Equipment and Accessories
በአራዳ ከፍለ ከተማ አስተዳደር በወረዳ 08 የበአታ ጤና ጣቢያ በ2019 ዓመት በጀት የሚያስፈልጉ እቃዎች እና አገልግሎት በግልጽ ጨረታ ለመግዛት ይፈልጋል
Equipment and AccessoriesElectrical, Electromechanical and ElectronicsComputer and Accessories
Addis Ababa
More tags
IT and TelecomOffice Machines and AccessoriesOffice Supplies and ServicesPrinted Advertising MaterialsAdvertising and PromotionPrinting and PublishingTextile, Garments and UniformsTextile, Garment and LeatherShoes and Other Leather ProductsCleaning and Janitorial Equipment and ServiceHand Tools and Workshop EquipmentMechanicalHealth Related Services and MaterialsHealth Care, Medical IndustryMedical Equipment and SuppliesPharmaceutical ProductsOthersMaintenance and RepairPlastic ProductsPlastic Raw Materials and ProductsPlastic Raw MaterialsStationeryHouse FurnitureFurniture and FurnishingOffice FurnitureDisposal of Hazardous WasteSafety and SecurityWater Engineering Machinery and EquipmentConstruction and Water WorksWater Pipes and FittingsBuilding and Finishing MaterialsWater System InstallationAmharic2merkatoArada Sub City Behata Health Post
Description
ለአንደኛ ጊዜ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
ግልጽ ጨረታ መለያ ቁጥር 01/2019
በአራዳ ከፍለ ከተማ አስተዳደር በወረዳ 08 የበአታ ጤና ጣቢያ በ2019 ዓመት በጀት የሚያስፈልጉ
- ሎት1 ቋሚ ኤሌክትሮኒክስ እና የቢሮ ቋሚ
- ሎት 2 የደንብ ልብስ
- ሎት 3 ህትመት
- ሎት 4 የጽህፈት መሳሪያ እና የጽዳት እቃዎች
- ሎት 5 የጥገና እቃዎች
- ሎት 6 የደንብ ልብስ ስፌት
- ሎት 7 የመድሃኒት እና የህክምና መገልገያ እቃዎች
- ሎት 8 የሚወገድ የመድሃኒቶች በኪሎ
- ሎት 9 ሮቶ የጥገና አገልግሎት
በግልጽ ጨረታ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በጨረታ መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን ሁኔታዎች በቅድሚያ ማሟላት ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች በተሰማሩበት የስራ መስክ የንግድ ፈቃድና የዘመኑን ግብር ለመክፈላቸውና የታደሰ የንግድ ፍቃድ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- የመንግስት የግዥ ጨረታ ላይ ለመሳተፍ የሚያስችል የተሟላ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።
- ተጫራቾች የግብር ክፍያ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው ለሚወዳደሩባቸው እቃዎች ከብር 200,000/ሁለት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ መሆናችሁን የሚያረጋግጥ ህጋዊ ማስረጃ ማቅረብ የምትችሉ።
- ተጫራቾች በጨረታ ያሸነፉባቸውን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ወደ መ/ቤታችን ግቢ ማድረስ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚያገለግል የተጫረቱበትን ዋጋ 2% በድርጅቱ ስም ሲ.ፒ.አ በበንክ የተረጋገጠ ከመወዳደሪያ ሰነዶቻቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች በአንድ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም።
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙት የጨረታ ሰነድ ላይ በጥንቃቄ ሞልተው በመፈረምና የድርጅቱን ማህተም ማድረግ ዋና ኮፒውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አስር ቀን) ተከታታይ የስራ ቀን ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- መ/ቤቱ ባዘገጀው የጨረታ ሰነድ ላይ ዋጋ ሞልቶ እና የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም አድርጎ የሚያቀርብ ተጫራች ተቀባይነት ይኖረውም።
- የጨረታውን አሸናፊ ማሸነፋቸውን በጽሁፍ የምንገልጽላቸው ሲሆን ለጨረታ አፈጻጸም ማስከበሪያ ላሸነፉበት እቃ ዋጋ 10% በማስያዝና ውል በመዋዋል የተመረጡትን እቃዎች በሙሉ በውሉ መሰረት ካላቀረቡት በግዢ ህጉ መሰረት መ/ቤቱ ተጠያቂ ያደርጋል፡፡ በጨረታው ያላሸነፉ ድርጅቶች ያስያዙትን የጨረታ ማስከበሪያ ወዲያውኑ ይመለስላቸውል።
- ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የማወዳደሪያ ሀሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ እንዲሁም ከጨረታው ራሳቸውም ማግለል እንደማይችሉ ማወቅ አላባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ የያዘ የማይመለስ ብር 100(አንድ መቶ ብር) በመከፈል ይህን ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣ ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ጤና ጣቢያ ቀርበው መውስድ ይችላሉ።
- የጨረታ ሳጥን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከ11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰአት ላይ ተዘግቶ 3፡30 ላይ የሚከፈት ሲሆን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኝበት አድራሽ አራዳ ክ/ከተማ በአታ ጤና ጣቢያ አዳራሽ በግልጽ ይከፈታል።
- ተጫራቾች የሚያቀርቧቸው እቃዎች በሎት 2-5 ያለው በሙሉ ኦርጅናል ሳምፕል ወይም ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤ እንዲሁም 1 ሎት1 ካታሎግ መስሪያ ቤቱ ድረስ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማቅረብ አለባቸው።
- የእቃዎችን ሳምፕል እና ካታሎግ ያላቀረቡ ተጫራቾች ከጨረታ ውድቅ መሆኑን ማወቅ አለባቸው።
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ፡- አድራሻ ከቅ/ስላሴ ቤተክርስቲያን ወደ ጠቅላይ ሚንስቴር ፅ/ቤት ወረድ ብሎ በስተምስራቅ
100 ሜትር ገባ ብሎ ከመስከረም 1ኛ ደረጃ ት/ቤት አጠገብ ነው።
ስልክ ቁጥር:- 011-8699041, 011-8684810 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
የበአታ ጤና ጣቢያ
Tender details
- Deadline: 2026-10-24
- Bid closing time: 09:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከ11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰአት
- Bid opening: 2026-10-24 09:30
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከ11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰአት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Arada Sub City Behata Health Post
- Buyer address: ከስላሴ ቤተክርስቲያን ወደ ጠቅላይ ሚንስቴር ፅ/ቤት ወረድ ብሎ በስተምስራቅ 100 ሜትር ገባ ብሎ ከመስከረም 1ኛ ደረጃ ት/ቤት አጠገብ
- Bid bond: 2%
- Bid document price: 100.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Oct 13, 2026)
- Posted at: 2026-10-13T10:20:39.000Z
- Source: Qelal Tenders