Stationery
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት በሰሜን ሸዋ ዞን የአሳግርት/ወ/ገንዘብ ጽ/ቤት የጽህፈት መሣሪያዎች እና እንስሳት መድኃኒትና መገልገያ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ መለያ ቁጥር 001/2019
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት በሰሜን ሸዋ ዞን የአሳግርት/ወ/ገንዘብ ጽ/ቤት ሎት 1 የጽህፈት መሣሪያዎች እና ሎት 2 እንስሳት መድኃኒትና መገልገያ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም በጨረታ ለመወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች ያለውን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡
1. በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው
2. የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር /TIN/ ያላቸው፡፡
3. የዘመኑን የሚፈለግባቸውን የመንግሥት ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማያያዝ አለባቸው
4. የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው
5. የግዥው መጠን ብር 500000.00/ ሁለት መቶ ሺህ ብር እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገበ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
6. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተ.ቁ 1-5 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው
7. የሚገዛው የዕቃው ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ማለትም ሎት 1 የጽህፈት መሣሪያዎች ብር 10000፣ ሎት 2 እንስሳት መድኃኒት ብር 16000 በጥሬ ገንዘብ ወይም ከታወቀ ባንክ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ በደብዳቤ የተረጋገጠ የሚሰጥ ዋስትና፣ ሲፒኦ ማስያዝ አለባቸው፡፡
9. አሸናፊው ድርጅት ጽ/ቤቱ አሸናፊነቱን ከገለፀለት ቀን ጀምሮ የውል ማስከበሪያ በማስያዝ በውሉ መሰረት ዕቃዎቹን ወዲያውኑ ማቅረብ አለባቸው፡፡
10. በተጫራቾች የተሞላ የጨረታ ሠነድ መ/ቤቱ ሰነዱን እንዲሸጥ ባስቀመጠው ከ02/02/2019 ዓ.ም ጀምሮ 10 ቀን ተከታታይ ቀናት በመ/ቤቱ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ በማንኛውም የሥራ ሰዓት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በሰም ባይታሸግም ዋናና ቅጂ በማለት ሙሉ አድራሻ በመፃፍ የጨረታ ሰነድ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
11. ጨረታው የሚዘጋበት ቀን በ11ኛው ቀን ማለትም 12/02/2019 ዓ.ም የጨረታው ሣጥን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ይታሸጋል በዛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል፡፡
12. የጨረታው መክፈቻ ቀን ቅዳሜና እሁድ ከዋለ በተከታዩ የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል
13. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሎት የተገለፀውን ሰነድ ከአሳግርት ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በመሄድ የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል መግዛት ይችላል፡፡
14. አሸናፊው ድርጅት የአሸነፈውን ዕቃ ንብረት አሳግርት ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ድረስ ወይም በተገለፀበት ሳይት ማቅረብ አለበት
15. መ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
16. የሚያቀርቡት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ቢያንስ ለ2 ወር የጊዜ ገደብ ያለው መሆን ይኖርበታል ።
17. ለኢንተርፕራይዞች ከሥራና ሥልጠና ጽ/ቤት የሚቀርብ ማንኛውም የዋስትና ደብዳቤ ተቀባይነት የለውም፡፡
18. ለአሸናፊውም ድርጅት ምንም አይነት ቅድመ ክፍያ የማከፈልና ዕቃውን አታሎ ሲያስገባ መሉ ክፍያ የሚከፈለው መሆኑ እንዲታወቅ፡፡
ማሳሰቢያ፡- አሸናፊው ድርጅት ጥራት ያለው ዕቃ በወቅቱ አስገብቶ እና ሂሳቡን በወቅቱ የሚያፀድቅ መሆን አለበት፡፡
ውድድሩ በሎት ስለሆነ ማንኛውም ተወዳዳሪዎች በሎት ውስጥ የተዘረዘሩት ሁሉ እቃዎች ዋጋ መሙላት ይጠበቅባቸዋል
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0116 240 394 ደውለው መጠየቅ ይቻላል።
ወረዳው የሚገኝበት ርቀት አዲስ አበባ በ25 ኪሜ እና ከደ/ብርሃን በኪ/ሜ ላይ ይገኛል፡፡
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በሰ/ሸዋ ዞን የአሳግርት ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-10-22
- Bid closing time: 10:00
- Bid opening: 2026-10-22 10:30
- Region: Amhara
- Publishing entity: Asagirt Woreda Finance and Economic Development Bureau
- Buyer address: ከአዲስ አበባ በ125 ኪ.ሜ እና ከደ/ብርሃን በ74ኪ.ሜ ላይ ይገኛል፡፡
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 500.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Oct 12, 2026)
- Posted at: 2026-10-13T09:38:00.000Z
- Source: Qelal Tenders