Textile, Garments and Uniforms

የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት የተለያዩ ደንብ ልብሶችን፣ ብትን ጨርቆችን፣ ጫማዎችንና ሌሎች የአደጋ መከላከያ ዕቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

የሠራተኞች ደንብ ልብስ ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ

ጨረታ ቁጥር፣ ኦ.ደ.ዱ..እ.ድ – 04/2019

የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት ዱር እንስሳት ድርጅት በሥሩ ለሚያስተዳድራቸው ሠራተኞች በ2019 ዓ/ም አገልግሎት የሚሆን ተሰፍተው የተዘጋጁ

  • የተለያዩ ደንብ ልብሶችን፤ ብትን ጨርቆችን፤ ጫማዎችንና ሌሎች የአደጋ መከላከያ ዕቃዎችን

 በጨረታ ሰነዱ ውስጥ በተዘረዘረው መሠረት በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በዚሁ መሠረት ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መመዘኛዎች የሚያሟሉና በዘርፉ የተሰማሩ ድርጅቶች ወይም ግለሰቦች በጨረታው ላይ እንድትሳተፉ ድርጅቱ ይጋብዛል።

  1. በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ፤ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር፤ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸውና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ እንዲሁም የዘመኑን ግብር ከፍለው ታክስ ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ በጨረታው ላይ መሳተፍ ይችላሉ።
  2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 1,000.00 (አንድ ሺህ) በመክፈል አዲስ አበባ ከተማ፤ ከቀበና ወደ አራት ኪሎ በሚወስደው መንገድ ኦይል ሊቢያ ማደያ ከፍ ብሎ ከሚገኘው የድርጅቱ ዋና መ/ቤት 4ኛ ፎቅ፤ ቢሮ ቁጥር 401 በመቅረብ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ።
  3. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ውስጥ ተያይዞ በቀረበው የዋጋ ማቅረቢያ ፎርም በመታገዝ የደንብ ልብሱን ዝርዝር በማየት እያንዳንዱን ዕቃ/ልብስ የሚያቀርቡበትን ዋጋ በመሙላት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
  4. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ከታወቀ ባንክ በኦሮሚያ ደንና ዱር እንሰሳት ድርጅት ስም ብር 250,000.00 (ሁለት መቶ ሃምሳ ሺህ) በባንክ የተረጋገጠ ቼክ (CPO) ወይም የባንክ ዋስትና (Bid Bond Guarantee) በማሠራት ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አብሮ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሠነዳቸውን በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ ከጥቅምት 02 ቀን 2019 ዓ/ም እስከ ጥቅምት 18 ቀን 2019 ዓ/ም ጠዋት 4፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብና ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል።
  6. ማንኛውም ተጫራች አንዱ ተጫራች ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም።
  7. ድርጅቱ የተሸለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  8. ለተጨማሪ መረጃ ከታች የተገጸውን ስልክ ቁፕር በመደወል ወይም በጽሁፍ መጠየቅና ማብራሪያ ማግኘት ይችላሉ።

የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት

አድራሻ፣ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፤

አራዳ ክ/ከተማ፤ ወረዳ 07፣

ቀበና ኦይል ሊቢያ ከፍ ብሎ

ስልክ ቁ. 011-122-00-20

011-124-02-58

የኦሮሚያ  ደንና ዱር እንስሳት


Tender details

  • Deadline: 2026-10-28
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-10-28 10:00
  • Bid opening (note): የጨረታ መክፈቻ ቀንና ሰዓት አልተገለጸም
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Oromia Forest and Wildlife Enterprise
  • Buyer address: አዲስ አበባ አራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ቀበና ኦይል ሊቢያ አጠገብ
  • Bid bond: 250,000.00 ብር
  • Bid document price: 1000.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Oct 12, 2026)
  • Posted at: 2026-10-13T09:00:14.000Z
  • Buyer website: https://www.oromiaforest.gov.et
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders