Stationery
በኢሉባቦር ዞን የመቱ ወረዳ ገንዘብ ትብብር ጽ/ቤት ለ2019 በጀት ዓ.ም የሚውሉ የተለያዩ የጽሕፈት መሳሪያዎች፣ የቢሮ ዕቃዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ የጽዳት ዕቃዎች፣ የተለያዩ የመኪና ጎማዎች፣ የሠራተኞች የደንብ ልብስ፣ የሞተር ሳይክል እስፔር ፓርቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
StationeryOffice Supplies and ServicesEquipment and Accessories
Oromia
More tags
Electrical, Electromechanical and ElectronicsComputer and AccessoriesIT and TelecomOffice Machines and AccessoriesCleaning and Janitorial Equipment and ServiceSpare Parts and Car Decoration MaterialsTextile, Garments and UniformsTextile, Garment and LeatherTri Wheeler, Motorcycles and Bicycles PurchaseOffice FurnitureFurniture and FurnishingShoes and Other Leather ProductsAmharic2merkatoMetu City FEDB
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
በኢሉባቦር ዞን የመቱ ወረዳ ገንዘብ ትብብር ጽ/ቤት ለ2019 በጀት ዓ.ም የሚውሉ የተለያዩ የጽሕፈት መሳሪያዎች፣ የቢሮ ዕቃዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ የጽዳት ዕቃዎች፣ የተለያዩ የመኪና ጎማዎች፣ የሠራተኞ የደንብ ልብስ፣ የሞተር ሳይክል እስፔር ፓርቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርት የምታሟሉ ነጋዱዎች መሠዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
- በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ኖሮት የታደሰ የንግድ ፈቃድ የያዘና የዘመኑን ግብር የከፈለ
- በንግድ ሚኒስቴር በአቅራቢነት ዝርዝር የተመዘገበና ማስረጃ ማቅረብ የሚችል
- የሚያሸንፉበትን የዕቃ ዋጋ ከብር 100,000 በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ለመሆኑ መረጃ ማቅረብ የሚችል
- ተጫራቹ ተጨማሪ የእሴት ታክስ VAT ተመዝጋቢ መሆኑን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ አለበት፡፡
- ለጨረታ ማስከበሪያ በጥሬ ገንዘብ ብር 35,000 ወይም በሲፒኦ( CPO) ማስያዝ የሚችልና ጨረታዉን ካሸነፈ በኋላ ለዉል ማስከበሪያ ያሸነፈበት ዕቃ የጠቅላላ ዋጋ 10% በባንክ ማስያዝ የሚችል
- ተጫራቹ ጨረታውን ካሸነፈ ዕቃዎቹን በራሱ ወጭ እስከ መቱ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ማቅረብ የሚችል፡፡
- መ/ቤቱ ለሚጠረጥራቸውና ማጣራት ለሚፈልገው የዕቃ ናሙና ማቅረብ የሚችል ሲሆን ነገር ግን የሠራተኞ የደንብ ልብስን በተመለከተ ተጫራች ከየዓይነቱ ናሙና የማቅረብ ግዴታ አለባቸው፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት በአየር ላይ የሚቆይ ሲሆን በ16ኛው ቀን 6፡00 ሰዓት ላይ የሚጠናቀቅ ሲሆን በዚሁ ቀን በ8፡00 ተጫራቾቹ ወይም ሕጋዊ ተወካዮቻቸው በተገኙበት በግልጽ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቹ የጨረታውን ሰነድ በማይመለስ 500 ብር በኢሉባቦር ዞን መቱ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 4 በመግዛት ዋጋቸውን ሞልተው ለዚህ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ቢሮ ቁጥር 4 በማስገባት ትችላላችሁ፡፡
- ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ተወካይ በጨረታው መክፈቻ ስነ-ሥርዓት ላይ ባይገኙ ፖስታውን መክፈት አያግደዉም ፡፡
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ፖስታ ኦርጅናልና ፎቶ ኮፒውን ማቅረብ አለባቸው::
ማሳሰቢያ ፡- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ሠይም ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥ 09 13 832 237/09 13 418 023/
251 471 410069
የመቱ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-10-31
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን 6፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-10-31 14:00
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን 8፡00 ሰዓት
- Region: Oromia
- Publishing entity: Metu City FEDB
- Bid bond: 35,000.00 ብር
- Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
- Published on: Addis Zemen (Oct 14, 2026)
- Posted at: 2026-10-14T07:52:50.000Z
- Source: Qelal Tenders