Stationery

በኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ የብረታ ብረትና ፋብሪኬሽን ኢንዱስትሪ የተለያዩ ዕቃዎች ግዥ መፈፀም ይፈልጋል

Description

የብሔራዊ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ  ቁጥር

ብ.ፋ.ኢ/ብ.ግ.ጨ/001/2019

ግዥ ፈፃሚ አካል ስም፡- በኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ የብረታ ብረትና ፋብሪኬሽን ኢንዱስትሪ

የዕቃ ግዢው ዓይነት፡-

  • ሎት 1- የተለያዩ የፅህፈት ዕቃዎች
  • ሎት 2 - የተለያዩ የፅዳት ዕቃዎች
  • ሎት 3- የተለያዩ አላቂ ዕቃዎች
  • ሎት 4- ፓስቸራይዝድ ወተት
  • ሎት 5- የመለዋወጫ ዕቃዎች
  • ሎት 6 የጥገና አገልግሎት
  •  ሎት 7- የሰራተኞች የካፌ መስተንግዶ አገልግሎት

የተጫራቾች መመሪያና ግዴታዎች

  1. የዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤
  2. ተጫራቾች በወጣው ጨረታ መሠረት በዘርፉ የተሰማሩና የተመዘገቡ ስለመሆናቸው የሚያረጋግጥ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው፣
  3. ተጨማሪ እሴት ታክስ VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት፤
  4. በግብር ከፋይነት የተመዘገቡና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር /TIN NO/ ያላቸው፤
  5. ተጫራቾች ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥና በግብር ሰብሳቢ ባለስልጣን የተሰጠ ማስረጃ
  6. ከጥቃቅንና አነስተኛ ማህበር የሚመጡ እንዲሁም ሌሎች ተጫራቾችን ጨምሮ ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት የጠቅላላ ዋጋ VAT)ን ጨምሮ ብር 2% ከታወቀ ባንክ የክፍያ ማዘዣ /CPO/ ብቻ በብረታ ብረት ፋብሪኬሽን ኢንዱስትሪ ስም ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  7. ተጫራቾች ዋጋ ሞልተው የሚያቀርቡት ከጨረታ ሰነድ ጋር ተያያዞ በቀረበው የዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ ብቻ ይሆናል፡፡ በዋጋ መሙያ ቅፅ ላይ ስርዝ ድልዝ ማድረግ እጅግ የተከለከለ ነው።
  8. ማንኛውም ተጫራች በሌላ ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይችልም።
  9. የመወዳደሪያ ጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 300.00 (ሶስት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል መካኒሳ መካነ ኢየሱስ ፊት ለፊት በሚገኘው በግዥ ክፍል ቢሮ ሰነዱን ማግኘት ይችላሉ።
  10. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በቀረበው ዝርዝር መሠረት በመሙላት የድርጅታቸውን ማህተምና ፊርማ በማድረግ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ  የስራ ቀናት ውስጥ በብረታ ብረት ፋብሪኬሽን ኢንዱስትሪ ሰፕላይ ቼይን ማኔጅመንት በግዥ ከፍል ቢሮ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2፡30 – 6፡00 እንዲሁም ከሰዓት 7፡00-10፡30 የጨረታ ሰነድ ማስገባት ይችላሉ።
  11. የጨረታ ማስገቢያ ቀንና ሰዓት ካለፈ በኋላ የሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
  12. የጨረታ መክፈቻ ቀን በህዝብ በዓላት ቀን ከዋለ የጨረታው መዝጊያና መከፈቻ ዕለት በዓሉ በዋለ በማግስቱ ይሆናል።
  13. ጨረታው ጠዋት 4፡30 ላይ ተዘግቶ 4፡45 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻችው በተገኙበት ይከፈታል።
  14. ጨረታውን አሸናፊ የሆነው ድርጅት አሸናፊ መሆኑ በደብዳቤ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ባሉት አምስት የስራ ቀናት ውስጥ ቀርቦ ውል መዋዋል አለበት።
  15. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ በሚገለፀው መመሪያ መሰረት ፋይናንሺያል እና ቴክኒካል ሰነዶችን አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  16. የብረታ ብረትና ፋብሪኬሽን ኢንዱስትሪ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ ማብራሪያ - በቢሮ ስልክ ቁጥር 0118 34 65 52 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

በኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ የብረታ ብረትና ፋብሪኬሽን ኢንዱስትሪ


Tender details

  • Deadline: 2026-10-20
  • Bid closing time: 10:30
  • Bid closing (note): ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት ጠዋት 4፡30
  • Bid opening: 2026-10-20 10:45
  • Bid opening (note): ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት ጠዋት 4፡45
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Ethio Engineering Group Metal Fabrication Industry
  • Bid bond: 2%
  • Bid document price: 300.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Oct 09, 2026)
  • Posted at: 2026-10-09T07:46:31.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders