Food Items and Drinks
በኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን ምርጥ ዘር አቅርቦት ዘርፍ በአርዳይታ፣ በኮፈሌ፣ በሀዋሳ፣ ቦንጋ፣ ነቀምት፣ ባህርዳር እና አሰላ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ላይ የሚገኘውን የምግብ እህል እና የብጣሪ እህል በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል
Description
የምግብ እህልና የብጣሪ እህል ለመሸጥ የወጣ
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ኢግስኮ-ምዘአዘ/ጨሽ/02ሠነድ/2019
በኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን ምርጥ ዘር አቅርቦት ዘርፍ በአርዳይታ፣ በኮፈሌ፣ በሀዋሳ፣ ቦንጋ፣ ነቀምት፣ ባህርዳር እና አሰላ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ላይ የሚገኘውን የምግብ እህል እና የብጣሪ እህል በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ስለሚፈልግ፡-
1. ማንኛውም ተጫራች በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው እና የዘመኑን የመንግስት ግብር የከፈሉ።
2. ማንኛውም ተጫራች የሚጫረቅበትን ጠቅላላ ዋጋ 2% በምርጥ ዘር አቅርቦት ዘርፍ (Seed Supply Sector) ስም የጨረታ ማስከበሪያ (Bid BOND) በባንክ የተረጋገጠ CPO ወይም የባንክ ጋራንቲ ዋስትና ማስያዝ አለበት።
3 ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ከላይ በተጠቀሱት ቅርንጫፍ ጽ ቤቶች ወይም ከአዲስ አበባ ዋናው መ/ቤት የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ።
4. ማንኛውም ተጫራች የተገለፀውን መጠን የምግብ እህል እና የብጣሪ እህል መጫረት ይችላል።
5. ማንኛውም ተጫራች የምግብ እህሉ እና የብጣሪ እህሉ በሚገኙበት ቅጽ ቤቶች በመገኘት አይቶ መጫረት አለበት። ይህን ሳያደርግ ዋጋ ቢያቀርብ ኃላፊነቱ የተጫራቹ ይሆናል።
6. ማንኛውም ተጫራች የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ የሚጠይቀውን በሙሉ አሟልቶ ማቅረብ ይጠበቅበታል።
7. ማንኛውም ተጫራች በሌላ ተጫራች ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም።
8. የምግብ እህልና የብጣሪ አህል መጠን በዚህ ጨረታ ሰነድ ላይ ከተገለፀው መጠን ሊያንስ ይችላል።
9. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ የምግብ እህል እና የብጣሪ እህል ዓይነት የሚሰጠውን ዋጋ በኢንቬሎፕ በማሸግ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጥቅምት 17 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት አለበት። ጨረታው ጥቅምት 17/2019 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ጥቅምት 17 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ በ8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዘርፉ ጽ ቤት እና ከላይ በተጠቀሱት ቅ/ጽ/ቤቶች ጨረታው ይከፈታል።
10.ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ምርጥ ዘር አቅርቦት ዘርፍ
ስልክ 09-11-31-35-79
አዲስ አበባ
የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን ምርጥ ዘር አቅርቦት ዘርፍ
Tender details
- Deadline: 2026-10-27
- Bid closing time: 14:00
- Bid opening: 2026-10-27 14:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Ethiopian Seed Enterprise
- Buyer address: Marketing Department Addis Ababa, Ethiopia
- Bid bond: 2%
- Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
- Published on: Addis Zemen (Oct 11, 2026)
- Posted at: 2026-10-12T06:44:26.000Z
- Source: Qelal Tenders