Equipment and Accessories
የሲዳማ ብሔ/ክል/መንግስት ማረሚያ ቤት ኮሚሽን በ2019 በጀት ዓመት ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የቢሮ የኮምፒውተርና ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Equipment and AccessoriesElectrical, Electromechanical and ElectronicsComputer and Accessories
Sidama
Description
ብሔራዊ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የሲዳማ ብሔ/ክል/መንግስት ማረሚያ ቤት ኮሚሽን በ2019 በጀት ዓመት ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የቢሮ የኮምፒውተርና ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን Desk top Computer ፣ Lap top Computer ፣ Photo Copier እና Printer ለመግዛት ህጋዊ አቅራቢዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
1. ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው ህጋዊ መስፈርቶች፡-
- በዘርፉ (በኤሌክትሮኒክስ ወይም በአይቲ ዕቃዎች አቅርቦት) በ2019 በጀት ዓመት የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ስራ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ።
- የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN certificate /ከኢትዮጵያ ታክስና ጉምሩክ ባለስልጣን የተሰጠ ማቅረብ የሚችሉ
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ምስክር ወረቀት / VAT Registration certificate /ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያሳይ ማቅረብ የሚችሉ።
- በ2019 የታክስ ክሊራንስ ሰርቴፍኬት / ወቅታዊ የመንግስት ግብር መክፈሉንና በታከስ ዕዳ አለመፈለጉን የሚያረጋግጥ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ።
- በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል በመንግስት አቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ከፌዴራል ከክልል/ግዥና ንብረት ባለስልጣን የሚሰጥ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
2. የጨረታ ሰነድ አገዛዝና አቀራረብ
- ተጫራቾች የማይመለስ የኢትዮጵያ ብር 200.00/ ሁለት መቶ ብር / ብቻ በመከፈል የዕቃዎቹን ዝርዝር መግለጫ /Technical Specifications/ የያዘውን የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለአስር / 10 / ተከታታይ የስራ ቀናት በኮሚሽኑ ግዥና ንብረት አስ/ር/ዳሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 12 በመምጣት መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የቴክኒክ /Technical Specifications/ እና የፋይናንስ /financial offer/ ሰነዶቻቸውን አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ፎቶ ኮፒ በማድረግ ለየብቻ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 100,000.00 /አንድ መቶ ሺህ ብር/ የያዘ በባንክ የተረጋገጠ የክፊያ ማዘዣ/ CPO/ ፤ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና/Bank Guarantee /በባንክ የተረጋገጠ ቼክ ከቴክኒካል ሰነዱ ጋር በማያያዝ ማቅረብ አለባቸው።
- የሚገዛው የዕቃ ብዛት ዓይነትና ጥራት በሚሸጠው የጨረታ ሰነዱ ላይ በዝርዝር የተቀመጠ ስለሆነ የጨረታ ሰነዱ ይበልጥ ተቀባይነት አለው።
- የጨረታው አሸናፊ የሚሆን ድርጅት ማሸነፉ ከተገለፀ በኋላ ከመ/ቤቱ ጋር ውል መግባት ይኖርባቸዋል። የዉል ስምምነቱን የማይገቡ ከሆነ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ሲፒኦ እንዲወረስ ተደርጎ በተጨማሪም በጥፋተኝነት ዝርዝር እንዲገቡ ይደረጋል ::
3. የጨረታ መዝጊያና መክፈቻ ቀን፡-
- ተጫራቾች ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ አስራ እንደኛው (11ኛው) ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ በኤንቬሎፑ ላይ የተጫራች ድርጅት ማህተም ተደርጎ፣ ተፈርሞበትና በሰም ታሽጎ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
- ኮሚሽኑ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 046-2127-875 ደውለው መጠየቅ ይቻላል።
የሲዳማ ክልል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን
Tender details
- Deadline: 2026-10-23
- Bid closing time: 14:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ አስራ እንደኛው (11ኛው) ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-10-23 14:00
- Bid opening (note): የጨረታው መክፈቻ ቀንና ሰዓት አልተገለፀም
- Region: Sidama
- Publishing entity: Sidama Region Prison Commission
- Bid bond: 100,000.00 ብር
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Oct 12, 2026)
- Posted at: 2026-10-13T10:09:13.000Z
- Source: Qelal Tenders