Cleaning and Janitorial Equipment and Service
በጉለሌ ክ/ከተማ አዲስ አበበ ቁ.1 የመ/ደ/ት/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት በመደበኛ፣ ድጎማ እና በውስጥ ገቢ በጀት የሚያገለግሉ ልዩ ልዩ እቃዎችን እና አገልግሎቶችን በመጀመሪያ ዙር ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
More tags
Description
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 001/2019
በጉለሌ ክ/ከተማ አዲስ አበበ ቁ.1 የመ/ደ/ት/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት በመደበኛ፣ ድጎማ እና በውስጥ ገቢ በጀት የሚያገለግሉ ልዩ ልዩ እቃዎችን እና አገልግሎቶችን በመጀመሪያ ዙር ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
1. ሎት 1 የፅህፈት መሳሪያ
2. ሎት 2 የደንብ ልብስ
3. ሎት 3 የደንብ ልብስ ማሰፊያ
4. ሎት 4 አጋዥ መፅሀፍት
5. ሎት 5 ልዩ ልዩ የመገልገያ እቃዎች
6. ሎት 6 የፅዳት እቃዎች
7. ሎት 7 የኤሌክትሪከ እቃዎች
8. ሎት 8 የኮምፒውተርና፣ፐሪንተር ጥገና
9. ሎት 9 የህትመት ስራዎች
10. ሎት 10 ቋሚ እቃዎች
11. ሎት 11 የጥገና ሥራ
12. ሎት 12 የካፌ አገልግሎት ግዥ
13.ሎት 13 የጭነት አገልግሎት እና
14.ሎት 14 የአላቂ የትምህርት እቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛትና ማሠራት ይፈልጋል።
በመሆኑም ከዚህ በታች ያለውን መስፈርት የምታሟሉ አመልካቾች መወዳደር ትችላላችሁ።
1. የንግድ ምዝገባ፣በዘርፉ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ መለያ ቁጥር (TIN) የ2018 ዓ.ም የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላችሁና የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT 15%/ ተመዝጋቢ የሆናችሁ።
2. ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው እቃዎች እና አገልግሎቶች ዋጋውን ከነቫቱ መሙላት ይኖርባቸዋል።
3. ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው እቃዎች የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
4. ተወዳዳሪዎች ለሚወዳደሩባቸው አቅርቦቶች ናሙና ማቅረብ የሚችሉ።
5. አንዱ በሌላው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም።
6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለሎት 1 ብር 10,000 /አስር ሺህ/
ለሎት 2 ብር 12,000.00 /አስራ ሁለት ሺህ ብር/
ለሎት 3 ብር 2,000.00 /ሁለት ሺህ ብር /
ለሎት 4 ብር 5,000.00 /አምስት ሺህ ብር /
ለሎት 5 ብር 2,000.00 /ሁለት ሺህ ብር/
ለሎት 6 ብር 5,000.00 /አምስት ሺህ/
ለሎት 7 ብር 1,000.00 ብር /አንድ ሺህ /
ለሎት 8 ብር 1,000.00 /አንድ ሺህ ብር/
ለሎት 9 ብር 12,000.00 /አስራ ሁለት ሺህ ብር/
ለሎት 10 ብር 12,000.00 /አስራ ሁለት ሺህ ብር/
ለሎት 11 ለሎት ብር 12,000.00 /አስራ ሁለት ሺህ ብር/ 13 እና ለሎት ብር 5,000.00 ብር /አምስት ሺህ/ በባንክ ሲፒኦ ማስያዝ አለባቸው። እንዲሁም ጥቃቅንና አነስተኛ ከሆነ ልዩ አስተያየት የሚኖረው አምራች በሆኑበት እቃዎች ላይ ብቻ ከአደራጃችሁ አካል የዋስትና ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው የመንግስት የስራ ቀን ድረስ ከቢሮ ቁጥር 5 ግዥ ክፍል በመምጣት በመንግስት የስራ ሰዓት ለእያንዳንዱ የጨረታ አይነቶች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ዋጋ በማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።
8. ተጫራቾች ሰነዱን በመሙላት ኦርጂናል የፋይናንሺያል ና የቴክኒኩን በአንድ ፖስታ እና ኮፒውን በሁለት ፖስታ በማሸግ እስከ 10ኛው የመንግስት የስራ ቀን ከቀኑ 11፡30 ሰዓት ድረስ በመንግስት የስራ ሰዓት በጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ወረዳ አድሰ አበበ ቁ.1 የመ/ደ/ት/ቤት በቢሮ ቁጥር 5 ፋይናንስ ክፍል ውስጥ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
9. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በ10ኛው ቀን 11፡30 ሠዓት ላይ ታሽጎ በ11ኛው ቀን ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 3፡30 ላይ በቢሮ ቁጥር 5 ፋይናንስ ክፍል ውስጥ ይከፈታል።
10. አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈባቸውን እቃዎች በራሱ ትራንስፖርት አዲስ አበበ ቁ.1 የመ/ደ/ት/ቤት ንብረት ክፍል ድረስ ማቅረብ አለባቸው።
11. መስሪያ ቤቱ በጨረታው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
12. ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን እቃዎች ናሙናዎችን ቀድመው ማስገባት ይጠበቅባቸዋል።
13. መስሪያ ቤቱ አሸናፊ ተጫራቾች ከመረጠ በኃላ ለሚገዙት እቃዎች ብዛት መጠን ላይ እንደ አስፈላጊነቱ እስከ 20% የመቀነስ ወይም የመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው።
14. ተጫራቾች ጨረታው ከተከፈተ በኃላ ባቀረቡት ዋጋ ላይ የዋጋ ለውጥም ሆነ ማሻሻያ ማድረግ አይችሉም በተወዳደሩበት ዋጋ አሸናፊነታቸው ከተገለፀላቸው ከ7(ሰባት) የቅሬታ ቀን በኃላ ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 5 ቀርበው የውል ማስከበሪያ 10% ለግዥ ፈፃሚው አካል ማስያዝ ውል መዋዋል ይኖርባቸዋል። ያስያዙት ገንዘብ ተመላሽ የሚሆነው በውሉ መሰረት የሚጠበቅባቸውን ግዴታ ከተወጡ ያስዙት የውል ማስከበሪያ ተመላሽ የሚደረግ ይሆናል።
አድራሻችን፡- ጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 እንቁላል ፈብሪካ ወደ አስኮ በሚወስደው መንገድ እስላም መቃብር ፊት ለፊት ይገኛል
ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 011 273 7297 / 011 230 6069
በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ትምህርት ፅ/ቤት የአዲስ አበበ ቁ.1 አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-10-21
- Bid closing time: 17:30
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው ቀን በ11፡30 ሠዓት
- Bid opening: 2026-10-22 09:30
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን በ3፡30 ሠዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ትምህርት ፅ/ቤት የአዲስ አበበ ቁ.1 አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Oct 10, 2026)
- Posted at: 2026-10-10T09:04:11.000Z
- Source: Qelal Tenders