Textile, Garments and Uniforms

አፍሪካ ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ የተለያዩ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

የደንብ ልብስ ግዥ ጨረታ የተጫራቾች ማስታወቂያ

የጨረታቁጥር AlC - 0017/2019

አፍሪካ ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ

  • የሰራተኛች የደንብ ልብስ (ሙሉ ልብስ፣ ጫማ፣ ሽሚዝ፤ካፖርት፣ ቱታ፣ ሴፍቲ ጫማ ወዘተ…) በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች በተገለፀው መሰረት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ።

  1. ተጫራቾች ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ፣የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
  2. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 50,000.00(ሃምሳ ሺ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ማስያዝ ይኖርባቸዋል:: የጨረታው አሸናፊ ባቀረበው ሰነድ መሰረት የደንብ ልብሱን ሳያቀርብ ቢቀር ያስያዘው በባንክ የተረጋገጠሲ ሲፒኦ (CPO) ኩባንያው ገቢ ያደርጋል ወይም ተመላሽ አይሆንም።
  3. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የማይመለስ ብር 400.00 (አራት መቶ) በመክፈል ሠነዱን ገዝተው ለሚወዳደሩበት አይነት እና ብዛት የሚገልፅ የጨረታ ሠነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት በስራ ሠዓት መግዛት ይችላሉ።
  4. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ከተጨማሪ እሴት ታክስ ጋር መሆኑን ወይም አለመሆኑን መግለፅ ይኖርባቸዋል።
  5. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ከጥቅምት 02 ቀን 2019 ዓ.ም እስከ ጥቅምት 6 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 9፡00 ድረስ ቦሌ በሚገኘው የአፍሪካ ኢንሹራንስኩባንያ አ.ማ ዋና መ/ቤት ህንፃ 11ኛ ፎቅ በስራ ሰዓት በመቅረብ ለዚሁ ጨረታ አገልግሎት በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
  6. ጨረታው ጥቅምት 6 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 9፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኩባንያው ዋና መ/ ቤት ህንፃ, 11ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የስብሰባ ስልጠና አዳራሽ ይከፈታል።
  7. ጨረታውን ያሸነፈ ተጫራች የቅድሚያ : ክፍያ (Advance Payment) ለመውሰድ ከፈለገ ከታወቀ ባንክ (Unconditional Guaranty) ማቅረብ አለበት።
  8. ተጫራቾች ዋጋ ሊያስገቡ ሲመጡ የሚያቀርቡት የደንብ ልብስ ሳምፕል ኩባንያው በሚፈልገው ዓይነትና ጥራት መሠረት መሆን አለበት።
  9. አንዱ ተጫራች በሌላው ዋጋ ላይ ተንተርሶ መጫረት ከጨረታው የሚታገድ መሆኑን እንገልፃለን።
  10. አሸናፊው ተጫራች የጨረታው አሸናፊ መሆኑ ከተገለፀለት ወይም የጨረታ ውጤት ከተለጠፈበት ቀን ጀምሮ የደንብ ልብሱን ከ2 ወር ባልበለጠ ጊዜ ወይም በውሉ መሠረት ማቅረብ ይኖርበታል።
  11. ኩባንያው ጨረታውን የተሻለ አማራጭ ካገኘ በማንኛውም ጊዜ በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። 

ለበለጠ መረጃ ፡- በስልክ ቁጥር 011 661 1877 / 011 663 7485 / 011 663 7716 በመደወል መጠየቅ ይቻላል።

አድራሻ፡- አዲስ አበባ ቦሌ ሩዋንዳ ድልድይ አካባቢ አፍሪካ ኢንሹራንስ ህንፃ


Tender details

  • Deadline: 2026-10-16
  • Bid closing time: 15:00
  • Bid opening: 2026-10-16 15:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Africa Insurance Company
  • Buyer address: ቦሌ ጃፓን ኤምባሲ አካባቢ
  • Bid bond: 50,000.00 ብር
  • Bid document price: 400.00 ብር
  • Published on: Reporter (Oct 11, 2026)
  • Posted at: 2026-10-12T13:46:01.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders