Finishig Works

የቀይ ኮከብ ቅድመ አንደኛ፤ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት የጥገና የፓርትሽን ስራ ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ በማወዳደር ለማሰራት ይፈልጋል

Description

የጥገና ፓርትሽን የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 001/2019 ዓ.ም

ቀይ ኮከብ ቅድመ አንደኛ፤ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ሊያሰራው ለፈለገው ስራ በግንባታ ዘርፍ ላይ የሚሰሩ ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ በማወዳደር ለማሰራት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ለግንባታ አስፈላጊ የሆኑ ግብአቶችን ፣የሰው ሃይል በማቅረብ የሚሰሩ በጥቃቅን አነስተኛ ዘርፍ ማህበራት የተደረጁ ህጋዊ የሥራ ተቋራጮችን በግልጽ ጨረታ በማወዳደር ለማሰራት ይፈልጋል።

ተቁ

የስራው አይነት

የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና

ደረጃ

 

የጨረታ ሰነድ መሸጥ የሚጀመርበት ቀን

የጨረታ ማስገቢያ ቀን

የጨረታ መክፈቻ ቀን

 

1

የቀይ ኮከብ ቅድመ አንደኛ፤ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት የጥገና የፓርትሽን ስራ 

10.000 ብር/ከተደረጁበት ወረዳ የዋስትና ደብዳቤ

 

በጥቃቅንና አነስተኛ ታዳጊ እና መብቃት

 

ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት 2፡30-11፡30 ሰዓት

ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 4፡00 ድረስ ብቻ

ጋዜጣው ከወጣበት በ11ኛው የስራ ቀን ከ4፡30 ሰዓት ጀምሮ

 

ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ለመውሰድ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ህጋዊ ደክሜንታችሁን ዋናውንና አንድ ኮፒ ማቅረብ ይጠበቅባችኋል።

  1. በዘርፉ የ2018/2019 ዓ.ም የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው ፤የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤ ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑና የምዝገባ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉና በጨረታ መሳተፍ የሚያስችል ታክስ ክሊራንስ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
  2. ከመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ የተመዘገቡ ምስክር ወረቀት ያላቸው፤
  3. ማንኛውም ስራ ተቋራጭ ከፌዴራል ከተማ ልማት እና ኮንሰትራክሽን ሚኒስቴር የምስክር ወረቀት ያላቸው እና ከአዲስ አበባ ከተማ ግንባታ እና ፍቃድ ቁጥጥር ባለስልጣን ተመዝግቦ የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ሳይዝ በጨረታው መሳተፍ አይችልም።
  4. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በአየር ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት 2፡30 እስከ 11፡30 ድረስ ቀይ ኮከብ ቅድመ አንደኛ፤ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 03 ቀርበው ሠነዱን 200 ብር (ሁለት መቶ ብር) በመከፈል መውሰድ  ይችላሉ።
  5. ጨረታው የሚከፈተው በ11ኛው የሥራ ቀን በእለቱ ባለቤቱና ተጫራቾች ወይንም ሕጋዊ ወኪሎች በተገኙበት በት/ቤቱ ጠዋት 4፡00 ተዘግቶ በዕለቱ 4፡30 የሚከፈት ይሆናል።
  6. ማንኛውም ተጫራቾች ለ60 ቀናት የሚያገለግል የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና / BID BOND / በባንክ የክፍያ ትዕዛዝ (CPO) ወይም የባንክ ጋራንቲ (unConditional Bank Guarantee) ከላይ በተጠቀሰው የብር መጠን ማቅረብ ግዴታ አለበት፡፡ የቀረበው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ማቅረብ ያለበት በቴክኒካል ኦርጂናል ሰነድ ውስጥ ወይም ከፖስታው ውጪ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  7.  አሰሪው መ ቤት አሸናፊው ካለፈበት አጠቃላይ የስራ መጠን 20% መጨመርም ሆነ መቀነስ ይቻላል።
  8.  ተጫራቾች የጨረታ ሰነድን ከማስገባታቸው በፊት የተጫራቾችን መመሪያ (instruction to Bidder (TB) እንዲያነቡና የግንባታ ሳይቱን እንዲመለከቱ ይገደዳሉ።
  9. ተጫራቾት ቴክኒካል ሰነድ አንድ ኦሪጅናል እና ሁለት ኮፒ፤ ፋይናንሺያል ሰነድ አንድ ኦርጅናልና ሁለት ኮፒ በድምሩ ስድስት ሰነድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ በተጨማሪም የታሸገውን ፖስታ በእንድ እናት ፖስታ የድርጅቱን ማህተም እና የሚወዳደሩበትን የስራ ፕሮጀክት አይነት ስም በመጻፍ ታሽጎ መቅረብ ይኖርበታል፡፡ እንዲሁም የጨረታው ፋይናንሻል ሰነድ ላይ ያልተፈረመ ሆኖ ስርዝ ድልዝና በፍሉድ የተስተካከለ ዋጋ ከሆነ ሙሉ ለሙሉ ከጨረታው ያሰርዛል፡፡ በተጨማሪም በስራ ዝርዝር በሙሉም ሆነ በአንድ የስራ አይተም ላይ ዋጋ አለመሙላት ከተገኘ ስራውን በነጻ እንደሚሰራ ይወሰዳል።
  10. ተጫራቾች የሥራዎችን የዋጋ ዝርዝር እና የጨረታ መወዳደሪያ ላይ ስማቸውን፣ ፊርማቸውን፣ አድራሻቸውን ማስፈር ማህተም ማድረግ ኢንቨሎፑን በማሸግማስታወቂያው በወጣበት በ11ኛው የስራ ቀን የቀይ ኮኮብ ቅድመ አንደኛ፤ አንደኛ መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ስራ ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 08 በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ እሰከ 4፡00 ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  11. ተጫራቾች ከዚህ በፊት ት/ቤቱ ባስገነባቸው ግንባታዎችም ሆነ እድሳቶች ምንም አይነት ውል ያላቋረጡ መሆን ይጠበቅባቸዋል።
  12. አሸናፊ ተጫራች በስራ ዝርዝር ላይ ከገበያ ዋጋ በጣም ከፍ ያለ እና ዝቅ ያለ ዋጋ ከሞላ (Cost Break Down) ያቀርባል።
  13. ተጫራቾች የሚያቀርቡት የድርጅቱ የስራ ልምድና ማንኛውም በቴክኒካል የተጠየቁት ዶክመንቶችን አሰሪ መ/ቤት ኦርጂናል ዶክመንት ከሰጠው አካል የማጣራት መብት የተጠበቀ ነው።
  14. ጨረታውን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ማስታወቂያው በወጣበት በ11ኛው ተከታታይ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ጀምሮ የቀይ ኮከብ ቅድመአንደኛ፤ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ቁጥር 08 ይከፈታል፡፡ የጨረታው መክፈቻ ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም በበዓል ቀን ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት እና ቦታ የሚከፈት ይሆናል።
  15. ት/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  16. ተጨማሪ ማብራሪያና አድራሻ፡- ቀይ ኮከብ ቅደመ አንደኛ፣ አንደኛና መካከለኛ ደ/ት/ቤት ልዩ ስሙ ጣሊያን ሰፈር ወይም ከዮሃንስ ቤተክርስትያን ወደ ጎጃም በረንዳ በሚወስደው መንገድ አራት መንታ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው።

ለበለጠ መረጃ በት/ቤቱ ስልክ ቁጥር 011-1-71-50-64 ደውለው ይጠይቁ

በአራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 02 የቀይ ኮከብ ቅድመ አንደኛ፤ አንደኛና መካከለኛ ደ/ት/ቤት

የቀይ ኮከብ ቅድመ አንደኛ፤ አንደኛና መካክለኛ ደ/ት/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-10-22
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 4፡00 ድረስ
  • Bid opening: 2026-10-22 10:30
  • Bid opening (note): ጋዜጣው ከወጣበት በ11ኛው የስራ ቀን ከ4፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Key Kokob Kindergarten and Elementary School
  • Buyer address: ልዩ ስሙ ጣሊያን ሰፈር ወይም ከዮሐንስ ቤተክርስቲያን ወደ ጎጃም በረንዳ በሚወስደው መንገድ አራት መንታ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው
  • Bid bond: 10,000 ብር/ ከተደራጁበት ወረዳ የዋስትና ደብዳቤ
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Oct 10, 2026)
  • Posted at: 2026-10-10T07:57:58.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders