Cleaning and Janitorial Equipment and Service

በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የወረዳ 4 ፋይናንስ ፅ/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውል የተለያዩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

ግልፅ ጥቅል ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 002/2019

በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የወረዳ 4 ፋይናንስ ፅ/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውል ሎት 1 የደንብ ልብስ ሎት 2 የጽህፈት መሳሪያዎች ሎት 3 የፅዳት እቃዎች ሎት 4 የቢሮ አላቂ ዕቃዎች ሎት 5 የቢሮ ቋሚ እቃዎች (ኤሌክትሮኒክስ እና ፈርኒቸር) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ።

1. በዘመኑ በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው

2. የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ።

3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) እና ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።

4. በሀገር ውስጥ የተሰማሩ መሆናቸውን የሚገልጽ በቂ ማስረጃ ለሚያቀርቡ የጥቃቅን እና አነስተኛ ማኅበራት ብቻ ልዩ አስተያየት የሚደረግ ሲሆን ማቅረብ ለማይችሉ የበጀት ዓመቱን የግብር ግዴታቸውን የተወጡ መሆን ይኖርባቸዋል።

5. ሆናቸው ማስረጃ ከ (EGP WWW.PPA.GOV.ET ) ፕሪንት አድርገው ማቅረብ የሚችሉ ከላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ እና እንዲሁም ናሙና ለሚጠይቁ እቃዎች ከመጫረቻ ሰነድ ጋር ናሙና ማቅረብ የሚችሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ።

6. ናሙና (Sample) ለተጠየቀባቸው እቃዎች የመጫረቻ ሰነድ በሚያስገቡበት እለት ናሙና ማቅረብ የሚችሉ።

7. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት እቃ ለሎት አንድ (1) የደንብ ልብስ ብር 50,000፣

ለሎት ሁለት (2) የፅህፈት መሳሪያዎች ብር 40,000፤

ለሎት ሶስት (3) የዕዳት እቃዎች ብር 60,000፤

ለሎት አራት (4) የቢሮ አላቂ ዕቃዎች ብር 10,000፤

ለሎት አምስት (5) የቢሮ ቋሚ እቃዎች (ኤለክትሮኒክስ እና ፈርኒቸር) 100,000 የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ ትእዛዝ (CPO) ብቻ ማቅረብ አለባቸው።

8. አሸናፊ የሚሆኑ ተጫራቾች የውል ማስከበሪያ 10% ማስያዝ የሚችሉ።

9. የጨረታ ሰነድ ሽያጭ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስር (10) ተከታታይ የስራ ቀናት የሚቆይ ሆኖ ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሠዓት ተከፍቶ በእለቱ ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ታዛቢዎች ባሉበት የሚከፈት ይሆናል።

10. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን አንደኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 106 በመቅረብ የማይመለስ ብር አራት መቶ (400) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።

11. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋናውንና ኮፒውን እንዲሁም የቴክኒክ ሰነዶችን በታሸገ ኢንቨሎፕ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10 ተከታታይ የስራ ቀናት በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ማንኛውም አቅራቢ የሚሞላው ሰነድ ላይ ስርዝ ድልዝ ካለው ወይም ለማንበብ አስቸጋሪ ሆኖ ከተገኘ ከውድድር ውጪ ይሆናል።

መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ- 09 55 37 36 36 በመደወል ማግኘት ይቻላል።

facebook page Akaki kality woreda 4 communication

በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የወረዳ 04 ፋይናንስ ፅ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-10-22
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስር (10) ተከታታይ የስራ ቀናት የሚቆይ ሆኖ ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሠዓት
  • Bid opening: 2026-10-22 10:30
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስር (10) ተከታታይ የስራ ቀናት የሚቆይ ሆኖ ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሠዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Akaki Kality Sub City Woreda 4 Finance and Economic Development Bureau
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 400.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Oct 10, 2026)
  • Posted at: 2026-10-10T08:59:18.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders