Cleaning and Janitorial Equipment and Service
በድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ የዶ/አቤል መልካሙ መታሰብያ ጤና ጣቢያ የቢሮ የጽህፈት መሣሪያዎች፣ የተለያዩ የጽዳት ዕቃዎች፣ ህትመት መግዛት ይፈልጋል
Description
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ዶ/ር/አ/መ/መ/ጤ/ ጣ
በድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ የዶ/አቤል መልካሙ መታሰብያ ጤና ጣቢያ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ግዢዎችን ለመፈፀምአቅራቢ ድርጅቶችን በጨረታ እንዲሳተፉ ይጋብዛል።
በዚሁ መሠረት በጨረታው ላይ ለመካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች፡-
- ሎት 1 -የቢሮ የጽህፈት መሣሪያዎች
- ሎት 2 -የተለያዩ የጽዳት ዕቃዎች
- ሎ ት 3 ህትመት
1. ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ በተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ እና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
1.2. በመንግስት ግዢ አቅራቢ የተመዘገቡና የተመዘገቡበትን ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
1.3. ተጫራቾች የታክስ መለያ ቁጥር (TIN No) ያላቸው መሆን ይኖርባቸዋል።
1.4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል በዶ/አቤል መልካሙ መታሰብያ ጤና ጣቢያ በግ/ፋ/ንብ/አስ/ድ የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 12 በመቅረብ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
1.5. መስፈርቱን የሚያሟሉ ተጫራቾች ለጨረታ ማሰከበሪያ የሚሆን ለያንዳንዱ ሎት ብር 10000.00 /አስር ሺህ ብር/ ለጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተመሰከረለት ቼክ ወይም /CPO/ወይም (Bl BOND) ከጨረታው ኦርጅናል ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
1.6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ መቀበያ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
1.7. የጨረታ ሰነዱ የሚከፈትበት ቀን ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ከቆየ በኃላ በ16ኛው ቀን ጠዋት ከ2፡30 እስከ 4፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ተገኙበት በግልጽ ይከፈታል።
1.8. የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ በጽሁፍ እንደተገለፀለት አስፈላጊውን የጨረታ ውል ማስከበሪያ በማስያዝ ከጤና ጣቢያው ጋር ውል መፈራረም አለበት። ይህ ባይፈፀም የጨረታ አሸናፊነቱን በመሰረዝ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ይሆናል።
1.9. ተጫራቾች ሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውን፣ ሙሉ አድራሻቸውን እና ፊርማቸውን እንዲሁም የተሟላ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።
1.10. የፅዳት እና ፅህፈት መሳርያዎች ናሙና ጨረታ በሚከፈትበት ወቅት ተወዳዳሪዎች ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
ማሳሰቢያ፡- ጤና ጣቢያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማስረጃ፡- በድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ የዶ/ር አቤል መልካሙ መታሰብያ ጤና ጣቢያ
0251-13-07-61 መደወል ይቻላል። ሞ/ል 0924124510
በድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ
የዶ/ር አቤል መልካሙ መታሰብያ ጤና ጣቢያ
Tender details
- Deadline: 2026-10-28
- Bid closing time: 17:00
- Bid closing (note): ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት
- Bid opening: 2026-10-29 10:00
- Bid opening (note): ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ጠዋት ከ2፡30 እስከ 4፡00
- Region: Dire Dawa
- Publishing entity: በድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ ዶ/ር አቤል መልካሙ መታሰቢያ ጤና ጣቢያ እና የደቻቱ ጤና ጣቢያ
- Bid bond: 10,000.00 ብር ለእያንዳንዱ ሎት
- Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
- Published on: Addis Zemen (Oct 11, 2026)
- Posted at: 2026-10-12T08:53:46.000Z
- Source: Qelal Tenders