Stationery
የአዲስ አበባ ከተማ ፍርድ ቤቶች ቋሚና አላቂ ዕቃዎች እና የአገልግሎት ግዥዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
StationeryOffice Supplies and ServicesEquipment and Accessories
Addis Ababa
More tags
Electrical, Electromechanical and ElectronicsComputer and AccessoriesIT and TelecomOffice Machines and AccessoriesCleaning and Janitorial Equipment and ServiceTextile, Garments and UniformsTextile, Garment and LeatherShoes and Other Leather ProductsOffice FurnitureFurniture and FurnishingHouse FurniturePrinted Advertising MaterialsAdvertising and PromotionPrinting and PublishingOffice Machines and ComputersMaintenance and RepairOthersMachineryFurnitureHome Appliance and SuppliesHouse and BuildingWater System InstallationConstruction and Water WorksWater Pipes and FittingsSpare Parts and Car Decoration MaterialsChemicals and ReagentsBuilding ConstructionFinishig WorksWater ConstructionInstallation, Maintenance and Other Engineering ServicesAmharic2merkatoAddis Ababa City Administration Court of Appeals
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
መለያ ቁጥር አ/አ/ከ/ፍ/ቤት/01/2019
የአዲስ አበባ ከተማ ፍርድ ቤቶች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ቋሚና አላቂ ዕቃዎች እና የአገልግሎት ግዥዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
- ሎት1. አላቂ የፅህፈት መሳሪያዎች
- ሎት2. የተለያዩ ቀለሞች
- ሎት3 አላቂ የጽዳት እቃዎች
- ሎት4. የደንብ ልብስ
- ሎት5. የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች
- ሎት6. የተለያዩ ፈርኒቸሮች
- ሎት7. የኤሌክትሪክ ዕቃዎች
- ሎት8. የተሸከርካሪ መለዋወጫ ዕቃዎች
- ሎት9. የተለያዩ የህትመት ሥራዎች
- ሎት10. የደንብ ልብስ ስፌት
- ሎት11. የኤሌክትሮኒክስ እና ማሽነሪ ጥገና ስራዎች
- ሎት12. የቤት እና የቢሮ እቃዎች ጥገና ስራ
- ሎት13. የቢሮ ጥገና እና የእድሳት ስራዎች
- ሎት14. የተለያዩ የውሃ መስመር ስራዎች ዝርጋታ እና የጥገና ስራዎች
- ሎት15. የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ እና ጥገና ስራዎች
- የግዥ መለያ ቁጥር አ/አ/ከ/ፍርድ ቤቶች 01/2019
- ግዥው ግልጽ ጨረታ ነው
- ጨረታ ሰነድ የወጣበት መስከረም ወር 2019 ዓ/ም
ተጫራቾች ህጋዊ በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ፤ እንዲሁም የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ስለመሆኑ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ሰርተፍኬት እና የጨረታ መሳተፊያ ደብዳቤ የሚያቀርቡ ላሸነፉበት እቃ የውል ማሰከበሪያ ማስያዝ የሚችሉ እንዲሁም ቋሚ የስራ ቦታ ወይንም ድርጅት ያላቸው ሆነው በቅድመ ምልከታ ወቅት ድርጅታቸውንወይንም የሥራ ቦታቸውን ማሳየት ፍቃደኛ የሆኑ ከዚህ በፊት በፍርድ ቤቱ ጨረታ አሸንፈው በገቡት ውል መሰረት ግዴታቸውን የተወጡ ድርጅቶች።
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመከፈል ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 የስራ ቀናት ውስጥ ከግዥ ፈጻሚ የአዲስ አበባ ከተማ ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት ቢሮ ኛ ፎቅ የቢሮ ቁጥር 102 በመቅረብ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ከላይ ለተገለፁት ዕቃዎች ለተወዳደሩበት ለእያንዳንዱ ሎት በባንክ በተመሰከረለት የክፍያ ትዕዛዝ (CPO) ብቻ ማቅረብ ይኖርባቸዋል ከሎት 1 እስከ ሎት 15 ድረስ ለሚወዳደሩበት ለእያንዳንዱ ሎት ከጠቅላላ ዋጋ 2% ፐርሰንት ወይም ተጫራቾች በጥቃቅን የተደራጁ ከሆነ ያደራጃቸው መስሪያ ቤት ለዋስትናው በፍርድ ቤቱ አድራሻ የተነፈ ደብዳቤ የጨረታ ማስከበሪያ ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ ኦርጅናል እና ኮፒ በተለያየ በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ አለባቸው የሚወዳደሩበትን በየሎቱ ለየብቻ በግልጽ ኤንቨሎፕ ላይ በመፃፍ እና የድርጅቱ ማኅተም እና ፊርማ በማድረግ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በወጣ በ11ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት የጨረታው ላጥን ተዘግቶ በዚያው እለት 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
- ተጫራቾች ናሙናቸውን ጨረታው ከመከፈቱ ከ 1ቀን በፊት ለሚጫረቱበት በሰነዱ ላይ ናሙና እንዲቀርብ ለተጠየቀባቸው እቃዎች በጨረታው ለመወዳደር ናሙና ማቅረብ አለባቸው ።
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነድ ላይ የተዘረዘሩት ዕቃዎች የእያንዳንዱን ነጠላ ዋጋ እና ድምር ዋጋ VAT ጭምሮ ማካተት ይኖርባቸዋል። ፍርድ ቤቱ ጨረታውን ለመገምገም የሚጠቀምባቸው መስፈርቶች ዕቃዎቹ ፍርድ ቤቱ ባስቀመጠው ስፔስፊኬሽን መሰረት ወይም በሚቀርበው ናሙና ጥራት፤ ዋስትና ፣ አነስተኛ ዋጋ እና አጠቃሎ የማቅረብ ጊዜ ግምት ውስጥ ይገባል።
- ፍርድ ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
- ሌሎች ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም።
- በየሎቱ የሚሳተፉ ተወዳዳሪ ድርጅቶች በዘርፉ የሚሰሩ ድርጅቶች ብቻ መሆን አለባቸው።
- ኮፒ እና ኦሪጅናል ኢንቨሎፕ በተናጠል (ለየብቻ) በፖስታ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- የሚወዳደሩበትን ሎት ለየብቻ ነጣጥለው በፖስታው ላይ ሎቱን በመፃፍ ማስገባት አለባቸው።
ከዚህ በላይ የተጠቀሱትን መስፋርት የማያሟሉ አቅራቢዎች ከጨረታው ውጪ የሚደረጉ ይሆናል
አድራሻ፡-
ልደታ ከፍለ ከተማ ወረዳ 10 ሜክሲኮ ፍሊፕስ ሕንጻ አጠገብ የአዲስ አበባ ፍትህ ቢሮ ሕንጻ 1ኛ ፎቅ ላይ አዲስ አበባ ከተማ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ቢሮ ቁጥር 102 ሲሆን ስልክ ቁጥር: 011 515 7040
አዲስ አበባ ከተማ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-10-21
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በወጣ በ11ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-10-21 10:30
- Bid opening (note): ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በወጣ በ11ኛው ቀን በ4፡30 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Addis Ababa City Administration Court of Appeals
- Buyer address: የአዲስ አበባ ፍትህ ቢሮ ህንፃ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 17
- Bid bond: ለእያንዳንዱ ሎት ከጠቅላላ ዋጋ 2%
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Oct 09, 2026)
- Posted at: 2026-10-09T08:06:56.000Z
- Source: Qelal Tenders