Stationery
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የመርካቶ ቁጥር 2 የህግ ተገዥነት ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ ቋሚ እና አላቂ የቢሮ ንብረቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
More tags
Description
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር 001/2019 ዓ.ም
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የመርካቶ ቁጥር 2 የህግ ተገዥነት ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ ቋሚ እና አላቂ የቢሮ ንብረቶችን ማለትም
- ሎት 1 የተለያዩ የደንብ ልብስ፣
- ሎት 2 የተለያዩ የፅህፈት መሳሪያዎች፣
- ሎት 3 የተለያዩ የህትመት ውጤቶች፣
- ሎት 4 የተለያዩ የፅዳት እቃዎች፣
- ሎት 5 የተለያዩ ቋሚ አላቂ የቢሮ እቃዎች፣
- ሎት 6 የተለያዩ የመኪና መለዋወጫ እቃዎች፣
- ሎት 7 የተለያዩ የቢሮ የፈርኒቸር እና አልሙንየም የጥገና መለዋወጫ እቃዎች እና የቢሮ ፓርትሽን ስራ፣
- ሎት 8 ቋሚ የአይቲ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣
- ሎት 9 ቋሚ የቢሮ እቃዎች፣ የምንጣፍ ማጠብ እና የመጋረጃ ስራ፣
- ሎት 10 የታሸገ ውሃ አቅርቦት እና
- ሎት 11 የኮምፒዩተር፣ የላፕቶፕ፣ የፎቶ ኮፒ፣ የፕሪንተር እና የፓወር ማቆያ ዩፒሰ/ የመለዋወጫ እና የጥገና እቃዎች የሚሰጥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ህጋዊ መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል።
1. የዘመኑን ግብር የከፈሉበት ክሊራንስ፣ ጨረታ ላይ እንዲሳተፉ የሚያስችል ደብደቤ፣ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ተመዝጋቢ የሆኑ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ሠርተፍኬት እንዲሁም የግብር ከፋይ መለያ ሠርተፍኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
2. ተጫራቾች ለጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 400.00 /አራት መቶ ብር/ በመክፈል ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ቅዳሜን ሙሉ ቀን ጨምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ልደታ መናፈሻ ፊት ለፊት በላይ ተክሉ ኬክ ቤት ጎን በሚገኘው ዊዝደም የገበያ ማዕከል አክሲዮን ማህበር መርካቶ ቁጥር 2 የህግ ተገዥነት ቅ/ጽ/ቤት ህንፃ ላይ 7ተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 705/704 የግዥ አገልግሎት ቡድን በአካል በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን በጥሬ ገንዘብ መግዛት ይችላሉ።
3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሁሉም ዓይነት እቃዎች 10,000.00 (አስር ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ(C.PO.) ብቻ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ መርካቶ ቁጥር 2 የህግ ተገዥነት ቅ/ጽ/ቤት (Addis Ababa City Administration Revenues Bureau Merkato No2 Law Enforcement Branch Office) በሚል ስም በማሰራት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
4. የጥቃቅንና አነስተኛ ተጫራቾች ለሆኑት ከአደራጅ መስሪያቤት የጨረታ መወዳደሪያ ዋስትና ደብዳቤ ማጻፍ እና ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
5. ዋጋ ያልተሞላበት የመወዳደሪያ ሰነድ ላይ የምትወዳደሩበትን እቃዎችን/አገልገሎቶች ብቻ በመለየት የዋጋ ማወዳደሪያ ሰንጠረዥ ላይ በማክበብ ወይም ምልክት በማድረግ ኦርጂናሉን እና ኮፒውን (ዋናውን እና ቅጅውን) ከቴክኒክ ሰነዶች ጋር አብሮ መያያዝ አለበት።
