Textile, Garments and Uniforms
በሀድያ ዞን የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት የሰራተኞች የደንብ ልብስ ግዥ በአገር አቀፍ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Description
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
በሀድያ ዞን የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት የሰራተኞች የደንብ ልብስ ግዥ በአገር አቀፍ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም -
1. የደንብ ልብስ ግዥ
የጨረታ መመሪያ፡-
ተጫራቾች በዘርፉ የተመዘገቡበት የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ሥራ ፍቃድ፣ ግብር ከፋይነት ማስረጃ፣ የታክስ ክሊራንስ ማስረጃ ፣በመንግስት ግዥ ላይ መሳተፍ የሚችሉበት የአቅራቢነት ማስረጃና የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ ሆኖ የጨረታ ሰነዱን ከሆሳዕና ከተማ አስተዳደር ህንፃ አራተኛ ፎቅ ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 011 ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው ቀን ከጠዋት 2፡30 – 11፡30 ሰዓት ድረስ የማይመለስ 300/ሦስት መቶ ብር ብቻ/ በሆሳዕና ከተማ ገቢዎች ቅ/ጽ/ቤት በመክፈል ባለፍቃዱ ወይም ህጋዊ ወኪል ኦርጅናልና አንድ ፎቶ ኮፒ የሠነድ ማስረጃ በመያዝ መግዛት ይችላሉ፡ ፡ የጨረታ ሰነዱ የሚሸጠዉ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት ሆኖ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ታሽጎ በዚሁ ቀን ተጫራቾች በተገኙበት ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ይከፈታል፣
ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና CPO/፡-
ሎት1 የደንብ ልብስ ግዥ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 40,000 /አርባ ሺህ ብር ብቻ/ በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና፣ በማይሻር ሌተር ኦፍ ክሬዲት (L/C) የቀረበ ዋስትና፣ በጥሬ ገንዘብ ወይም በታወቀ ባንክ የተረጋገጠ CPO ወይም የክፍያ ትዕዛዝ ማቅረብ ይጠበቅበታል፣ ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን አንድ ኦርጅናል፣ ሁለት ፎቶ ኮፒ፣ የተፈረማና ቀን ያለበት የጨረታ ማቅረቢያ ሠንጠረዥ ሞልቶ እና የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /CPO/፣ እያንዳንዱን በፖስታ በማሸግ በመጨረሻም በአንድ በሰም በታሸገ እናት ፖስታ ውስጥ አስገብቶ በማሸግ የአጫራች መስሪያ ቤት ስም፣ የዕቃ ስም፣ የፓኬጅ ቁጥር እና የአቅራቢ ድርጅት ስም በፖስታዉ ላይ በመጻፍ፣ የአቅራቢ ድርጅቱን ማህተም በፖስታዉ ማሳረፍ፣በፖስታው ላይ ኃፊነት በተሰጠዉ አካል በመፈረም በሆሳዕና ከተማ አስተዳደር ህንፃ ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 011 አራተኛ ፎቅ ላይ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው ቀን 3፡30 ድረስ ማስገበት ይኖርባቸዋል፣
በእጅ የተሞላ ኮፒ ሰነዶችን እንደ ኦርጅናል ማቅረብ ከጨረታ ውድድር ውጭ ያደርጋል፡፡ የጨረታ ዋጋ በሰነድ ላይ በተዘጋጀ ቦታ ብቻ መሞላት አለበት፣ ሁሉም ተጫራች በጨረታ ሠነዱ እያንዳንዱ ገጽ ላይ የድርጅቱን ማህተም ማሳረፍና መፈረም አለበት፡፡ ይህ ካልሆነ ከጨረታ ሂደት ዉጪ ያደርጋል፡፡
ማንኛውም ተጫራች በሚያቀርበው ሰነድ ላይ አንድ ሐሰተኛ እና የተጭበረበረ ሰነድ ቢገኝ ከጨረታ ሂደት ወጪ ከተደረገ በኋላ በህግ ተጠያቂ ይሆናል፡፡
በጨረታ ሰነድ ይዘት ላይ ቅሬታ ያለበት ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከመከፈቱ 5 ቀን በፊት ቅሬታዉን በጽሁፍ ለመስሪያ ቤቱ ኃላፊ ቢሮ ቁጥር 001 ማቅረብ ይኖርበታል፤
ጨረታዉ ከተከፈተ በኋላ በጨረታ ሰነድ ይዘት ላይ የሚቀርብ አቤቱታ ተቀባይነት አይኖርም፣
ጨረታው የሚከፈተው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው የዉክልናዉን ኦርጅናል ይዞ ሲቀርቡ ይሆናል፣ ጨረታው በሚከፈትበት ቀንና ሰዓት ተጫራች አለመገኘት የጨረታ አከፋፈት ሂደቱን አያስተጓጉልም፣ መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፣
ለተጨማሪ መረጃ 0910 097 563/0916 838 549
የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-10-24
- Bid closing time: 09:30
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት ሆኖ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30
- Bid opening: 2026-10-24 10:00
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት ሆኖ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00
- Region: Central Ethiopia
- Publishing entity: Hosana City Administration Finance and Economic Development Office
- Bid bond: 40,000.00 ብር
- Bid document price: 300.00 (ሶስት መቶ ብር)
- Published on: Addis Zemen (Oct 14, 2026)
- Posted at: 2026-10-14T08:50:40.000Z
- Source: Qelal Tenders