Equipment and Accessories

የኢትዮጵያ ብሮድካሰቲንግ ኮርፖሬሽን ሠራተኞች ኃላፊነቱ የተወሰነ የሸማቾች ህብረት ስራ ማህበር የኮፊ ሀውስ እቃዎች እና የኤሌክትሪክ ማሽኖች ዕቃዎች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የብሔራዊ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ብሮድካሰቲንግ ኮርፖሬሽን ሠራተኞች ኃላፊነቱ የተወሰነ የሸማቾች ህብረት ስራ ማህበር በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ የግዥ ዘዴ በግዥ መለያ ቁጥር NCB-001-2019 የኮፊ ሀውስ እቃዎች (ሎት 1) እና የኤሌክትሪክ ማሽኖች ዕቃዎች (ሎት 2) አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በመሆኑም በመስኩ የተሰማሩና ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸው አቅራቢዎች (ድርጅቶች) ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን፡-

1. በዘርፉ የተሰማራ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ኮፒ (Valid Trade Licensee)

2. የታክስ ከፋይ የምዝገባ ሰርተፍኬት

3. የተጨማሪ እሴት ታከስ የምዝገባ ሰርተፊኬት ኮፒ (VAT Certificate)

4. በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል የታደሰ ፈቃድ (Valid Tax Clearance Certificate)፡

5. የጨረታ ማስከበሪያ በባንከ የተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ወይም የባንከ ጋራንቲ ለኮፊ ሀውስ እቃዋች (ሎት 1) ብር 10,000.00 (አስር ሺህ ብር) እና ለኤሌክትሪከ ማሽኖች ዕቃዎች (ሎት 2) ብር 15,000.00 (አስራ አምስት ሺህ ብር) በማቅረብ በግልፅ ጨረታው ላይ መወዳደር ይችላሉ። በጨረታው መወዳደር የሚፈልጉ አቅራቢዎች (ድርጅቶች) ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ጠዋት 3፡00-6፡00 ከሰዓት 7፡00-10፡00 ሰዓት ብቻ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በጥሬ ገንዘብ በመከፈል የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በሸጎሌ በሚገኘው የኢትዮጵያ ብሮድካሰቲንግ ኮርፖሬሽን ሠራተኞች ኃላፊነቱ የተወሰነ የሸማቾች ህብረት ስራ ማህበር ሱቅ መውሰድ ይችላሉ።

ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ዶክመንት በታሸገ ኤንቨሎፕ ኦሪጅናል እና ኮፒ በመለየት እስከ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ በ5፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያኑ ቀን በ5፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ግቢ ውስጥ ይከፈታል። ሆኖም የመከፈቻ ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓላት ቀን ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል።

ማሳሰቢያ:- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ስልክ ቁጥር፡ 09 13 22 23 38, 09 11 04 59 52, 09 13 23 65 39

የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሸን ሠራተኞች ኃላፊነቱ የተወሰነ የሸማቾች ህብረት ስራ ማህበር


Tender details

  • Deadline: 2026-10-17
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ በ5፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-10-17 12:00
  • Bid opening (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ በ5፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Ethiopian Broadcasting Corporations
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 300.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Oct 07, 2026)
  • Posted at: 2026-10-08T13:03:30.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders