Equipment and Accessories

ጢስ እሳት ውሃ ስራዎች የኤሌክትሮ-ሜካኒካል እቃዎች (ፖምፕ እና አልትራ ሶኒክ ፊቲንግ)፣ የአካባቢ ግብአት (አሸዋ፣ ጠጠርና የግንባታ ድንጋይ)፣ የደንብ ልብስ፣ የተሽከርካሪና ማሽነሪ መለዋወጫ፣ የቧንቧ መገጣጠሚያ ፊቲንግ እና አሸዋና ግራቭል ማጓጓዝ እንዲሁም ተሽከርካሪና ማሽነሪዎችን ኪራይ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

ኩባንያችን ጢስ እሳት ውሃ ስራዎች የኤሌክትሮ-ሜካኒካል እቃዎች (ፖምፕ እና አልትራ ሶኒክ ፊቲንግ)፣ የአካባቢ ግብአት (አሸዋ፣ ጠጠርና የግንባታ ድንጋይ)፣ የደንብ ልብስ፣ የተሽከርካሪና ማሽነሪ መለዋወጫ፣የቧንቧ መገጣጠሚያ ፊቲንግ እና አሸዋና ግራቭል ማጓጓዝ እንዲሁም ተሸከርካሪና ማሽነሪዎችን ኪራይ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል።

ተ.ቁ

የእቃው አይነት

የጨረታ ማስከበሪያ

የማቅረቢያ ጊዜ

ሎት 1

የኤሌክትሮ ሜካኒካል እቃዎች (ፓምፕ እና አልትራ ሶኒክ ፊቲንግ)

200,000.00

ከ45-60 ቀናት

ሎት 2

የአካባቢ ግብአት (አሸዋ፣ ጠጠርና የግንባታ ድንጋይ)

300,000.00

የጨረታ ሰነዱ ላይ በተገለጸው መሰረት

ሎት 3

የደንብ ልብስ

50,000.00

ከ30-45 ቀናት

ሎት 4

የተሽከርካሪና ማሽነሪ መለዋወጫ

100,000.00

ከ45-60 ቀናት

ሎት 5

ተሽከርካሪና ማሽነሪዎች ኪራይ

የጨረታ ሰነዱ ላይ በተገለጸው መሰረት

የጨረታ ሰነዱ ላይ በተገለጸው መሰረት

ሎት 6

አሸዋና ግራቭል ማጓጓዝ

400,000.00

የጨረታ ሰነዱ ላይ በተገለጸው መሰረት

ሎት 7

የቧንቧ መገጣጠሚያ ፊቲንግ

100,000.00

ከ30-45 ቀናት

ስለዚህ ማንኛውም በዘርፉ የተሰማራና በጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ አቅራቢ ድርጅት ዝርዝር የጨረታ ሰነዱን በድርጅታችን ዌብ ሳይት www.tisisat.com  ማግኘት ይችላል።

የተጫራቾች መመሪያ፡-

  1. ተጫራቾች የዘመኑን ግብር ከፍለው የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ የምሰክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ እና የTIN ሰርተፊኬት፣ በዘርፉ ለመሰማራት የተሰጣቸውን ፈቃድ እና ተያያዥነት ያላቸውን ማስረጃዎች ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
  2. ጨረታው ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ21ኛው ቀን ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከቀኑ 9፡30 ሰዓት ባህርዳር ከተማ አባይ ማዶ ቴዲ የአሸከርካሪዎች ማሰልጠኛ ጎን በሚገኘው ዋናው መ/ቤት ተጫራቾች እና ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት ተዘግቶ ይከፈታል።
  3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በድርጅታችን ዌብ ሳይት www.tisisat.com ማግኘት ይችላሉ።
  4. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ በሰንጠረዥ የተመለከተውን ገንዘብ በCPO ወይም ያለቅድመ ሁኔታ እንደተጠየቀ ለገዥ የሚከፈል (unconditional Bank Guarantee) ማስያዝ አለባቸው።
  5. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያወጡት ወጪ በተጫራቹ የሚሸፈን ይሆናል።
  6. ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያቸውን እና ቴክኒካል ሰነዳቸውን ለየብቻ በተለያየ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ተጫራች ድርጅቶች ለሚያቀርቡት ዋጋ ለእያንዳንዱ እቃ ነጠላ ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ በትክክል ሞልተው በግልፅ ማስቀመጥ አለባቸው።
  7. ይህ ጨረታ በኩባንያችን የግዥ መመሪያ PRS-03/2017 መሰረት ተፈፃሚ ይሆናል።
  8. ኩባንያው በጨረታ ሰነዱ ላይ ከተገለፀው መጠን 20% ቢጨምር ወይም ቢቀንስ የጨረታ አሸናፊው ውል የመያዝ ግዴታ ይኖርበታል።
  9. የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ በጽሁፍ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ 05 ቀናት ውስጥ የጠቅላላ ዋጋውን 10 % የውል ማስከበሪያ ያለቅድመ ሁኔታ ለገዥ የሚከፈል (unconditional Bank Guarantee) በማሰራት ውል የመያዝ ግዴታ ይኖርበታል።
  10. የማቅረቢያ ጊዜ ከላይ በሰንጠረዡ ላይ በተገለፀው መሠረት መሆን አለበት፡፡ የአቅራቢዎች ዋጋ ቢያንስ ለ90 ቀናት ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ፀንቶ መቆየት አለበት።
  11. ኩባንያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ በዚህ ጨረታ አይገደድም ፤ወይም ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  12. ዕቃው ወይም አገልግሎቱ የሚቀርብበት ቦታ ባህር ዳር ከተማ የኩባንያው ጽ/ቤትና በጨረታ ሰነዱ ላይ በተገለጹ ቦታዎች መሆን አለበት።

ማሳሰቢያ፡- እንደ ኩባንያችን ፍላጎት ውድድሩ በሎት ወይም በእያንዳንዱ እቃ ነጠላ ዋጋ መሠረት ሊሆን ይችላል።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥራችን፡- 058-220-48-26 /058-320-25-48/ በፋክስ ቁጥራችን
058 220 4830 መጠየቅ ይችላሉ።
ጢስ እሳት ውሃ ስራዎች ኃ/የተ/የግ/ማህበር


Tender details

  • Deadline: 2026-10-29
  • Bid closing time: 15:00
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ21ኛው ቀን ከቀኑ 9፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-10-29 15:30
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ21ኛው ቀን ከቀኑ 9፡30 ሰዓት
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: Tis Esat Water Works P.L.C
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Published on: Addis Zemen (Oct 09, 2026)
  • Posted at: 2026-10-09T09:43:41.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders