Cleaning and Janitorial Equipment and Service
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር የፃግብጅ ወረዳ ገን/ጽ/ቤት ለወረዳው ሴ/መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል የተለያዩ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ ማወዳደር ይፈልጋል
More tags
Description
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር የፃግብጅ ወረዳ ገን/ጽ/ቤት ለወረዳው ሴ/መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል የፅሕፈት መሳሪያ፤ የፅዳት እቃዎች፤ ህትመት፤ የውሃ እቃዎች ፤ የህንፃ መሳሪያ፤ የመኪና መለዋወጫ እቃዎች፤ የመኪና ጎማ፣ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ፤ የፈርኒቸር ውጤቶች፣ የደንብ ልብስ ፤ የስፖርት ትጥቅ፤ በግልፅ ጨረታ ማወዳደር ይፈልጋል::
ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
1. በየዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው
2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር(TIN)
4. የቫት ተመዝጋቢ የሆነ
5. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን “ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ ቫትን ጨምሮ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒዩ ወይም ጥሬ ገንዘቡን ከፖስታው ጋር ማያያዝ አለባቸው
7. የእቃዎቹን አይነት ዝርዝር መግለጫ/ስፔስሬፊኬሽን ከጨረታ ሰነድ ማግኝት ይችላሉ
8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 ሁለት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 ቀን ከ 28/01/2019 እስከ 07/02/2019 11፡30 ድረስ ሰነድ መግዛት የሚቻል ሲሆን በ08/02/2019 3፡30 ድረስ የገዙትን ሰነድ በማስገባት በ 08/02/2019 ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ይከፈታል:: ጨረታው የሚከፈተው ተጫራች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሲሆን በሰዓቱ ካልተገኙ ጽ/ቤቱ በሌሉበት የመክፈት መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
9. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጆች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
10. ጨረታው በሚከፈትበት ቀን በካላንደር ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል ፡፡
11. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኝ በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው
12. ጨረታው ስርዝ ድልዝ ወይም የማይነበብ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
13. በዚህ የጨረታ ማስታወቂያ ያልተካተቱ ህግና ደንቦች በግዥ መመሪያ ቁጥር 144/2018 ተግባራዊ ይደረጋል፡፡
14. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ሁሉ የጨረታውን ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 2 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር የፃግብጅ ወረዳ ገን/ጽ /ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-10-18
- Bid closing time: 09:30
- Bid opening: 2026-10-18 10:00
- Region: Amhara
- Publishing entity: Tsagibji Woreda F/E/D/B
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Oct 08, 2026)
- Posted at: 2026-10-08T12:27:16.000Z
- Source: Qelal Tenders