋጋ 1/4% ወይም ሃያ አምስት በመቶ (25%) በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ሰነድ (CPO) ብቻ በአማራ ባንክ አማ ስም በማሠራት; በማሰያዝ እና በመመዝገብ በጨረታው ላይ መሳተፍ ይችላሉ።

2. ከፍተኛ ዋጋ የሰጠው ተጫራች የጨረታው አሸናፊ ነው የሚባለው ከባንኩ አሸናፊነቱን የሚገልጽ ደብዳቤ በጽሑፍ ሲደርሰው ብቻ ነው።

3. የጨረታ አሸናፊው አሸናፊ መሆኑ በድብዳቤ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 አስራ አምስት ቀናት ውስጥ ቀሪውን ገንዘብ አጠናቆ መክፈል ይኖርበታል። ባይከፍል ግን የሐራጁ ውጤት ተሰርዞ ያስያዘው ሲፒኦ አይመለስለትም፤ ለባንኩ ገቢ ይሆናል። በተጨማሪም ንብረቱ ድጋሚ ለሐራጅ ሲቀርብ ለሚታየው የዋጋ ልዩነት ይጠየቃል። ላላሸነፉት ተጫራቾች ግን ያስያዙት ሲፒኦ በዕለቱ ይመለስላቸዋል።

4. የሐራጁ አሸናፊ ገዥ ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ማናቸውንም ለመንግሥት የሚከፈሉ ክፍያዎችን የሊዝን ከፍያን ጨምሮ፤ ግብር፤ በዋጋው ላይ ሚታሰብ ተጨማሪ እሴት ታክስ (15%) ካለ ከስም ማዘዋወሪያ ጋር የተገናኙ እና ሌሎች ገዥ እንዲከፍላቸው በሕግ የተወሰኑ ታክስ እና ግብሮች ገዥው አሸናፊው ይከፍላል።

5. ተጫራቾች በሐራጅ ለመሳተፍ ሲመጡ መታወቂያ የቀበሌ የመንጃ ፍቃድ፣ ፓስፖርት ወይም ብሄራዊ መታወቂያ መያዝ ይገባቸዋል። ተጫራቾች የሕግ ሰውነት የተሰጣቸው አካላት ከሆኑ ደግሞ ሕጋዊ ሰውነት ያገኙበትን የዋና ምዝገባ ምስክር ወረቀት እና ሐራጁን ለመሳተፍ የቀረበው ግለሰብ ሥልጣኑን የሚያሳይ በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ጽ ቤት የጸደቀ መመስረቻ ጽሑፍ የመተዳደሪያ ደንብ፣ ቃለጉባኤወይም የውክልና ሰነድ ይዞ መቅረብ አለበት።

6. ንብረቱ በገዢው ስም አንዲዞር ባንኩ ለሚመለከተው መንግሥታዊ አካል ደብዳቤ ይጽፋል።

7. ለሐራጅ የቀረበውን ንብረት ለመጎብኘት የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች የጉብኝት ፕሮግራም ከወርካውትና ሪከቨሪ ከፍል ጋር አስቀድሞ ቀጠሮ በማስያዝ ጨረታው ከመካሄዱ ከ5 ቀን በፊት መጎብኘት ይችላል።

8. ጨረታው በሰንጠረዡ ላይ በተጠቀሰው ቀን፣ ሰዓትና ቦታ ተጫራቾች፣ ተበዳሪ እና ንብረት አስያዥ ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው እና ታዛቢዎች በተገኙበት ይካሄዳል። ነገር ግን ተበዳሪውም ሆነ መያዣ ሰጪው ባይገኙ ጨረታው በሌሉበት ይካሄዳል።

9. ንብረቱን/ቶቹን በጨረታ አሸንፎ የገዛ ግለሰብ ድርጅት የሽያጭ ገንዘቡን ከፍሎ ባጠናቀቀ በ15 ቀናት ጊዜ ውሰጥ ንብረቱን መረከብ ያለበት ሲሆን በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ንብረቱን ካልተረከበ በንብረቱ ላይ ለሚደርስ ጉዳት ባንኩ ኃላፊነት አይወስድም። ገዥው በተጠቀሰው ጊዜ ንብረቶቹን ካልተረከበ ከንብረቶቹ ጋር በተያያዘ ለሚኖር ወጪ ኃላፊነቱን ይወስዳል።

10. በባንኩ የብድር ፖሊሲ መመሪያ እና ቅድመ ሁኔታ መሰረት የሚፈለገውን ማስረጃ አሟልቶ ለቀረበ የጨረታ አሸናፊ ባንኩ፤

  • እስከ 100% ድረስ ብድር ሊያመቻች ይችላል።
  • በንብረቱ ላይ የምርት ተግባር ለሚያከናውኑ ገዥዎች ባንኩ ተጨማሪ ብድር ሊያመቻች ይችላል። በተጨማሪም ለባንኩ የተሸለ ጥቅም የሚያስገኝ ከሆነ ባንኩ ለመደራደር ዝግጁ ነው።

11. የተጫራቾች ምዝገባ ከሐራጁ መዝጊያ ሰዓት 30 ደቂቃ በፊት ይጠናቀቃል።

12. በወንድ አንቀጽ የተጠቀሰው ለሴት አና ሕጋዊ ሰውነት ላላቸው ድርጅትም ያገለግላል።

13. ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

14. ለበለጠ ማብራሪያ አማራ ባንክ አ.ማ 011 558 2764 ወይም 011 558 4189 በሥራ ሰዓት ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

አማራ ባንክ


Tender details

  • Deadline: 2026-11-06
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid opening: 2026-11-06 12:00
  • Bid opening (note): በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Amhara Bank S.C.
  • Bid bond: 25%
  • Published on: Addis Zemen (Oct 07, 2026), Reporter (Oct 07, 2026)
  • Posted at: 2026-10-08T11:23:59.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders