Textile, Garments and Uniforms
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Textile, Garments and UniformsTextile, Garment and LeatherShoes and Other Leather Products
Addis Ababa
More tags
StationeryOffice Supplies and ServicesCleaning and Janitorial Equipment and ServiceHand Tools and Workshop EquipmentEquipment and AccessoriesElectrical, Electromechanical and ElectronicsMechanicalFood and BeverageFood Items and DrinksSpare Parts and Car Decoration MaterialsComputer and AccessoriesIT and TelecomOffice Machines and AccessoriesOffice FurnitureFurniture and FurnishingHouse FurniturePrinting and PublishingOthersMaintenance and RepairFurnitureOffice Machines and ComputersAmharic2merkatoAddis Ketema Sub City Small Tax Payers Branch Office
Description
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 001/2019 ዓ.ም.
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል
- ሎት1 የደንብ ልብስ፣
- ሎት 2 የጽሕፈት መሣሪያዎች፣
- ሎት 3 ኅትመት
- ሎት 4 የፅዳት እቃ፣
- ሎት 5 ልዩ ልዩ እቃ፣
- ሎት 6 የውሃ ግዥ፣
- ሎት 7 የመኪና እቃ፣
- ሎት 8 የቢሮ ዕቃ ጥገና፣
- ሎት 9 የአይቲ ዕቃ፣
- ሎት 10 ቋሚ እቃ፣ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ።
- በጨረታ ለመሳተፍ የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ሠርተፍኬት እንዲሁም የግብር ከፋይ መለያ ሠርተፍኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ለጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00 መቶ ብር በመክፈል ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናትና ቅዳሜን ሙሉ ቀን ጨምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ዊንጌት አደባባይ ድንገተኛ እሳት አደጋ መከላከያ ጎን በሚገኛው ሕንፃ 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 33 ግዢና ፋይናንስ የሥራ ሂደት በመቅረብ የጨረታ ሠነዱን በጥሬ ገንዘብ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሃሳባቸውን የአንድ ዋጋና ጠቅላላ ዋጋ የተጨማሪ ዕሴት ታክስን ያካተተ ዋጋ ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው በመሙላትና የድርጅታችሁ ማህተምና ፊርማና ሙሉ አድራሻችሁን በግልጽ በመጻፍ የሚወዳደሩበትን ሠነድ ኦርጂናልና ኮፒ ለየብቻ እንዲሁም የቴክኒክ ዶክሜንት ለብቻ በማድረግ በታሸገ ፖስታ መ/ቤታችን በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት የሚጠበቅበቸው ሲሆን መ/ቤቱ ባዘጋጀው የዋጋ ማወዳደሪያ ሰንጠረዥ ብቻ መሙላት አለበት።
- ተጫራቾች በተሳተፉበት አቅርቦት ላይ ለመ/ቤቱ የቴክኒክ ኮሚቴዎች ናሙና ለማቅረብ እና ናሙና ለማሳየት ፍቃደኛ መሆን ይጠበቅባቸዋል እና የጥራት መለኪያ፣ ስፔስፊኬሽን በተጠቃሚ ምርጫ መሆን አለበት።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000.00/ አስር ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ/C.PO. በጽ/ቤታችን ስም ማለትም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በሚል ስም በማስያዝ ከዋጋ ማቅረቢያ ጋር በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ እስከ 10ኛው የሥራ ቀን ቅዳሜን ጨምሮ ባሉት ቀናት እስከ 11:00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- የጨረታ ሣጥኑ ጨረታው በወጣበት በ11ኛው የሥራ ቀን ጠዋት 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጽ/ቤታችን በግዥና ፋይናንስ ቢሮ ውስጥ ይከፈታል።
- አሸናፊው ድርጅት የአሸናፊነት ውጤት በደብዳቤ ከተገለጸበት ከሰባተኛው ቀን በኋላ በመቅረብ የውል ማስከበሪያ የመጫረቻ ዋጋውን 10% /አስር ፐርሰንት/CPO በማስያዝ የውል ስምምነት መፈረም ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች አሸናፊ የሆኑባቸውን እቃዎች በራሳቸው የትራንስፖርት ወጪ ጭነው መ/ቤቱ የእቃ መጋዘን ውስጥ ማቅረብ የሚጠበቅበቸው ሲሆን እንዲሁም አንድ ተጫራች ሌላው በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም።
- በጨረታው የአሸነፉ ድርጅቶች እቃውን ባያቀርቡ ወይም ውል አንዋዋልም ቢሉ ያሲያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ ሙሉ በሙሉ ለመ/ቤቱ ገቢ ይሆናል።
- የጨረታውን ዋጋ 20 % መጨመር ወይም መቀነስ እንደተጠበቀይሆናል፡፡ ጨረታው ለ90 ቀናት ጸንቶ ይቆያል።
- ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው
ለበለጠ መረጃ : 0112735558/0112707761/0112706596 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-10-26
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው የሥራ ቀን ጠዋት 4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-10-26 10:30
- Bid opening (note): ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው የሥራ ቀን ጠዋት 4፡30 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Addis Ketema Sub City Small Tax Payers Branch Office
- Buyer address: መሳለሚያ ወረዳ 4 ወጣቶች ማእከል ፊት ለፊት የእህል በረንዳ አካባቢ ገበያ ልማት የሱቆች ግንባታ አክሲዮን ማህበር ሕንፃ ላይ 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 6 ሀብት አስተዳደር
- Bid bond: 10,000.00 ብር
- Bid document price: 300.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Oct 14, 2026)
- Posted at: 2026-10-14T09:08:27.000Z
- Source: Qelal Tenders