Cleaning and Janitorial Equipment and Service

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ሳርማሌ ወረዳ ፋይናንስና ፕላን ልማት ጽ/ቤት ለወረዳው ሴክተር መስሪያ ቤቶች በ2019 በጀት ዓመት የጽህፈት መሣሪያና ሌሎች አላቂ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

የጽህፈት መሳሪያና ሌሎች አላቂ ዕቃዎች ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ

ጨረታ ቁጥር 1/2019

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ሳርማሌ ወረዳ ፋይናንስና ፕላን ልማት ጽ/ቤት ለወረዳው ሴክተር መስሪያ ቤቶች በ2019 በጀት ዓመት የጽህፈት መሣሪያና ሌሎች አላቂ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በጨረታ ለመሳተፍ መሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች:-

1. በዘርፉ ንግድ ፈቃድ የዘመኑ ግብር ተከፍሎ የታደሰ ፣ቲን ቁጥር ሰርተፊኬት የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት የቫቲ ተመዝጋቢነት ምስክር ወረቀት ያለውና የሚያቀርብ፣

2. ጨረታው የሚካሄድበት ቦታ ሳርማሌ ወረዳ ፋይናንስና ፕላን ልማት ጽ/ቤት ግዥና ንብረት ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር-5

3. ተፈላጊ የጽህፈት መሳሪያና ሌሎች አላቂ ዕቃዎችን የሚያቀርብበትን ዋጋ በዋጋ ማቅረቢያ ፕሮፎርማ ሞልቶ ከተፈላጊ መረጃዎች ፎቶ ኮፒ ጋር በፖስታ አሽጎ የሚያቀርብ

4. የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 50/ሃምሳ ብር ብቻ/ ለሳርማሌ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት በመክፈል ይህ ጨረታ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ እስከሚያበቃበት ቀን ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከፋይናንስ ጽ/ቤት ግዥና ንብረት ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር–5 መውሰድ ይቻላል፡፡

5. ጨረታ ሣጥን የሚታሽግበትና የሚከፈትበት ቀንና ሰዓት በተመለከተ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ወደ ፊት የሚቆጠር በ16ኛው ቀን በ8፡00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ በ8፡15 ደቂቃ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ዕለቱ በሳምንት ዕረፍት ወይም በህዝብ በዓል ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡

6. የጨረታ አሸናፊ አሸናፊነት ይፋ ከሆነበት ዕለት ጀምሮ ለ5 የሥራ ቀናት ለቅሬታ አቤቱታ ጊዜ ሰጥቶ ከ8ኛው እስከ 15ኛው ቀን ድረስ የጠቅላላ ዋጋ 10 % የውል ማስከበሪያ ይዞ በመቅረብ ውል ካልተፈራረመ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ሲፒኦ ለመንግስት ውርስ በማድረግ ለአፈፃፀሙ ለክልል ግዥ ኤጀንሲ ሪፖርት እናደርጋለን።

7. የጨረታ ማስከበሪያ 10,000//አስር ሺህ ብር ብቻ/ በጥሬ ገንዘብ ወይም በሲፒኦ የሚያስይዝ መሆን አለበት።

8. አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈውን ዕቃዎችን ሁሉንም ወጪ ችሎ እስከ ሳርማሌ ወረዳ ፋይናንስና ፕላን ልማት ጽ/ቤት መጋዘን ድረስ አቅርቦ ማስረከብ አለበት።

9. ተጫራቾች ተሟልተው ያለመገኘት የጨረታ ሂደትን አያስተጓጉልም።

10. አሸናፊ ተጫራች ያሸነፈበትን ዕቃ በጥራት 1ኛ ደረጃ እና ኦርጅናል መሆን አለበት። አቀላቅሎ የሚያቀርብ ካለ እንደተጭበረበረ ተቆጥሮ በክልል ግዥ ኤጀንሲና በህግ እርምጃ እንዲወሰድበት ይደረጋል፡፡

11. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፈል የመሰረዝ መብት አለው፡፡

ለበለጠ መረጃ፡- 0920 984 330 / 0916 172 728

ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሳርማሌ ወረዳ ፋይናንስና ፕላን ልማት ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-10-22
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ወደ ፊት የሚቆጠር በ16ኛው ቀን በ8፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-10-22 14:15
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ወደ ፊት የሚቆጠር በ16ኛው ቀን በ8፡15 ሰዓት
  • Region: South Ethiopia Regional State
  • Publishing entity: ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሳርማሌ ወረዳ ፋይናንስና ፕላን ልማት ጽ/ቤት
  • Bid bond: 10,000.00 ብር
  • Bid document price: 50.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Oct 07, 2026)
  • Posted at: 2026-10-08T12:38:53.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders