Cleaning and Janitorial Equipment and Service
በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የፋና 02 ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ለ2019 ዓ/ም በጀት ዓመት የሚያስፈልጉ እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
More tags
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የፋና 02 ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ለ2019 ዓ/ም በጀት ዓመት የሚያስፈልጉ እቃዎችን ማለትም በየሎታቸው የተቀመጡት ሎት 01 የደንብ ልብሶች፣ ሎት 02 አላቂ የቢሮ እቃዎች፣ ሎት 03 አላቂ የትምህርት እቃዎች፣ ሎት 04 የፅዳት እቃዎች፣ ሎት 05 ሌሎች መሣሪያዎች፣ ሎት 06 ቋሚ እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ለሎት 01 የጨረታ ማስከበሪያ ብር 20,000.00 /ሃያ ሽህ ብር ብቻ/ ለሎት 02 የጨረታ ማስከበሪያ ብር 8,000.00 /ስምንት ሽህ ብር ብቻ/ ለሎት 03 የጨረታ ማስከበሪያ ብር 5,000.00 /አምስት ሽህ ብር ብቻ/ ለሎት 04 የጨረታ ማስከበሪያ ብር 8,000.00 /ስምንት ሺህ ብር ብቻ/ ለሎት 05 የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000 /አስር ሽህ ብር ብቻ/ ለሎት 06 የጨረታ ማስከበሪያ 20,000.00 /ሃያ ሺህ ብር ብቻ/ በባንክ በተረጋገጠ ሰነድ (CPO) ከጨረታው ሰነድ ጋር በፖስታ በማሸግ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
በዚህ መሠረት ተጫራቾች የሚከተሉት ቅድመ ሁኔታዎች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡
1. በጨረታው ለመወዳደር ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾችን የታደሰ የንግድ ፈቃድና የዘመኑ ግብር የከፈሉ ለዚህም ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
2. በመንግሥት ግዥ ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ በዕቃ አቅራቢነት የተመዘገቡ መሆን ይኖርበታል፡፡
3. ተጨማሪ እሴት ታከስ ተመዝጋቢ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡ የግብር ከፋይ መለያ (Tin) ቁጥር ሊኖራቸው ይገባል፡፡
4. ተጫራቾች የጨረታ ሳጥን ከመከፈቱ በፊት ለተወዳደሩባቸው ለእያንዳንዱ ለአላቂም ለቋሚም ዕቃ ናሙና ማቅረብ አለባቸው፡፡ ማለትም ለቋሚ እቃዎች በት/ቤቱ ፍላጎት መግለጫ መሠረት ብቻ ይሆናል።
5. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ታትሞ አየር ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት የማይመለስ 200.00/ሁለት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን በክ/ሂ/ግ/ን/አስ እና ጠ/አገ ደጋፊ የሥራ ሂደት ቢሮ በት/ቤቱ በመውሰድ ይችላሉ፡፡
6. ተጫራቾች ቦሚጫረቱበት ዋጋ በገዙት ሰነድ ላይ ባለው የዋጋ ማቅረቢያ ለእያንዳንዱ እቃዎች ቫት አካቶ ያለውን ዋጋ በግልፅ በመሙላት በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ ከላይ በተጠቀሰው የሥራ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት ቢሮ ቁጥር 04 በዚህ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
7. ጥቃቅን እና አነስተኛ ተጫራቾች አምራችነታችሁን የሚገልፅ ደብዳቤ ይዛችሁ መገኘት ይኖርባችኋል፡፡
8. ጨረታው በጋዜጣ ታትሞ አየር ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው ቀን 11 ሰዓት ድረስ አየር ላይ ውሎ ይዘጋ እና በ11ኛው የሥራ ቀን በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በት/ቤቱ ፋይናንስ እና ግዥ ቡድን መሪ ቢሮ ይከፈታል፡፡
9. ትምህርት ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
10. የዘገየ ጨረታ እና በጨረታ መክፈቻ ሳይ ያልተነበበ ጨረታ ተቀባይነት የለውም። በተጨማሪም አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ግዥ ፈጻሚው መሥሪያ ቤት ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
አድራሻ፡- ወደ ጀሞ በሚያስኬደው መንገድ ከአንበሳ ጋራዥ አስፍ ብሎ በናሰው ሪልስቴት በአዲሱ መንገድ 300ሜትር ገባ ብሎ
ለበለጠ መረጃ፡- 0967 195 217
በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ፋና 02 ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-10-21
- Bid closing time: 17:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ታትሞ አየር ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ቆይቶ በ10ኛው ቀን 11 ሰዓት
- Bid opening: 2026-10-22 10:30
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ታትሞ አየር ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ቆይቶ በ11ኛው የሥራ ቀን በ4፡30 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Fana 02 Secondary School
- Buyer address: ከአንበሳ ጋራዥ አለፍ ብሎ በናሰው ሪል እስቴት 300 ሜትር ገባ ብሎ
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Oct 10, 2026)
- Posted at: 2026-10-10T09:13:06.000Z
- Source: Qelal Tenders