Tri Wheeler, Motorcycles and Bicycles Purchase
ቸሻየር ኢትዮጵያ ፒክአፕ እና ባለ ሦስት ጎማ ኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Description
ፒክአፕ እና ባለ ሦስት ጎማ ኤሌክትሪክ ተሸከርካሪ ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
ቸሻየር ኢትዮጵያ በሲቪል ማህበረስብ ድርጅቶች ባለሥልጣን በመዝግብ ቁጥር 0505 የተመዘገበ ሀገር በቀል መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ሲሆን በኢትዮጵያ ውስጥ ለበርካታ አስርተ ዓመታት ለአካል ጉዳተኞች የተሀድሶና መልሶ ማቋቋምና የድጋፍ አገልግሎቶችን በመስጠት ላይ ይገኛል። ለተለያዩ ፕሮጅክቶች ማሰፈጸሚያ የሚዉሉ ዝርዝር ሁኔታቸዉ ከዚህ በታች የተገለጠዉ አንድ በናፍጣ የሚስራ ፒክአፕና ሶስት ባለ ሶስት እግር ኤልክትሪክ ተሽከርካሪዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ |
የተሸከርካሪ ዓይነት |
መግለጫ (አስፔስፊኬሽን |
|
1 |
ፒክ አፕ መኪና |
ሁለት ጋቢና (Double Cabin ሾፌሩን ጨምሮ 5 ሰዉ የሚጭን በናፍጣ የሚሠራ ፎር ዊል ድራይቭ (4WD); |
|
2 |
2 ባለ ሶስት ጎማ ኤልክትሪክ ተሸከርካሪ |
ባለ ሁለት በር ሹፌሩን ጨምሮ 7 ሰዉ የሚጭን በኤልክትሪክ ቻርጅ የሚሠራ ፤ በአንድ ጊዜ ቻርጅ ከ100-120 ኪሎሜትር ሊጓዝ የሚችል ለአስቸጋሪ የገጠር መንገዶች ተስማሚ የሆነ |
ስለሆነም
1. ተወዳዳሪዎች የሚከተሉትን ማቅረብ አለባቸው፦
- የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ፣ የቫት (VAT) እና ግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN)
- የጨረታ አሸናፊዉ የአሸነፈዉን የተሽከርካሪ ዓይነት ወዲያዉኑ ማቅረብ የሚችል
- ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ተሽከርካሪ የሚሸጡበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ፖስታ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት 7 ተከታታይ የስራ ቀናት ለዚሁ በተዘጋጀዉ ሳጥን ዉስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፤
- ጨረታዉ በ7ኛዉ የሥራ ቀን ከቀኑ 11 ሰዓት ላይ ይዘጋል፤
- ጨረታው ተወዳዳሪዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሚቀጥለዉ የስራ ቀን ጠዋት 4:00 ሰዓት (10:00 AM) ይከፈታል። የመክፈቻው ቀን ቅዳሜ ወይም እሁድ ላይ ከዋለ በሚቀጥለው ሰኞ በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
2. የጨረታ ማስከበሪያ (Bd Security
ሁሉም ተወዳዳሪዎች ከጠቅላላ የጨረታ ዋጋቸው 2% በሲፒኦ (CPO) ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል
3. አድራሻ
ቸሻየር ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ፣ የካ ክፍለ ከተማ፣ ሲኤምሲ መንገድ
(ሳህሊተ ምህረት ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት፣ ከኢትዮጵያ ሥራ አመራር ኢንስቲትዩት ጎን
ስልክ፦ 072 301 225 / 09 11 89 88 42
Tender details
- Deadline: 2026-10-14
- Bid closing time: 17:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ በ7ኛዉ የሥራ ቀን ከቀኑ 11 ሰዓት
- Bid opening: 2026-10-15 12:00
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ በ7ኛዉ የሥራ ቀን ከቀኑ 11 ሰዓት ተዘግቶ በሚቀጥለዉ የስራ ቀን ጠዋት 4:00 ሰዓት (10:00 AM)
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Cheshire Ethiopia
- Bid bond: 2%
- Published on: Reporter (Oct 07, 2026)
- Posted at: 2026-10-08T13:08:17.000Z
- Source: Qelal Tenders