Equipment and Accessories
የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት የተለያዩ እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Equipment and AccessoriesElectrical, Electromechanical and ElectronicsSpare Parts and Car Decoration Materials
Addis Ababa
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር 5/2019
የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የተለያዩ እቃዎች ግዢ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፤
1. የተሽከርካሪ መለዋወጫዎች፣
2. የኤሌክትሪክ ዕቃዎች፣
3. የተለያዩ ጄኔሬተሮች ጥገና፣ የላውንደሪ ማሽን፣ የበረዶ ቤት እና የሶፍትነር የጥገና አገልግሎት፣
ማንኛውም ተጫራች፡-
- በዘርፉ ወይም በተመሳሳይ ህጋዊና የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያለው፣ ለተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገበ መሆኑን እና የታክስ ክፍያ መለያ ቁጥር(TIN) የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ፣ተጫራቾች ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ ስለመሆናቸው በግብር ሰብሳቢው ባለስልጣን የተሰጠ በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል የታደሰ ክሊራንስ እንዲሁም በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ መመዝገባቸውን የሚገልፅ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣
- ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር ብር 500/አምስት መቶ ብር/ በመክፈል በስራ ሰዓት ከግዥና ንብረት አስተዳደር የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 30 ዝርዝር መረጃ የያዘውን የጨረታ ሠነድ ማግኘት ይችላል፤
- የጨረታ ማስከበሪያ /ቢድቦንድ/ ለሚጫረትበት የጠቅላላ ዋጋውን 2% በሲ.ፒ.ኦ፣ በባንክ ጋራንቲ ወይም በጥሬ ገንዘብ በድርጅቱ ደረሰኝ ማስያዝ ይኖርበታል፣
- የጨረታ ሰነዶችና ከጨረታው ጋር ተያያዥ የሆኑ ሠነዶችን በፖስታ በማሸግ ከጨረታ መዝጊያው ሰዓት በፊት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለበት፣
- ጨረታው ጥቅምት 19 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ሁሉም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ ውስጥ ይከፈታል። በጨረታ አከፋፈት ሂደት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙ የጨረታ ሂደቱን አያስተጓጉለውም።
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 011 466 4705 መጠየቅ ይቻላል።
የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት
Tender details
- Deadline: 2026-10-29
- Bid closing time: 10:00
- Bid opening: 2026-10-29 10:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Addis Ababa Abattoirs Enterprise
- Buyer TIN: 0000028921
- Bid bond: 2%
- Bid document price: 500.00 ብር ለእያንዳንዱ ሎት
- Published on: Reporter (Oct 11, 2026)
- Posted at: 2026-10-12T12:01:09.000Z
- Buyer website: https://www.aaae.gov.et/en/
- Source: Qelal Tenders