Cleaning and Janitorial Equipment and Service
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ከተማና መሠረተ ልማት ቢሮ እና ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ በ2019 በጀት ዓመት ለቢሮ አገልግሎት የሚውል የተለያዩ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
More tags
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ከተማና መሠረተ ልማት ቢሮ እና ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ በ2019 በጀት ዓመት ለቢሮ አገልግሎት የሚውል ከዚህ በታች በተዘረዘሩት ሎቶች መሰረት እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
- ሎት 1.የጽህፈት መሳሪያዎች፣
- ሎት2. ኤሌክትሮኒክስ፣
- ሎት3. የጽዳት ዕቃዎች እና
- ሎት4. ደንብ ልብስ
ስስዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡
1. በዘርፉ የዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያለው እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለው
2. በአቅራቢነት የተመዘገበ እና የቫት ተመዝጋቢ መሆኑን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
3. በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች ወይም ህጋዊ ወኪል ከተራ ቁጥር 1-2 ላይ የተጠቀሱትን ኦርጅናል ሰነድ ይዘው መቅረብ አለባቸው፡፡
4. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 11፡30 ድረስ ከግ/ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት በመምጣት የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 200 ብር በጥሬ ገንዘብ በመከፈል የሚፈለገውን የእቃ አይነትና ዝርዝር መግለጫ(እስፔስፊኬሽን) የጨረታ ሰነድ መግዘት የሚችሉ ሲሆን ተጫራቾች የቫት ተመዝጋቢ ከሆኑ የሚያቀርቡት ዋጋ ከነቫት ነው፡፡
5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በየሎቶቹ ለየብቻ በመለየት የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ 2% ሲፒኦ ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው። የሚያስዙት የጨረታ ማስከበሪያ በቢድቦንድ ከሆነ ከ60 ቀን ያነሰ የጨረታ ማስከበሪያ ቢድቦንድ ተቀባይነት የለውም፡፡
6. አሸናፊ ተጫራች ያሸነፈባቸውን እቃዎች አሸናፊነቱ ከተገለጸበት ቀናት ጀምሮ ካሉት 5 የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የዋጋውን የውል ማስከበሪያ በየሎቱ 10% በማስያዝ ውል መውሰድ ይኖርባቸዋል፡፡
7. ተጫራቾች በየሎቱ በተለያዩ ፖስታ በማሸግ የጨረታ ሰነዱን ኦርጅናል ኮፒ በተለያዩ ፖስታ በጥንቃቄ በማሸግ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት ከተማና መሠረተ ልማት ቢሮ እና ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰአት ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ቀናት አየር ላይ ውሎ በ16ኛው ቀን 4፡00 ሰአት ድረስ በማስገባት ሳጥኑ የሚታሸግ ሲሆን በዚያ ቀን 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በመክፈቻው ዕለት የማይገኙ ከሆነ በሌሉበት ይከፈታል። የጨረታ መክፈቻው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣይ የስራ ቀን እና ሰአት የሚከፈት ሆኖል፡፡
8. ሁሉም የጨረታ ሰነድ ላይ ፊርማ መኖሩ የሚገባው ሲሆን ስርዝ ድልዝ ሲያጋጥም በፊርማ ማረጋገጥ ይጠበቅባቸዋል፡፡
9. መ/ቤቱም ካሸናፊው ድርጅት ወይም ግለሰብ ካሸነፈው እቃ ወይም ገንዘብ መጠን ላይ 20% ጨምሮ ወይም ቀንሶ የመግዛት መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
10. ተጫራቾች ክልሉ ላወጣቸው የግዥ አፈጻጸም መመሪያዎች ተገዥ መሆን ሲኖርባቸው ማሸነፉ ከተነገረ በኋላ ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታው ራስን ማግለል አይቻልም፡፡
11. አሸናፊ ድርጅት ንብረቱን በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት ከተማና መሠረተ ልማት ቢሮ እና ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ድረስ ማቅረብ ግዴታ ይሆናል፡፡
12. ቢሮው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፈልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
13. አሸናፊ ተጫራች ኦርጅናል እቃዎችን የማቅረብ ግዴታ ያለበት ሲሆን እቃዎችን የምንቀበለው በሚመለከተው ባለሙያ ሲያረጋግጥ ነው፡፡
14. በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር ማስረጃ ከፈለጉ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት ከተማና መሠረተ ልማት ቢሮ እና ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 057 775 2939 / 0913 248 379 በመደወል ማግኘት ይቻላል፡፡
ማሳሰቢያ፡- በማንኛውም ሁኔታ የተጫራቾች የመጫረቻ ሰነድ በሚከፈትበት ሰዓት የሚቀርብ የጨረታ ማስከበሪያ ተቀባይነት የለውም፡፡
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ከተማና መሠረተ ልማት ቢሮ እና ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ
Tender details
- Deadline: 2026-10-22
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ቀናት አየር ላይ ውሎ በ16 ኛው ቀን 4፡00 ሰአት
- Bid opening: 2026-10-22 10:30
- Bid opening (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ቀናት አየር ላይ ውሎ በ16 ኛው ቀን 4፡30 ሰአት
- Region: Beneshangul Gumuz
- Publishing entity: Benshangul Gumuz City Infrastructure Office and Trade and Market Development Office
- Bid bond: 2% በየሎቶቹ ለየብቻ
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Oct 07, 2026)
- Posted at: 2026-10-08T12:49:36.000Z
- Source: Qelal Tenders