Cleaning and Janitorial Equipment and Service
ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ/የተ/የግል ማህበር የተለያዩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዢ ለመፈጸም ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
CN/NCB/08/19
ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ/የተ/የግል ማህበር ለድርጅታችን የሚያስፈልጉ
- ሎት 1 የተለያዩ የፅዳት ማሽነሪዎች (Different Cleaning Machineries)፡- Floor Scrubbing machine, backpack vacuum cleaner, Driving type electrical Road sweepers, etc
- ሎት 2፡- የፅዳት ማሽነሪዎች መለዋወጫ አቅርቦትና የጥገና አገልግሎት
- ሎት 3፡- የመኪና ግዥ (Mid - Bus, Double Pickup, Van mini bus)
- ሎት 4፦ ኢቪ ቻርጀሮች DC
ማቅረብ የሚችሉ ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዢ ለመፈጸም ይፈልጋል። በመሆኑም ተጫራቾች የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ በጨረታ ላይ መሳተፍ እንደሚችሉ የሚገልጽ ደብዳቤ፣ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡትን ማስረጃ፣ የተጨማሪ እሴት ታከስ የምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ እና የዕቃው ዝርዝር መግለጫ በተለየ በሰም በታሸገ ፖስታ እንዲሁም ዕቃዎቹን የምታቀርቡባቸውን ዋጋ በተለየ በሰም በታሸገ ሁለተኛ ኤንቨሎፕ በማድረግ እንድትወዳደሩ ይጋብዛል። የጨረታ ዶክመንቱን ቦሌ መንገድ ደንበል የገበያ ማዕከል ጀርባ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መ/ቤት ህንፃ 5ኛ ፎቅ የግዢ ዋና ክፍል ብር 100.00 በመክፈል ከሰኞ እስከ አርብ (ጠዋት 2፡00-6፡00 እና ከሠዓት 7፡00-11፡00 እንዲሁም ቅዳሜ ግማሽ ቀን ጠዋት 2፡00-6፡00) ማግኘት ይቻላል። የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ለሎት 2 ብር 50,000 ለሎት 1, 3 እና 4 ብር 100,000 ለእያንዳንዳቸው በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ. ከመጫረቻ ዶክመንት ጋር መቅረብ ይኖርበታል። ተጫራቾች የመጫረቻ ዶክመንታቸውን ከላይ በተጠቀሰው አድራሻና የሥራ ሰዓት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ ጥቅምት 10 ቀን 2019 ዓ.ም 4፡00 ድረስ ማስገባት ይችላሉ። ጨረታው በዚሁ ዕለት ጠዋት በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል። የዕቃዎች ርክክብ የሚደረግበት ቦታ ገርጂ የድርጅቱ የዕቃ ግምጃ ቤት ይሆናል። ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች ያላሟላ ተጫራች ያለተጨማሪ ማስታወቂያ ከውድድሩ ውጪ ይደረጋል።
ድርጅቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ.የተ.የግ.ማ
ቦሌ መንገድ ደንበል የገበያ ማዕከል ጀርባ በሚገኘው የድርጅቱ
ዋና መ/ቤት ህንፃ 5ኛ ፎቅ
ስልክ ቁጥር 011-156 9992
አዲስ አበባ
የኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ.የተ.የግ.ማ
Tender details
- Deadline: 2026-10-20
- Bid closing time: 10:00
- Bid opening: 2026-10-20 10:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Commercial Nominees P.L.C.
- Buyer TIN: 0000958158
- Buyer address: ቦሌ መንገድ ደንበል የገበያ ማዕከል ጀርባ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መ/ቤት ህንፃ 5ኛ ፎቅ
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 100.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Oct 07, 2026)
- Posted at: 2026-10-08T11:35:35.000Z
- Buyer website: https://commercialnominees.com/
- Source: Qelal Tenders