Equipment and Accessories

በአብክመ በሰ/ወሎ ዞን የግዳን ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለ2019 በጀት አመት ለግ/ወ/ሴ/መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል የተለያዩ ዕቃዎችን መግዛት ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 001/2019

በአብክመ በሰ/ወሎ ዞን የግዳን ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለ2019 በጀት አመት ለግ/ወ/ሴ/መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል በመደበኛ በጀት፡-

  • ሎት፡- 1 የጽህፈት መሳሪያ፣
  • ሎት፡- 2 ቋሚ አላቂ የቢሮ መገልገያ
  • ሎት፡- 3 የሚገጣጠም ፈርኒቸር
  • ሎት፡- 4 ኤሌክትሮኒክስ እቃ
  • ሎት፡_ 5 የመኪና ጎማ
  • ሎት፡- 6 የመኪና መለዋወጫ እቃወች
  • ሎት፡- 7 የጽዳት እቃዎች
  • ሎት 8፡- የግንባታ እና የዉሃ እቃዎች ማቴሪያል
  • ሎት 9፡- ስሚንቶ ጨረታ አወዳድሮ መግዛትና ማሰራት ይፈልጋል።

ስለሆነም፡-

1ኛ. በየዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ስራ ፈቃድና ምዝገባ ማቅረብ የሚችል።

2ኛ. ተወዳዳሪዉ በግብር አመቱ ተገቢዉን የታክስ እና ግብር ግዴታ የተወጡ መሆኑን የሚያሳይ የታክስ ክሊራንስ ማቅረብ የሚችል እና ላለማጭበርበር እና ላለመመሳጠር የሚሰጠዉን ፎርም ሞልቶ ማቀረብ አለበት።

3ኛ. የግዥ መጠኑ ከ500000 (አምሰት መቶ ሺህ) ብር በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ቫት ተመዝጋቢ የሆነና መረጃ ማቅረብ የሚችል።

4ኛ.ተጫራቾች በጨረታ ላይ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው 10 ማቅረብ (ማስገባት) አለባቸው።

5ኛ. የሚገዙ እቃዎች አይነት እና ዝርዝር መገለጫ /ስፔስፍኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት የሚችሉ ሲሆን የተሰጣቸዉን የጨረታ ቅጽ በአግባቡ መሙላት የሚችል መሆን አለበት።

6ኛ.ተጫራቾች ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ የኢትዮጵያ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከዚህ በታች በዝርዝር በተገለጸው መሰረት ከሎት 1 እስከ ሎት 9 ድረስ ያሉት ሁሉም ሎቶች 10ኛዉ ቀን 11፡30 ድረስ ግ/ወ/ ገንዘብ ጽ/ቤት ፋይናንስ ቡድን ዋና ገንዘብ ያዥ ቢሮ  ቁጥር 001 ድረስ ዘወትር በስራ ስአት በመምጣት መግዛት ይችላሉ።

7ኛ. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ቢድ ቦንድ የሚወዳደሩበት እቃ ከሞሉት ጠቅላላ ዋጋ ቫትን ጨምሮ

  • ሎት፡-1 የጽህፈት መሳሪያ  ሎት፡- 3 የሚገጣጠም ፈርኒቸር ሎት፡- 4 ኤሌክትሮኒክስ  ሎት፦ 5 የመኪና ጎማ ሎት፡- 6 የመኪና መለዋወጫ እቃወች ሎት 8፡- የግንባታ እና የዉሃ እቃዎች ማቴሪያልሎት 9፡- ስሚንቶ ጨረታ ብር 40000 /አርባ ሺህ ብር/ እና ፣
  • ሎት፡ 2 ቋሚ አላቂ የቢሮ መገልገያ  ሎት፡-7 የጽዳት እቃዎች ብር 10000 / አስር ሺህ/ ብቻ በባንክ በተረጋገጠ ትእዛዝ ሲ.ፒ.ኦ/፤ ወይም በጥሬ ገንዘብ በደረሰኝ ወይም በሁኔታ ላይ ባልተመሰረተ የባንክ ጋራንት በማስያዝ ከዋጋ ማቅረቢያው ፖስታው ውስጥ አሽጎ (አያይዞ) ማቅረብ ይኖርበታል።

8ኛ, ጨረታዉ ጸንቶ የሚቆይበት ጊዜ ጨረታዉ ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 40 አርባ ቀን የሚቆይ ይሆናል።

9ኛ. ጨረታው ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ግ/ወ/ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 20 ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ጨረታዎች ከሎት 1 እስከ ሎት 9 ድረስ ያሉት በ11ኛው ቀን 4፡00 ስአት ታሽጎ በዚሁ ቀን 4፡3ዐ ስአት ይከፈታል። የተጠቀሰው ቀን ቅዳሜ እና እሁድ ወይም ካላንደር ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ታሸጎ በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።

10ኛ አሸናፊ ተጫራች ውጤቱ በማስታወቂያ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው ቀን ድረስ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ ቢያንስ 10% በባንክ በተረጋገጠ ትእዛዝ ሲ.ፒ.ኦ/፤ ወይም በጥሬ ገንዘብ በደረሰኝ ወይም በሁኔታ ላይ ባልተመሰረተ የባንከ ጋራንት በማስያዝ በፍትህ ውለታ መውሰድ ይኖርበታል።

11ኛ. የሚገዙት እቃዎች የማስረከቢያ ቦታ ግዳን ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ስር ባሉ ሁሉም ንብረት ክፍሎች ዉስጥ ይሆናል።ለዚህ ም የሚዎጡ ወጭወች በሙሉ በአሸናፊዉ ድርጅት የሚሸፈን ይሆናል።

12ኛ መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ።

13ኛ, ስለጨረታው ዝርዝር ሁኔታ መረጃ ካስፈለገ በግዳን ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0332120008 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ።

በአብክመ የግዳን ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት 


Tender details

  • Deadline: 2026-10-22
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-10-22 10:30
  • Bid opening (note): ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን 4፡30 ሰዓት
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: North Wello Zone Gedan FEDB
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 200.00 ብር ለእያንዳንዱ ሎት
  • Published on: Addis Zemen (Oct 12, 2026)
  • Posted at: 2026-10-13T09:10:36.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders