House and Building Sale
ኢቲሲኤል ሪል እስቴት ኃላ/የተ/የግ/ማህ በአዲስ አበባ ከተማ ሜክሲኮ አካባቢ የሚገኘው እና አገልግሎቱ ለመኖሪያ አፓርትመንት የሆነው ብሎክ ላይ የሚገኙ የአፓርትመንት ቤቶችን በከፊል በተጠናቀቀ ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Description
2ኛ የጨረታ ማስታወቂያ
ሜክሲኮ አካባቢ የመኖሪያ አፓርትመንት ጨረታ
በአዲስ አበባ ከተማ ሜክሲኮ አካባቢ የሚገኘው እና አገልግሎቱ ለመኖሪያ አፓርትመንት የሆነው ብሎክ ላይ የሚገኙ የአፓርትመንት ቤቶችን በከፊል በተጠናቀቀ ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። የቤቱ መነሻ ዋጋ 89,000 ብር በካሬ ነዉ።
1. በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልግ ተጫራች የጨረታ ሰነድ ለመግዛት ማንነቱን የሚገልፅ መታወቂያ ኦሪጅናልና ኮፒ፣ በውክልና ሰነድ ለመግዛት ከፈለጉ የውክልና ማስረጃ እና መታወቂያ ይዞ በአካል መቅረብ ይኖርበታል።
2. በኢቲሲኤል ሪል እስቴት ኃላ/የተ/የግ/ማህ ሜክሲኮ አካባቢ በሚገኝው የአፓርትመንት ህንፃ ላይ በመምጣት የቋሚ ንብረቶችን ዝርዝር መረጃ የያዘ የተጫራቾች መመሪያ እና የዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ በብር 1,000.00 (አንድ ሺህ) ብቻ ከፍለው መግዛት ይችላሉ።
3. ተጫራች የጨረታ ሰነድ ገዝተው ማስታወቂው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ቀናት በስራ ሰአታት ውስጥ በመገኘት ለጨረታ የቀረቡትን ቋሚ ንብረቶች መመልከት ይችላሉ።
4. ተጫራቾች ለሚገዙት የሚገዟቸው ንብረቶች 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ) ብር የጨረታ ማስከበርያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ ለኢቲሲኤል ሪል እስቴት ኃላ/የተ/የግ/ማህ (ETCl Real Estate PLC) እንዲከፈል የታዘዘ ሲፒኦ CPO ከጨረታ ሰነዱ ጋር እና ማንነቱን የሚገልፅ መታወቂያ ኮፒ በማያያዝ በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል።
5. በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች ላሸነፉባቸው ንብረቶች 30% በአስር ቀናት ውስጥ የሚከፍሉ ሲሆን ቀሪውን 70% ደግሞ በሚቀጥሉት 12 ወራት ውስጥ የሚከፍሉ ይሆናል።
6. የጨረታ ሳጥኑ ጥቅምት 17/2019 አ.ም ከቀኑ 10፡00 ተዘግቶ በቀጣዩ ቀን ይከፈታል። የአሸናፊዋችም ስም ዝርዝር በቀጣዩ እለት በድርጅቱ ቢሮ ይለጠፋል።
7. አጫራች በማንኛውም ጊዜ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
8. ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 011-1-26-61-20 ወይም 09-77-55-50-27 ይደውሉ።
ኢቲሲኤል ሪል እስቴት ኃላ/የተ/የግ/ማህ
Tender details
- Deadline: 2026-10-27
- Bid closing time: 16:00
- Bid closing (note): ጥቅምት 17/2019 አ.ም ከቀኑ 10፡00
- Bid opening: 2026-10-28 16:00
- Bid opening (note): ጥቅምት 17/2019 አ.ም ከቀኑ 10፡00 ተዘግቶ በቀጣዩ ቀን ይከፈታል
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: ETCL REAL ESTATE PLC
- Bid bond: 100,000.00 ብር
- Bid document price: 1000.00 /አንድ ሺህ ብር/
- Published on: Addis Zemen (Oct 13, 2026)
- Posted at: 2026-10-13T11:22:55.000Z
- Source: Qelal Tenders