6. የፋይናንሻል ወይም የዋጋ ማወዳደሪያ ሰንጠረዥ ዋጋው ከነቫቱ ተሞልቶ ብቻውን በኦርጅናል እና ኮፒ (ዋናውና ቅጅ) ለየብቻው ታሽጎ መቅረብ ይኖርበታል።
7. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ሰነድ በድምሩ በአራት ኤንቨሎፕ ኦርጂናልና ኮፒውን ወይም(ዋናውንና ቅጂውን) ለየብቻ በሰም ወይም በሌላ ማጣበቂያ በማሸግ በመ/ቤታችን በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ የጨረታ ማስታወቂያው አየር ላይ ከዋለበት ቀን እስከ 10ኛው የስራ ቀን ቅዳሜን ጨምሮ እስከ ጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
8. ተጫራቾች በተሳተፉበት አቅርቦት ላይ ለመ/ቤቱ ኮሚቴዎች ሳምፕል ማቅረብ ማለትም የፅህፈት መሳሪያዎች፣ የፅዳት እቃዎች፣ የደንብ ልብስ፣ የህትመት ውጤቶች፣ የመኪና እቃዎች እና ለሌሎች ናሙና ለተጠየቀባቸው ፍላጎቶች ሁሉ ሳምፕል ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል። እንዲሁም በቀላሉ ለማንቀሳቀስ የማይችሉ ልዩ ልዩ ቋሚ እቃዎች ናሙና ለመስሪያ ቤታችን የቴክኒክ ኮሚቴዎች በተጫራቾች ድርጅት ውስጥ በአካል ለማሰያት ፍቃደኛ መሆን ይጠበቅበታል።
9. የጨረታ ሣጥኑ ጨረታው በወጣበት በ10ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጽ/ቤታችን የመሰብሰቢያ አዳረሽ ውስጥ ይከፈታል። ሆኖም ጨረታ የሚከፈትበት ቀን አመት በዓል ከሆነ በሚቀጥለው ቀን 4፡30 ይከፈታል።
10. አንድ ተጫራች ሌላው በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም፡፡
11. ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
12. የጨረታ ሳጥኑ ከተዘጋ በኋላ ዘግይቶ የሚቀርብ የመጫረቻ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም።
13. እኩል ውጤት ያገኙ ተጫራቾች ተጨማሪ የማወዳደሪያ ሃሳብ እንዲያቀርቡ ይደረጋል፤ ለሶስተኛ ጊዜ እኩል ከሆኑ በእጣ እንዲለዩ ይደረጋል።
14. የጨረታ መገምገሚያ ዘዴዎች በጨረታ ሰነዱ ውስጥ በክፍል ሶስት እና ክፍል ስድስት በተጠቀሱት መሰረት ብቻ ይሆናል።
15. ተጫራቾች ሁሉንም የመወዳደሪያ ሰነዶች ህጋዊ ስልጣን ባለው አካል ተፈርሞባቸውና የድርጅታቸውን ማህተም አርፎባቸው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
16. የጨረታ ዋጋ ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ60 ቀን እና ለተጨማሪ 28 ቀን የሚቆይ ይሆናል።
17. መስሪያ ቤታችን ከአሸናፊ ድርጅቶች ጋር በጨረታ ሰነዱ ከተገለጸው የአቅርቦት መጠን ላይ ምንም የዋጋ ልዩነት ሳይኖር እስከ 20% ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል።
ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 0112769862/0112732771 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የመርካቶ ቁጥር 2 የህግ ተገዢነት ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-10-21
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-10-21 10:30
- Bid opening (note): ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Ministry of Revenue
- Buyer address: የቀድሞ ቡና ቦርድ ከንፋስ ስልክ ት/ቤት ዝቅ ብሎ ባለው ሙለጌ ህንፃ ላይ
- Bid bond: 10,000.00 (አስር ሺ ብር)
- Bid document price: 400.00 /አራት መቶ ብር/
- Published on: Addis Zemen (Oct 10, 2026)
- Posted at: 2026-10-10T08:32:01.000Z
- Source: Qelal Tenders