Equipment and Accessories

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ሰላም እና ጸጥታ ቢሮ ዲስክ ቶፕ ኮምፒተር እና ኘሪተር ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የግዥ መለያ ቁጥር ግ/ጨ/03/2019

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ሰላም እና ጸጥታ ቢሮ ዲስክ ቶፕ ኮምፒተር እና ኘሪተር  ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡

1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡

2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡

3. የግዥው መጠን ብር 500,000 (አምስት መቶ ሽህ) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡

4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ. 1 እስከ 3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡

5. የሚገዙ የአገልግሎት ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡

6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300 (ሰስት መቶ) ብቻ በመክፈል ከግዥና ፋይ/ንብ/አስተ/ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 315  ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት ማግኘት ወይም መግዛት ይችላሉ፡፡

7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከግዥና ፋይ/ንብ/አስተ/ዳይሬክቶሬት  ቢሮ ቁጥር 315  ማስታወቂያው ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት ማግኘት ወይም መግዛት ይቻላል፡፡

8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድቦንድ) ለሚወዳደሩበት የዕቃ ግዥ ብር 20,000 (ሃያ ሽህ) ብቻ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡

9. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በማድረግ በአብክመ ሲቪል ሰርቪስ ቢሮ ከግዥና ፋይ/ንብ/አስተ/ዳይሬክቶሬት በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ጨረታው ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት በ11ኛው ቀን አስከ 3፡30  ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

10.  ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 315 በ11ኛው ቀን 3፡30  ተዘግቶ 4፡00 ይከፈታል፡፡ ዕለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በ3.00 ተዘግቶ 4፡00  ይከፈታል፡፡

11. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

12. በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 315 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 220 9644/ 058 220 9646 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ሰላም እና ጸጥታ ቢሮ 

ባህር ዳር


Tender details

  • Deadline: 2026-10-22
  • Bid closing time: 09:30
  • Bid closing (note): ጨረታው ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት ቆይቶ በ11ኛው ቀን 3፡30
  • Bid opening: 2026-10-22 10:00
  • Bid opening (note): ጨረታው ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት ቆይቶ በ11ኛው ቀን 4፡00
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: ANRS Peace & Security Bureau
  • Bid bond: 20,000.00 ብር
  • Bid document price: 300.00 ብር
  • Published on: Be'kur (Oct 12, 2026)
  • Posted at: 2026-10-13T10:42:38.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders