Textile, Garments and Uniforms

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የካፊቴሪያ አገልግሎት ሠራተኞች አልባሳት አምራች ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በኮንትራት ለማሰራት ይፈልጋል

Description

የካፌቴሪያ አገልግሎት ሠራተኞች የአልባሳት አቅርቦት

ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር SSNT-T650

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የካፌቴሪያ አገልግሎት ሠራተኞች አልባሳት አምራች ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በኮንትራት ለማሰራት ይፈልጋል።

በመሆኑም ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉ አምራቾች በጨረታው ላይ መሳተፍ ይችላሉ።

  1. ለስራው ብቁ የሆኑ ተጫራቾች እና በሙያ ዘርፉ አምስት (5) ዓመት እና ከዚያ በላይ የሰሩ ፣ የዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ በመንግስት ጨረታዎች ለመሳተፍ ጊዜው ያላለፈበት ፈቃድ ያላቸው እና ከግብር እዳ ነጻ ስለመሆናቸው ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
  2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት የስራ ቀናት በአቅራቢያቸው ከሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ የማይመለስ 200.00 ብር/ ሁለት መቶ ብር/ በሂሳብ ቁጥር 1000006958277(E-99) ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ጨረታ ቁጥር SSNT T650 በሚል ገቢ በማድረግና የከፈሉበትን የገቢ ደረሰኝ ቅጅ (Deposit Slip Copy)፣ የጨረታውን ቁጥርና አይነት እንዲሁም የድርጅቱን ሙሉ አድራሻ ከታች በተጠቀሰው የኢሜይል አድራሻ በመላከ የጨረታ ሰነዱን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል በኢሜይል ማግኘት ይችላሉ።
  3. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ሃምሳ ሺህ ብር (50,000.00) በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ (CPO)ወይም ለ150 ቀናት የሚቆይ ምንም አይነት ቅድመ ሁኔታ የሌለው የባንክ ዋስትና ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ከማንኛውም ኢንሹራንስ የሚቀርብ ዋስትና ተቀባይነት አይኖረውም፡፡ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ተጫራቾችን የጨረታ ማስከበሪያ ለተጨማሪ ቀን የሚቆይበት ጊዜ እንዲራዘምለት የመጠየቅ መብት አለው።
  4. ተጫራቾች በጨረታው ደንብ መሠረት የመጨረቻ ሠነዳቸውን (ቴክኒካል እና ፋይናንሻል) ዋናውን እና ቅጂውን እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያ በተለያየ ኢንቨሎፕ አሽገው ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል ዓርብ፣ ጥቅምት 27 ቀን 2019 ዓ.ም እስከ ከሰዓት 8:30 ሰዓት ድረስ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት በተመሳሳይ ቀን 9፡00 በቦሌ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና መሥሪያ ቤት በጨረታ መክፈቻ አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል።

ለተጨማሪ ማብራሪያ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ

ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ

ስትራቴጂከ ሶርሲንግ ነን ቴክኒካል ክፍል

በስልክ ቁጥር: +251-115-17-80-25 በመደወል መጠየቅ ይቻላል::

ኢሜል: [email protected] 

አየር መንገዱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

Ethiopian

የኢትዮጵያ


Tender details

  • Deadline: 2026-11-06
  • Bid closing time: 14:30
  • Bid opening: 2026-11-06 15:00
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Ethiopian Airlines Group (ETG)
  • Buyer TIN: 0000028498
  • Bid bond: 50,000.00 ብር
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Oct 12, 2026)
  • Posted at: 2026-10-13T09:38:34.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders