Equipment and Accessories

በሲዳማ ብ/ክ/መ/ እንስሳት ሀብት ልማት ቢሮ የሀዋሳ ዳልጋ ከብት አባለዘር ማምረቻ፣ ማቀነባበሪያና ማሰራጫ ማዕከል በ2019 በጀት ዓመት ህጋዊ ዕውቅና ካላቸው ድርጅቶች CCTV Camera ከነ ሙሉ ዕቃና ኢንስታሌሽን እና ጣት አሻራ ማሽን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 02/19

በሲዳማ ብ/ክ/መ/ እንስሳት ሀብት ልማት ቢሮ የሀዋሳ ዳልጋ ከብት አባለዘር ማምረቻ፣ ማቀነባበሪያና ማሰራጫ ማዕከል በ2019 በጀት ዓመት ህጋዊ ዕውቅና ካላቸው ድርጅቶች ከታች የተዘረዘሩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

    • LOT 1. CCTV Camera ከነ ሙሉ ዕቃና ኢንስታሌሽን
    • LOV 2. ጣት አሻራ ማሽን

በመሆኑም በንግድ ዘርፉ የታደሰ ፍቃድ፣ የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ማስረጃ እና የአቅራቢነት ምዝገባ ወረቀት የሚያቀርቡ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።

  • ተጫራቾች ለመጫረት የሚያቀርቡትን ጠቅላላ ዋጋ 1% ገንዘብ የጨረታ ማስከበሪያ በሲፒኦ ማስያዝ አለባቸው።
  • ተጫራቾች በቢሮው የተዘጋጀውን የተጫራቾች መመሪያና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ይህ ጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን 9፡00 ሰዓት ድረስ ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ 200/ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ከማዕከሉ ግዢ ፋይ/ንብ/አስ/ቢሮ መውሰድ ይችላሉ።
  • ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነድ /ፕሮፎርማ/ በመሙላት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛ ቀን ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ድረስ የቴክኒካል እና የፋይናንሻል ኦርጅናል እና ሁለት ኮፒ እያዳንዳቸው በተለያየ ፖስታ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ እና CPO ቴክኒካል ዶክሜንት ውስጥ በማድረግ አጠቃላዩን በአንድ ፖስታ በማሸግ በማዕከሉ በማዕከሉ ግዢ ፋይ/ንብ/አስ/ቢሮ ለዚሁ ጨረታ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
  • የጨረታውን ሳጥን የጨረታው ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛ ቀን ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ 9፡05 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ተወካዮቻቸው በተገኙበት በማዕከሉ የግዢ ፋይ/ንብ/አስ/ቢሮ ይከፈታል። ነገር ግን 15ኛው ቀን የሥራ ቀን ባይሆን ሳጥኑን የማሸጉም ሆነ የመክፈቱ ሥነ-ሥርዓት የሚከናወነው በቀጣዩ የሥራ ቀን ከላይ በተገለጸው ሰዓትና ሁኔታ ይሆናል፡
  • ተጫራቾችና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በጊዜ ወይም በቦታው ባይገኙም ጨረታውን ከመክፈት አያስተጓጉልም።

ማዕከሉ ለዚሁ ጨረታ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ በዚህ ስልክ ቁጥር 046 212 9501 / 046 212 9504 ይደውሉ።

የሀዋሳ ዳልጋ ከብት አባለዘር ማምረቻ፣ ማቀነባበሪያና ማሰራጫ ማዕከል

/ሀዋሳ/


Tender details

  • Deadline: 2026-10-26
  • Bid closing time: 15:00
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛ ቀን ከቀኑ 9፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-10-26 15:05
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛ ቀን ከቀኑ 9፡05 ሰዓት
  • Region: Sidama
  • Publishing entity: Hawassa Livestock Breeding, Processing and Distribution Center
  • Bid bond: 1%
  • Bid document price: 200.00 ብር ለእያንዳንዱ ሎት
  • Published on: Addis Zemen (Oct 11, 2026)
  • Posted at: 2026-10-12T10:48:46.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders