Others

የደቡብ ኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን በሥሩ ላሉት ዲስትሪክቶች አገልግሎት የሚውሉ የኮንስትራክሽን እና ኢንጅነሪንግ መሣሪያዎች መገልገያ ማለትም ዶዘር፣ ሎደር፣ ግሬደር፣ ኤክስካቫተርና ሮለር ብቁ ተጫራቾችን አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር ደኢመባ 07/2019

መ/ቤታችን የደቡብ ኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን በሥሩ ላሉት ዲስትሪክቶች አገልግሎት የሚውሉ የኮንስትራክሽን እና ኢንጅነሪንግ መሣሪያዎች መገልገያ ማለትም ዶዘር፣ሎደር፣ግሬደር፣ኤክስካቫተርና ሮለር ብቁ ተጫራቾችን አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል::

በመሆኑም፡-

1. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችለውን የዘመኑን ግብር የተከፈለበትን ከሚፈለገው አገልግሎት የተዛመደ የንግድ ሥራ ወይም የአገልግሎት ሥራ ፈቃድ፣የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

2. ተጫራቾች ዋጋቸውን በታሸገ ኢንቨሎፕ የፋይናንሻል ፕሮፖዛሉን በተለያየ ፖስታ በማድረግ አንድ ዋና እና አንድ ኮፒ ኦሪጂናል እና ኮፒ በማለት እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያው በተለያ ፖስታ ኦሪጅናል እና ኮፒ ለብቻው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

3. ተጫራቾች ሰነዱን የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር ብቻ/ በመክፍል ከባለስልጣኑ ዋና መ/ቤት መውሰድ ይችላሉ፡፡

4. የጨረታው አሸናፊ የሚወሰነው በጨረታ ሰነዱ ውስጥ በተመለከቱት መስፈርቶች መሠረት ሲሆን ጨረታው ዜግነትን ሳይመለከት ለማንኛውም አቅራቢ ክፍት ነው፡፡

5. አቅራቢዎች ጨረታውን ለዚህ ተግባር በተዘጋጀ ሳጥን ገቢ የሚያደርጉት ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ድረስ ይሆናል፡፡ ጨረታው በዚያኑ ቀን ከቀኑ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል፡፡ ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡

6. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ማሽን ብር 20,000.00 /ሃያ ሺህ ብር ብቻ/ የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በግዥ መመሪያው ላይ በተፈቀደ አቅራቢው በሚፈልገው ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ከዚህ ውጭ በኢንሹራንስ የሚቀርብ የጨረታ ማስከበሪያ የጨረታ ማስከበሪያ ተቀባይነት የለውም፡፡

7. ተጫራቾች በጨረታው ደንብና መመሪያ መሰረት ጨረታውን ማቅረብ አለባቸው፡፡ ከጨረታው ደንብና መመሪያ ውጭ የሚቀርብ ማንኛውም ጨረታ ተቀባይነት የለውም፡፡

8. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

9. ለበለጠ መረጃ ተጫራቾች የሚከተለውን አድራሻ መጠቀም ይችላሉ፡፡

የደቡብ ኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን

አቅ/ን/አስ/ደጋፊ የሥራ ሃደት

የፖስታ ሳጥን ቁጥር 404

የስልክ ቁጥር 0911 041 447 / 0923 690 085

ዲላ ኢትዮጵያ

ደቡብ ኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን


Tender details

  • Deadline: 2026-10-23
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00
  • Bid opening: 2026-10-23 14:30
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡30
  • Region: South Ethiopia Regional State
  • Publishing entity: South Ethiopia Roads Authority
  • Bid bond: 20,000.00 ብር ለእያንዳንዱ ማሽን
  • Bid document price: 500.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Oct 08, 2026)
  • Posted at: 2026-10-08T12:23:35.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders