Vehicle (garage service)

በድሬዳዋ አስተዳደር የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ በ 2019 ዓ.ም. ከመንግስት በተመደበ በጀት በአንድ አመት የሚቆይ የማዕቀፍ ውል የተሽከርካሪ ጥገና፣ የተለያዩ ህትመት አገልግሎት፣ የዲኮር መድረክ ሽብርቅ እንዲሁም ለአንድ ጊዜ ጨረታ የሚሆን የሚዲያ ኤሌክትሮኒክ መሣርያዎች ግዢ ለመፈጸም የአካባቢያዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨ/መ/ቁ/መ/ኮ 01/ 2019

በድሬዳዋ አስተዳደር የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ በ 2019.ም ከመንግስት በተመደበ በጀት በአንድ አመት የሚቆይ የማዕቀፍ ውል በሎት 1. የተሽከርካሪ ጥገና በሎት 2. የተለያዩ ህትመት አገልግሎት ሎት 3. የዲኮር መድረክ ሽብርቅ እንዲሁም ለአንድ ጊዜ ጨረታ በ ሎት 4.የሚዲያ ኤሌክትሮኒክ መሣርያዎች ግዢ ለመፈጸም የአካባቢያዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡-

በመሆኑም፦

1. ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፍቃድና በመንግስት የእቃና አገልግሎት አቅሪቢዎች ዝርዝር ዉስጥ ተመዝግበው የምስክር ወረቀት ያላቸው መሆን አለባቸው፡ ፡

2. የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።

3. የዘመኑን ግብር የከፈሉና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው::

4. ተጫራቾች ለተወዳደሩበት ጨረታ አባባብነት ያለው የተሟላ ሰነድ ማቅረብ አለባቸው።

5.ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ጨረታው ከወጣበት እለት ጀምሮ ጨረታው እስከሚታሽግበት እለትና ሰዓት ቀደም ብሎ የጨረታ ሰነዱን በቢሮው የፋይናንስና ግዢ ንብረት አስተዳደር ዳሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 201 ቀርበው የማይመለስ 100 (አንድ መቶ ብር ብቻ) በመከፈል መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን ተጫራቾች አስፈላጊውን ዋጋ በግልፅ የተጨማሪ እሴት እሴት ታክስን ያካተተ ወይም ያላካተተ መሆን በመሙላት ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዋናውንና ኮፒውን በአግባቡ በማሸግ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

6. የጨረታ ሳጥኑ ጥቅምት 11/ 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጐ በዚሁ ዕለት ጠዋት 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተኙበት በዳሬክቶሬቱ ቢሮ በግልፅ ይከፈታል።

7. የሎት አንድ ተጫራቾች ብር 5000(አምስት ሺብር ብቻ) ፣የሎት ሁለት ተጫራቾች ብር 10000(አስር ሺብር ብቻ)፣የሎት ሶስት ተጫራቾች ብር 5000(አስር ሺብር ብቻ)፣ሎት 4 ተጫራቾች 20,000 ጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ቼክ፣ በጥሬ ገንዘብ፣ በባንክ ዋስትና፣ በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት እንዲሁም ሲፒኦ ከነዚህ አማራጮች ውስጥ በአንዱ በመጠቀም ለብቻው በፖስታ በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

8. ቢሮው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መፍቱ የተጠበቀ ነው።

9. ተጨማሪ ማብራሪያና መረጃ ቢያስፈልግ በሚከተለው አድራሻ መጠቀም ይችላሉ።

የ ድ/ዳ / አስተዳደር መንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ

የስልክ ቁጥር፦ 0251-11-60-61

ሞባይል ስልክ፦ 09-48-59-70-11

ፊክስ ቁጥር፦025 111 4972

ድሬዳዋ


Tender details

  • Deadline: 2026-10-21
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-10-21 10:30
  • Region: Dire Dawa
  • Publishing entity: Dire Dawa Administration Government Communication Affairs Bureau
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 100.00 ብር
  • Published on: Melekite Dire (Oct 07, 2026)
  • Posted at: 2026-10-10T08:03:31.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders