Textile, Garments and Uniforms
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የአዲስ አበባ ቁጥር 2 መካከለኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት የተለያዩ እቃዎችን መግዛት ይፈልጋል
Textile, Garments and UniformsTextile, Garment and LeatherShoes and Other Leather Products
Addis Ababa
More tags
StationeryOffice Supplies and ServicesPrinted Advertising MaterialsAdvertising and PromotionPrinting and PublishingCleaning and Janitorial Equipment and ServiceEquipment and AccessoriesElectrical, Electromechanical and ElectronicsHand Tools and Workshop EquipmentMechanicalVehicle (garage service)Maintenance and RepairOthersSpare Parts and Car Decoration MaterialsBuilding and Finishing MaterialsConstruction and Water WorksOffice Machines and ComputersConstruction Machinery and EquipmentMachineryComputer and AccessoriesIT and TelecomOffice Machines and AccessoriesGardening and LandscapingPlastic ProductsPlastic Raw Materials and ProductsPlastic Raw MaterialsCatering and Cafeteria ServicesHouse and BuildingFood and BeverageFood Items and DrinksOffice FurnitureFurniture and FurnishingFlora and HorticultureAgriculture and FarmingAmharic2merkatoAddis Ababa City Administration Customs Revenue Authority Addis Ababa number 2 medium taxpayers Bureau
Description
የመጀመሪያ ዙር ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
ማስታወቂያ መለያ ቁጥር 01/2019
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የአዲስ አበባ ቁጥር 2 መካከለኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት በተለያዩ ሎቶች
- የደንብ ልብስና የስራ ልብስ
- የጽህፈት መሳሪያዎች እና
- አላቂ የቢሮ ዕቃዎች፣
- ህትመት ውጤቶች፣
- የፅዳት እቃዎች፣
- የቋሚ እና አላቂ የመረጃ ቴክኖሎጂ እቃዎች፣
- ልዩ ልዩ መሳሪያዎች ግዥ፣
- ለተሽከርካሪዎችና ሌሎች መጓጓዣዎች እድሳት ጥገናና ጌጣጌጥ ግዥ ለፕላን፣
- ለማሽነሪ እና ለተገጣጣሚዎች እድሳትና ጥገና፣ህንፃና ቁሳቁስ እና ለተገጣጣሚዎች እድሳት እና
- ጥገና፣የመስተንግዶ ግብአት (ቆሎና ውሀ)፣ለህንፃ እና
- ለቁሳቁስ ለተገጣጣሚዎች መግዣ (ቀሚ እቃዎች መግዣ) ፣
- ልዩ ልዩ እቃዎች (አበባ እና አበባ ማስቀመጫ እንዲሁም ሌሎች) በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም ከዚህ በታች የተገለጸውን መስፈርት የምታሟሉ አቅራቢዎች እንድትሳተፉ ይጋብዛል።
- በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤
- የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፍኬት (TIN) ያላቸው መሆነን፤
- ገንዘብ ሚኒስቴር ባዘጋጀው የዕቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ እና መረጃ ያላቸው፤
- ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡና ለተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምሥክር ወረቀት ከሰነዳቸው ጋር አያይዘው የሚያቀርቡ፤
- በአነስተኛና ጥቃቅን የተደራጁ ከሆኑ ከአደራጀው አካል የድጋፍ ደብዳቤ፤
- የጨረታ ማስከበሪያ መጠን፡-
- የደንብ ልብስ (ሎት 1) 7,000.00፣
- ለአላቂ የጽህፈት እቃዎች (ሎት2) ብር 10,000.00፣
- ለህትመት ውጤቶች (ሎት3) ብር 26,000.00፤
- ለጽዳት እቃዎች (ሎት4) ብር 3,000.00፣
- የመስተንግዶ ግብአት (ቆሎና ውሃ) ፣ (ሎት5) ብር 6,000.00፤
- ልዩ ልዩ መሳሪያዎች (ሎት6) ብር 3,000.00፣
- ለተሽከርካሪዎችና ሌሎች መጓጓዣዎች እድሳት ጥገናና ጌጣጌጥ ግዥ (ሎት7) ብር 8,000.00፣
- ለህንጻ እና ለቁሳቁስ መገጣጠሚያዎች ዕቃ ግዥ (ሎት8) ብር 6000.00፣
- ለፎቶ ኮፒና ፕሪንተር እድሳትና ጥገና አገልግሎት እንዲሁም መለዋወጫ ዕቃዎች ለፕላን፣ለማሽነሪ እና ለተገጣጣሚዎች እድሳትና ጥገና፣ (ሎት9) ብር 7,000.00፣
- ለፕላን፣ለማሽነሪ እና መሳሪያ ግዥ (ሎትıo) ብር 10,000.00 ፣
