Textile, Garment and Leather
በለሚኩራ ክፍለ ከተማ የወረዳ 09 የቦሌ አዲስ ቅድመ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ፋይናንስ ቡድን በ2019 በጀት አመት አገልግሎት ላይ የሚውል የተለያዩ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
More tags
Description
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በለሚኩራ ክፍለ ከተማ የወረዳ 09 የቦሌ አዲስ ቅድመ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ፋይናንስ ቡድን በ2019 በጀት አመት አገልግሎት ላይ የሚውል ግዢ፤-
- ሎት 1. የደንብ ልብስ
- ሎት 2. አላቂ የቢሮ እቃዎች
- ሎት 3 የህትመት ስራዎች
- ሎት 4. አላቂ የትምህርት እቃዎች
- ሎት 5. አላቂ የፅዳት እቃዎች
- ሎት 6. ልዮ ልዮ መሳሪያዎች
- ሎት 7. የህንፃና ቁሳቁስና ለተገጣጣሚ እቃዎች
- ሎት 8. ቋሚ እቃዎችና ኤሌክትሮኒክስ
በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
በዚሁ መሰረት
1. ተጫራቾች በመንግስት እቃ አቅራቢነት የተመዘገቡ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል
2. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው
3. የዘመኑ ግብር የከፈሉና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ተጫራቾች በማንኛውም መንግስት መ/ቤትም ሆነ በግል ድርጅት በጨረታ ምክንያት ይሁን በሌሎችም ያልታገዱ ያልተከሰሱ መሆን አለበት
4. ተጨማሪ እሴት ታከስ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልፅ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
5. የግብር መለያ ቁጥር ሰርተፌኬት ማቅረብ የሚችል
6. ተጫራቾች ይህ ማስታወቅያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰአት በትምህርት ቤቱ ግዢና አስተባባሪ የቢሮ ቁጥር 2 ብር 500(አምስት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል ጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡ ጨረታው በ10ኛው ቀን ልክ 4 ሰአት ተዘግቶ በአስራ አንደኛው ቀን በ4፡30 የሚከፈት ሲሆን በአስረ አንደኛው ቀን ቅዳሜ ከዋለ በሚቀጥለው ሰኞ በተባለው ሰአት ይከፈታል፡፡
7. ተጫራቾች ናሙና ለሚያስፈልጋቸው እቃዋች ጨረታውን ለመክፈት አንድ ቀን አስኪቀረው ድረስ ብቻ ማስገባት ይኖርባቸዋል ለአንድ እቃ አንድ ናሙና ብቻ ማቅረብ ይኖርበታል ለአንድ እቃ 2 አይነት ናሙና ያቀረበ ተጫራች እንዲሁም በሚቀርቡ ናሙና ላይ የተለየ ምልክት ከተቀመጠ ያቀረቡትን ናሙና በሙሉ የሌላውን ተጫራች እድል የሚያሳጣው ስለሆነ ውድቅ ይሆናል በተጨማሪ ትምህርት ቤቱ በሚቀረቡትና በሚመረጡት ናሙና መሰረት ግዢው ይፈፀማል ፡፡ በተጨማሪ ውስብስብ አይደሉም ልዮ ግምገማ አያስፈልጋቸውም ብሎ መስሪያ ቤቱ ያመነባቸውን እቃ በዋጋ በማወዳደርያ ግዢ ይፈፅማል ፡፡
8. ጨረታው ሲከፈት የጨረታ ማስከበርያ ብር በባንክ የተረጋገጠ ሲፕዮ ሎት 1 የደንብ ልብስ ብር 30000(ሰላሳ ሺህ ብር) ሎት 2 አላቂ የቢሮ እቃዎች 25000(ሀያ አምስት ሺህ ) ሎት 3 የህትመት ስራዎች 15000(አስራ አምስት ሺህ ብር ) ሎት4 አላቂ የትምህርት እቃዎች 20000(ሀያ ሺህ ብር) ሎት 5 አላቂ የፅዳት እቃዋች 20000(ሀያ ሺህ ብር)ሎት 6 ልዩ ልዮ መሳሪያዎች 15600(አስራ አምስት ሺህ ስድስት መቶ) ሎት 7 ለህንፃ ቁሳቁስ እና ተገጣጣሚ እቃዎች 15000(አስራ አምስት ሺህ ብር)ሎት 8 ቋሚ እቃዎች ኤሌክትሮኒክስ 70000(ሰባ ሺህ ብር) ተጫራቾች በጨረታ የሚሞላውን ማንኛውም መረጃ በጥንቃቄ በመሞላት ማቅረብ ይኖርባቸዋል ሆኖም ሳይሞሉ የሚቀርቡ ተጫራቾች ሙሉ ለሙሉ ውድቅ ይደረጋል ፡፡
9. ጨረታውን አሸናፊ ሆነው ከተገኙ በኋላ በአሸነፉት እቃ መጠን የውል ማስከበርያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል
10. ጨረታውን ለማዛባት የሚሞክሩ ይህን ጨረታ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ግንኙነት ካላቸው ግለሰቦች ጋር የሚመሳጠሩ ለመመሳጠር የሚሞክሩ የጨረታውን ሰነዱን ለማሻሻል ለመቀየር እንዲሁም የሌላን ጨረታ ዋጋ መሰረት በማድረግ መሙላትና ዋጋ የጨረታ ሰነድን ኮፒ በየትኛውም አግባብ የማይመለስ ከሆነ ስርዝ ድልዝ እንዲሁም በፍሎድ የተነካካ ከሆነ ተጫራቾች ከጨረታ ውጭ እንዲሁን የጨረታ ማስከበርያው ሲፒዮ እንደሚመለስላቸው ማወቅ ይኖርባቸዋል እንዲሁም አንድ ተጫራች ሊወዳደር የሚችለው በአንድ ድርጅት ብቻ ሲሆን ኮፒ በተለያዮ ድርጅቶች ተወዳድሮ ከተገኘ ሙሉ በሙሉ ከውድድሩ ይገላል አማራጭ ጨረታ መጠቀም የተከለከለ ነው ፡፡
11. የጨረታው ዋጋ ቫትን ጨምሮ ሲሆን የሚሞሉ በተቀመጠለት መለኪያ ብቻ ከመለኪያው ውጭ የተሞላ ዋጋ ውድቅ ይደረጋል
12. ትምህርት ቤቱ የተሻለ አማራጭ ከአገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው
13. በአነስተኛ እና ጥቃቅን ተደራጅቶ ለሚመጡ ተጫራች ከአደራጃቸው ወረዳ የድጋፍ ደብዳቤ በተደራጀበት ዘርፍ ጠቅሶ ማምረት በሚችሉት ምርት ወይም በአገር ውስጥ በሚመረት ምርት ለማከፋፈል ብቻ ማወዳደር ይችላሉ፡፡ሆኖም የአገር ውስጥ ወይም በራሳቸው ያልተመረተ ምርት ይዘው መወዳደር ከፈለጉ የጨረታ ማስከበርያ በማስያዝ ብቻ ሊወዳደሩ ይችላሉ፡፡
14. በማንኛውም ጨረታ ተጫራች ከላይ የተጠቀሱትን ያላሟሉ ከሆኑ በቀጥታ ከውድድሩ በቅድሚያ ምርመራ ውድቅ ይደረጋል
15. ጨረታ ከተዘጋ በኋላ የሚመጣ ጨረታ የጨረታ ሰነዱም ሆነ ናሙና ተቀባይነት የለውም ፡፡
16. ከላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች በአንድም በሌላም ያላሟላ ተጫራች ከጨረታው ውድቅ ይደረጋል
17. የጨረታ ውጤትን በተመለከተ በውስጥ ማስታወቅያ ብቻ ይገለጣል ቅሬታ ማቅረብ የሚችሉ በቅሬታ ማቅረቢያ ጊዜ ብቻ ነው
18: የድርጅቱን ማህተም በሁሉም ገፅ ላይ በማስቀመጥ በመሙላት ሰነድ ላይ ፊርማ ያልተቀመጠ ሰነድ ተቀባይነት የለውም
19. እቃ አስገብቶ ባጀት ቢቆይ ያለምንም ጥያቄና ጭቅጭቅ አስኪለቀቅ ድረስ ለመቆየት ፍቃደኛ የሆነ
አድራሻ ፊጋ መብራት ወረድ ብሎ ቦሌ አዲስ ቅድመ መደበኛ እና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት
ለሚኩራ ክፍለ ከተማ የወረዳ 09 የቦሌ አዲስ ቅድመ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-10-23
- Bid closing time: 16:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቅያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ቆይቶ በ10ኛው ቀን ልክ 4፡00 ሰአት
- Bid opening: 2026-10-24 10:30
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቅያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ቆይቶ በአስራ አንደኛው ቀን በ4፡30 ሰአት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Bole Addis Elementary School
- Buyer address: ፊጋ ሰሚት በአቋራጭ የሚወስደው መንገድ
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 500.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Oct 13, 2026)
- Posted at: 2026-10-13T08:57:47.000Z
- Source: Qelal Tenders