- ለህንፃ፣ለቁሳቁስ ለተገጣጣሚዎች መግዣ (ቋሚ እቃዎች መግዣ) (ሎት11) ብር 5,000.00፣
- ልዩ ልዩ እቃዎች (አበባና አበባ ማስቀመጫ እንዲሁም ሌሎች) (ሎት12) ብር 3,000.00 በባንክ በተመሰከረለት (CPO) ብቻ መያዝ አለበት።
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ሎቶች የእቃው ናሙና ወይም ሳምኘል በድርጅቱ በተረጋገጠ ማህተም እና ፊርማ ከጨረታ መዝጊያ ቀን እና ሰዓት በፊት ለግዥ ክፍል ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ሳምፕል ሲወዳደር ካሳየው ሳምፕል ውጪ ካመጣጥ የመቀየር ግዴታ አለበት።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 400 (አራት መቶ ብር) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 ተከታታይ የስራ ቀን ስቴድየም አካባቢ ይሓ ሲቲ ሴንተር ህንፃ 3ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የቅ/ጽ/ቤታችን ግዥና ፋይናንስ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 303 መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡበትን የቴክኒክ ፕሮፖዛል “አንድ ኦርጅናል ኮሮ" እና የፋይናሻል ዋጋ ማቅረቢያ ዝርዝር “አንድ ኦርጅናል ኮፒ የድርጅት ስም አድራሻ እና ማህተም እንዲሁም የሚጫረቱበትን የጨረታ ዓይነት ሎት በመፃፍ እና በየሎቱ በመለየት በታሸገ ኤንቨሎፕ በማቅረብ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው ቀን ከቀኑ 11:00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው በ11ኛ ቀን ጥዋት 3፡00 ሰዓት ታሽጎ በዛው እለት ጥዋት 3፡30 ሰዓት 6ኛ ፎቅ የስብሰባ አዳራሸ ቢሮ ቁጥር 604 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። በጨረታው መክፈቻ ቀን እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።
- የጨረታው አሸናፊ ድርጅት አሸናፊነቱ ከተገለፀለት ቀን ጀምሮ በ10 ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን የእቃው ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ በባንክ በተመሰከረለት (CPO) በማስያዝ ከመስሪያ ቤቱ ጋር ውል በመፈፀም አሸናፊ የሆነባቸውን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት በማምጣት ቅ/ጽ/ቤቱ ንብረት ክፍል ድረስ ገቢ ማድረግ አለበት።
- ለጨረታ ከቀረቡት ዕቃዎች ዝርዝር ውስጥ ጽ/ቤቱ እስከ 20% /ሃያ ፐርሰንት/ ጨምሮ ወይም ቀንሶ የመግዛት መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ ተ.እ.ታ (ቫት) ጨምሮ ወይምተ.እ.ታ (ቫት) በፊት መሆኑን መግለፅ ይኖርባቸዋል፡፡ያልተገለፁ ከሆነ ተ.እ.ታ (ቫት) ጨምሮ እንደሆነ ተደርጎ ይወሰዳል።
- ተጫራቾች በጨረታው ስነዱ የተገለፀው የመጫረቻ ሰነድ ማቅረቢያ የመጨረሻ ጊዜ ካለፈ በኋላ ወይም በጨረታው ሰነዱ በተገለፀው የጨረታ ዋጋ ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ውስጥ ራሱን ከጨረታ ካገለለ እና በጨረታው አሸናፊነቱ ከተገለፀ በyላ ከተገለፀላቸው ቀን ቀርበው ውል ካልፈፀሙና የውል ማስከበሪያ ካላስያዙ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ለመንግስት ገቢ ይሆናል።
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0115581772/0115580505 መጠየቅ ይቻላል።
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ
የአዲስ አበባ ቁጥር 2 መካከለኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-10-23
- Bid closing time: 09:00
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛ ቀን ጠዋት 3፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-10-23 09:30
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛ ቀን ጠዋት 3፡30 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Addis Ababa City Administration Customs Revenue Authority Addis Ababa number 2 medium taxpayers Bureau
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 400.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Oct 12, 2026)
- Posted at: 2026-10-13T09:49:28.000Z
- Source: Qelal Tenders